ራያ ቢራ፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ በእውነት ትንቢት ተናገረ

የጽሑፉ ዓላማ፥

ይህ ጽሑፍ በምንም ዓይነት መልኩ የራያ ቢራ ፋብሪካ ማስታወቂያ በ/ለመደገፍ ታስቦ የተዘጋጀ ጽሑፍ አይደለም። የጽሑፉ ዓላማ “በክርስትና” እምነት ተከታዮች ህይወት ላይ የነገሰና የሰለጠነ ልቅ የሆነ፣ ኸይ ባይ ያጣ የግብዝነት ህይወት ለመቀንጠጥ/ለማራገፍ ታስቦ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው።

የጽሑፉ ውስኑነት፥

ጽሑፉ በኢ-ሜይል አድራሻዬ ለተላከልኝ/ለቀረበልኝ ጥያቄ ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ሐተታ ነው። ከክስተቱ ተታይዘው ሊነሱ የሚችሉ በርካታ ጥያቄዎች ማለትም “የራያ ፋብሪካ ማስታወቂያ ትክክል ነው ትክክል አይደለም? ፤ ቢራ መጠጣት ኃጢአት ነው ኃጢአት አይደለም? ፤ በቢራ ጥርሙስ አንገት ላይ መስቀል ማንጠልጠልስ መስቀሉን ያረክሰዋል ወይስ መስቀሉ ቢራውን ይቀድሰዋል? ማስታወቂያው ከክርስትና ጋር በተለይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ሰውነት የሚያገናኘው ነገር አለው – የለውም? …”  እና ሌሎች ሊነሱ ስለሚችሉ ጥያቄዎች መልስ አይሰጥም። ጽሑፉ በይዘቱ መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት በማድረግ ተከሰተ በተባለ ጉዳይና ጩሆቱን እያቀለጠው ባለው ትውልድ መካከል ያለው አንፃራዊ ግኑኝነት ብቻ የሚያጠነጥን ፅሑፍ ነው።

ጽሑፉ ይነስም ይብዛ ምንም ዓይነት የአልኮል መጠጥ (ጠላና ጠጅ ጨምሮ) ለማይቀምስሱ፣ መጠጥ ባለፈበት የማያልፉ፣ ሃይማኖታዊ ሆነ ባህላዊ በዓላት ሲያከብሩ በውሃ ለሚያከብሩ ወንዶችና ሴቶች የክርስትና እምነት ተከታዮች/አማኞች አይመለከትም።

መሪ ቃል፥ 

(Read pdf) ራያ ቢራ፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ በእውነት ትንቢት ተናገረ

Advertisements