አጽናኝ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ጋር ይሁን

በመጀመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዓለም መገናኛ ብዙሐን ርዕሰ አንቀጽ ወይም ማነጋገር ርዕስ ሆኖ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመላ ዓለም ስሙ የተዋወቀው “አይ.ሲ.ስ” ተብሎ የሚታወቀው የጥፋት መልዕክተኛ – የጥፋት ሃይሉ ከተቋቋመበት ዓላማ ምንም ዓይነት ግኑኝነት በሌላቸው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከአገራቸው በወጡ በንጹሐን ወንድሞቻችን ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በምድሪትቱ ከነገሰው አረመንያዊ አገዛዝ ለማምለጥ ከአገራቸው ተሰደው የሞት ሞት ሰለባ ለሆኑት ኤርትራውያን ላይ የፈፀመው አሰቃቂና ኢ ሰብአዊ ድርጊት የተሰማኝ ጥልቅ ሐዘን ስገልፅ በተሰበረ ልብ ነው። በመቀጠልም የጥፋት መልዕክተኛው ሰለባ ለሆኑት ወንድሞታችን ዕረፍተ ነፍስ በመራር ሀዘን ውስጥ ለምትገኙ ወላጆችና ቤተ ዘመድ እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን (ኤርትራውያን) በሙሉ ፍጹም የሆነ መፅናናት የሚሰጥ እግዚአብሔር ነውና አጽናኝ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ጋር ይሁን ለማለት እወዳለሁ። 

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

April 26, 2015  

Advertisements