የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራ ላይ የሚወስደው ማንኛውም የኃይል እርምጃ ፍትሐዊ ነው

ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ወታደራዊ ኪሳራዎች ያንኮታኮታት ሀገረ ኤርትራ ባለቤት ቀቢጸ ተስፋው የአስመራ መንግሥት በስራ ራሱን መለወጥ ሲያቅተውና በውድቀት ላይ ውድቀት፤ በኪሳራ ኪሳራ ተደራርበውበት ከፖለቲካ ክሳት አልፎ ሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው ሻዕቢያ “” የሚል ጊዜው ያለፈበት አባባል አነግቶ ለክፋትና ለአመጽ ከተጋ ዓመታት አልፋል። ምንም እንኳ የሚመክራቸው ምክሮች፣ የሚዶልታቸው ተንኮሎችና የሚያሴራቸው ሴራዎች ግባቸው ባይመቱም አቅሙ በፈቀደው ሁሉም ስራ ላይ የተሰማራ የኢትዮጵያ መንግሥት ወጥመድ ውስጥ ለማስገበትና ጠልፎ ለመጣልና ለማደናቀፍ የተቻልውን አድርጓል እያደረገም ይገኛል። ቁምነገሩ ሻዕቢያ ከዚህ በኃላ በሚቆፍሮው ጉድጓድ ራሱ እንደሚገባበትና እዛው በቆፈርው ጉድጓድ ውስጥ እንደሚቀበርም ይውጣ አልጠራጠርም። ሌላ ሲያቅተው ኢትዮጵያን “በሰብአዊ መብት” አያያዝ በዓለም ማህበረሰብ ፊት ለማስጠቆር ካሴራቸው የከሸፈበት የቅርብ የሻዕቢያ ትልቁ ሴራ ላውሳሎት።  

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፎ መሰጠት በተመለከተ በቀጥታም ሆነ በእጀ አዙር አስፈላጊውን መረጃ በመስጠትና በማስተላለፍ ረገድ ብዙ ነገር ሲለዋወት ያልተለወጠ ከነ አሮጌ ማንነቱና አስተሳሰቡ ያረጀ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ዋና ተዋናይ ናቸው ብዬ ነው የማምነው። የኤርትራ መንግሥት ይህን ያደርገበት ምክንያትም “የበርሃ ወዳጅነቱ” ለማስመስከር ሳይሆን የኤርትራ መንግሥት “ወያኔ” በማለት የሚከሰውን የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይዞ እንደ ሽንኩርት ይከታትፈዋል፤ እንደ አይጥም ጉድጓድ ውስጥ ይቀብረዋል ብሎ አሰፍስፎ ስለ ጠበቀ ነበር። ይህን አጋጣሚ በመጠቀምም ከውስጥም ከውጭም ኢ.ሳ.ትና የመሳሰሉ ደማቸው ሳይቀር ሕዝባቸውንና የአገራቸው ሉዓላዊት ለቁራሽ እንጀራ አሳልፈው የሸጡ ባንዳዎች በማሰማራት አውሎ ነፋስ እንዲሁም ወጀብና ማዕበል አስነሳበታለሁ በማለት ስለአመነ ነበር። ታድያ የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው የተቀበለበት አቀባበል፣ መስተንግዶና አያያዝ ሻዕቢያ በጠላትነት ፈርጆ ድምፃቸው ያጠፋቸው ዜጎቹ ዓይነት አረመኒያዊ አያያዝ ሳይሆን ሻዕቢያ ይሆናል ብሎ ካሰበውና ከጠበቀው አያያዝ በአንፃሩ ሆኖ በመገኘቱ የሻዕቢያ ወሽመጥ ቆርጦታል።   

ሻዕቢያ አቅሙ ኖሮት ዕድሉ ቢገጥመውና በለስ ቢቀናው አገራችን ኢትዮጵያ በመውረር የቀንድ አፍሪካ “ጎብለል” (አንበሳ) የመሆን ህልሙ እውን ለማድረግ የማይመለስ በደም የተጨማለቀ ጥርስ አልባ ውሻ ነው። ሐቁ፥ በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው የኤርትራ መንግስት ኦሮማይ አቅሙና ጉልበቱ ከድቶታል እንጅ ከገባበት ጉድጓድ ለመውጣትና ለማንሰራራት ተኝቶ ያድራል ብሎ ማመን የዋህነት ነው። በመዘዘው ካርታ ሽንፈትና ውርደት ከመከናነንብ ያለፈ ድል የማያውቀው የኤርትራ መንግሥት የቀረችው የጦርነት ጆከር መዞ ለመጫወት መገለባበጡም ለኢትዮጵያ መንግሥት እንግዳ ይሆንበታል ብዬ አላምንም።  

ሻዕቢያ ከነ ጭፍሮቹ ተጠርጎ ሬሳው ቀይ ባህር መዘፍዘፍ አለበት!

ምዕራባዊያን እንደሚደርጉት የጦር ሃይላችን ጡንቻ በመተማመን ሰበብ ፈልገን፣ ያልተገባ ስም ሰጥተንና ለጥፈን የሰው አገር ለማውደምና ደም ለማፍሰስ አምሮን አይደለም። የሰው አገር እየወረርንም አይደለም። ኢትዮጵያዉያን ይህን የማድረግ ፍላጎቱም ሆነ ምኞቱም የለንም ኖሮንም አያውቅም። በአንፃሩ ተዘሎ የተቀመጠ፣ የአገሩ ገፅታና ግለ ህይወቱን ለመለወጥ ደፋ ቀና እያለ ያለው ሰላማዊ ህዝብ ሰላም ለመንሳት አደጋ ጣዮችና ሰርጎ ገቦች በማሰልጠንና በማሰማራት የሌሊት ግርማ የቀን ፍላፃ በመሆን/ሆኖ ራሱን መቆጣጠርና አደብ መግዛት ተስኖት እየተናኮሰን ያለው አመፀኛ የኤርትራ መንግሥት ነው።

ወጣም ወረደ፥ ኢትዮጵያ እንደ አንዲት ሉዓላዊት አገር፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም እንደማንኛውም ሰላማዊ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ነው። በትረ ሥልጣኑን የጨበጠ የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ይሁንታውን ሰጥቶ በላዩ ላይ የሸሞው ህዝብ ሰላምና ደህነንት ከጠላት የመጠበቅ ሥልጣን፣ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ጠብቆ የማስጠበቅ የኢትዮጵያ መንግሥት ቀዳሚ ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ለዚህ ሰላማዊ ሕዝብ ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ የሆነው የኤርትራ መንግሥት መወገድ ግድ እስከሆነ ድረስ ሻዕቢያ ስመ ዝክሩ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት ከሚያዋስኑት አከባቢ ብቻ ሳይሆን ህልውናውና ታሪኩ ከምስራቅ አፍሪካ መሰረዝ/መደምሰስ አለበት። የአገራችን ዕድገትና ብልፅግና ለማደናቀፍ የማሰናከያ ዐለት (አሽክላ) የሆነው ሻዕቢያ ከነ ጭፍሮቹ ተጠርጎ ሬሳው ቀይ ባህር መዘፍዘፍ አለበት።

ልማት እንጅ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓቢይ ትኩረት ሆኖ አያውቅም!

የብዙሐን አገር ኢትዮጵያ ሻዕቢያ ባሻው ሰዓት እንደፈለገ የሚተናኩሳት ሰው አልባ “ምስኪን” አገር ሳትሆን እንደ አንዲት ሉዓላዊት አገር የሕዝቦችዋን ህልውና የሚፈታተን ማንኛውም ኃይል የመመከት፣ የማድቀቅና የመቅበር ሙሉ ሥልጣን ያላት አገር ናት።

ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት አይደለም። ልማት እንጅ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓቢይ ትኩረት ሆኖ አያውቅም። ጦርነት ያደከመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦርነት መተኪያ የሌላት የሰው ነፍስ የሚበላ፣ አውዳሚ፣ የሞት እኩያ ነው! ብሎ ነው የሚያምነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም እንኳ ታሪኩ የጦርነት ታሪክ ቢሆንም በጦርነት የሚገኝ ትርፍ ግን አጥብቆ የሚፀየፍ ሕዝብ ነው። በጦርነት አተርፋለሁ በማለት እረፍት እየነሳን የሚገኘው፤ እያቆሳሰለንና እያደማን ያለው የኤርትራ መንግሥት ነው። ታድያ የኢትዮጵያ መንግሥት ይሄድበት ዘንድ እየተገደደበት ያለው መንገድ የኤርትራ መንግሥት ምርጫ እስከሆነ ድረስ ሻዕቢያ በምርጫው የማይስተናገድበት ምክንያት ምንድ ነው?

አገራችንና ህዝባችን ከጣላት ለመከላከል የማን ትዕዛዝ ነው የምንጠብቀው? አሜሪካና አውሮፓ ባሻቸው ሰዓት ካላንቀሳቀሱትና ይሁንትቸውን ካላገኘን በስተቀር የገዛ ራሳችን አገርና ህዝብ ከጠላት መከላከል አይችልምን? ለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የሲዖል አጋፋሪው መናገሻ የሆነው የአሥመራ ቤተ መንግሥት የማያፀዳበት ምክንያት ምንድ ነው? ኢትዮጵያ ይህን ለማደረግ ከህግም ከሞራልም አንፃር በርካታ ተጨባጭ ምክንያቶች የላትም ወይ? ኢትዮጵያ በአስመራ መንግሥት ላይ የምትወስደው ማንኛውም የሃይል እርምጃ ፍትሃዊ ነው እያልኩ ነው።  

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ፅሑፉን በማስመልከት ጸሐፊው ለመገናኘት yetdgnayalehe@gmail.com ይመይሉ።

Advertisements