እንጀራህን የበላ ውሻ የአንተ አይደለም

የጽሑፉ ዓላማ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአጭር ጊዜ እንደ ወረርሽኝ የተዛመደው የሙስና በሽታ ለመዋጋት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያሳዩት ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እየተወሰዱት ያለው ቁርጠኝነት የተሞላበት እርምጃ የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሐን ሳይቀር ቀልብ ስበዋል። የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ሙስና፣ ሙሰኛና ሙሰኝነት በአገር ሉዓላዊነት፤ በህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚያደርሰው አደጋ በማስመልከት መጠነኛ ግንዛቤ ማስጨበጥ ሲሆን በተጨማሪ ሙስና፣ ሙሰኛና ሙሰኝነት ከምንጩ ለማድረቅ በሚደረገው ትግል ጸሐፊው ህዝብና መንግሥት እጅና ጓንት ሆነው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲል ይሞግታል። በመጨረሻም የጽሑፉ አዘጋጅ እንደ አንድ ዜጋ የኢ.ህ.አ.ዲ.ግ መንግሥት ሙስና ለመዋጋት በነደፈው ፕሮግራም ውጤታማነት ግላዊ ምክሩን ይለግሳል።

የጽሑፉ ውስንነት

በጽሑፉ ማብቂያ ከሰፈረ “ምክር” በተጨማሪ የሙስና፣ ሙሰኛና ሙሰኝነት ጸባይ፤ እንዲህ ዓይነቱ አደገኛ ወንጀል አስቸኳይ እርምጃ ያልተወሰደበት እንደሆነም በዜጎች የዕለት ዕለት ህይወት ጥቁር መጋረጃ ከመጋረዱ አልፎ በአገር ላይ የሚያደርሰው አደጋና ጠንቅ ያተኮረ ነው።

ትርጓሜ

ሙስና ምንድ ነው? ሙሰኛስ ማን ነው? የ “ባህሪ” ሥነ መለኮታዊ ትርጓሜው የአካል መገለጫ ተብሎ እንደሚፈታ ሁሉ የሙስና ፖለቲካዊ ትርጓሜ በተመሳሳይ – ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ኃላፊነትት … ጨምሮ ሌሎች የመልካም አስተዳደር መገለጫዎች አንፃር መሰለፍ የሚለው ሰፊ አንድምታ ሙስና ተብሎ ሊደመደም፣ ሊቀመጥና ሊተረጎም ይችላል። በሌላ አገላለጽ ሙስና – አንድን ግለሰብ/ቡዱን አጋጠሚዎች በመጠቀም የማይገባው፣ የራሱ ያልሆነ፣ ያልላበበት፣ ከሚገባው በላይ የሚሰበስብ፤ ጠቅለል ባለ መልኩ የሀገርና የህዝብ ንብረት/ሃብት ኢ-ፍትሃዊ/ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለግል ጥቅሙ የሚያውል፤ ድርጊቱ ሙስና ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን የድርጊቱ ፈፃሚ ሰው ደግሞ ሙሰኛ ተብሎ ይታወቃል። ሙስና እጅግ ጥልቅና ውስብስብ የሆነ ወንጀል ሲሆን የሙሰኛ ስብእና በተመሳሳይ የተወሳሰበ ነው።  ሙሉ የጽሑፉ ይዘት ለማንበብ ቀጥሎ የተቀመጠውን የ pdf ሊንክ ይጫኑ እንጀራህን የበላ ውሻ የአንተ አይደለም

Advertisements