ዕድለ ሰባራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ተናገረ አልተናገረ …

የፅሑፉ ውስኑነት

ፅሑፉ የቃለ ምልልሱ አንደኛውን ክፍል ዙሪያ ብቻ የሚያጠነን ነው። በአቀራረቡ ለንባብ በሚያመች እጅግ አጠር አጠር ባለ መልኩ በንዑስ ርእሶች ተከፋፍሎ የቀረበ ሲሆን ከጊዜ አንፃር በግርድፉ የቀረበ ሐተታም ነው።

የፅሑፉ ዓላማ

የኢሳት ዓላማና ድርሻ በሰፊውም የፕሬዝዳንት ኢሳይይስ አፈወርቂ እስትንፋስ መፍታትና መተርጎም ሲሆን አንዳንድ ቦታዎች “አንተ” በሚል በነጣላ አገላለፆች የተቀመጡ ዓረፍተ ነገሮች ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ እንደ አገር መሪ የሚገባቸውን ክብር ከመሳት ጋር ምንም የሚያገናኝ ነገር እንደሌለው አንባቢ ይገነዘብ ዘንድ እጠይቃለሁ።   

መንደርደሪያ

ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ገፅታ በማስመልከት መልካም ምስክርነት መስጠት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባል መሆን አይጠይቅም። ለውጥ አለ? የለም? ብሎ የደንቆሮ ሙግት ውስጥም አልገባም። የትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ፖለቲካ የሰከረ፣ የከሰረ የዲያስፖራ የትርፍ ጊዜ የዕንደት ፖለቲካ የተነከረ ግለሰብ ካልሆነ በስተቀር የሚያይ ዓይን ያለው ዜጋ ሁሉ የሚያየው ለውጥ አለ። “የሚታየኝ ነገር የለም” የምትል ነፈስ ያለች እንደሆነም በእውነትቱ ነገር በኢትዮጵያ ምድር የሚታይ ነገር ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን የሚያይ ጤናማ ዓይን እንደሌለህ ስነግርህ በታላቅ አክብሮት ነው። ኢትዮጵያ እንደ አገር የዓለም መድረኮች እያጣበበች በምትገኝበት ሰዓት የኢትዮጵያ ቡናና ቆዳ የራሱን ምርት በማስመሰል ለዓለም ገበያ በማቅረብ በማጭበርበር “ኤርትራን ሆንግኮንግ አደርጋታለሁ” ሲል በቅጀት ብዛት ራሱን ያበላሸ ህልም ያበሰበሰውና በቁሙ ገድሎ የቀበረው ፕሬዝዳት ኢሳይያስ አፈወርቂ በለውጥ ጎዳና እየተራመደች ያለችው አገርና ሕዝብ አስመልክቶ ምን እንዲል ነው የሚጠበቀው? ሆንግኮንግ ኤርትራ አጠገብ ስትገነባ እያየ አስችሎት እጁና አፉ ሰብስቦ ቢቀመጥ ነበር የሚደንቀኝ። ሐቁ ይህ ነው፣

 • አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከሃያዎቹ አመታት በፊት የሚያውቃት/ያውቃት የነበችው ኢትዮጵያ አይደለችም። የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የዘወትር ምኞትና ፀሎትም የፈራረሰችና የወደመች ኢትዮጵያ እንጅ የተለወጠች ኢትዮጵያ ማየት አይደለም። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሌሉ ብሔሮች ጨምሮ አደጋ ጣዮች እያሰለጠነ የሚያሰማራው አንዲት፣ የበለፀገች፣ ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ ለመገንባት ነው እንዴ? ሲበዛ የዋህ ኖት።
 • የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ዓይኑ እያየ ጆሮውም እየሰማ የተለወጠችና በለውጥ ጎዳና እየገሰሰች ያለች አገር ናት። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሰላም የኢትዮጵያ ሕዝብ መረጋጋት መየት የማይፈልግ ሰይጣን በእሳት ያጠመቀው የደም ሰው መሆኑን ነው ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው።
 • ኢትዮጵያ በገዛ አገራቸው መኖር የተሳናቸው ስደተኞች ኤርትራውያን ተቀብላ በማስተናገድ ለኤርትራውያን ስደተኞች የተስፋይቱ ምድር የሆነች አገር ናት።
 • የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ እንደ ግለ ንብረቱ በፈላጭ ቆላጭነት የሚገዛት ሰማይ የተደፋባት ኤርትራ ሳትሆን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት የተረጋገጠባት የዜጎች አገር ናት።
 • ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖትና ስልጣኔ ባለቤት የሆነ የብሔር ብሔርሰቦችና ሕዝቦች ድምር ውጤት አገር ናት። ለዚህ ሁሉ ያልታደለች ዕድለ ሰባራ ሀገረ ኤርትራ መሪ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የሚመራት አገር የሚገልፅበት ቋንቋ የሰው አገር ላይ ሲጠቀመበት ስሰማ ብዕሬን አነሳ ዘንድ ግድ ብሎኛል። መልካም ንባብ

“አጀባ” – ከራሱ ጥላ ጥቃት እንዳይደርስበት ነውን?

“በኤርትራ ቆይታችን ብዙ ነገር ያስገረሙን ነገሮች አሉ በተለይ የኤርትራ ባለ ስልጣናት በአጀባ አይንቀሳቀሱም። … ሁሉም ባለስልጣናት ስንመለከታቸው መንገድ ላይ ሲሄዱ ነው። አጀብ የላቸውም። ይሄ ከምን የመነጨ ይመስሎታል?” መሳይ መኮነን

መሳይ ከበደ የኤርትራ ባለ ስልጣናት በተመለከተ የታዘበው ቀለል ባለ አማርኛ ያስቀመጥነው እንደሆነ መልዕክቱ የሚከተለውን ይመስላል። “የአስመራ ባለ ስልጣናት ስራ ፈት ናቸው። አንድም ስራ አጥ ናቸው እያለን ነው።” እውነት ነው ሰው ስራ ሳይኖረው ሲቀር ነው መንገድ ለመንገድ ሲንቀዋለል ፀሐይ የምትጠልቅበት እንጅ የስራ ሰው መንገድ ለመንገድ የሚልከሰከስበት ጊዜም የለው። ባለ ስልጣናቱ ተጨማሪ በድለላ ስራ የተሰማሩ ካልሆኑ በስተቀር።

ግድ የለህም መሳይ፣ እውነትም የኤርትራ ባለ ስልጣናት መንገድ ለመንገድ ሲርመሰመሱ ካያሃቸው እነሱም የረሃብ አለንጋ እየተገረፈው ያለ ኤርትራዊ ዜጋ እኩል ስራ ፍለጋ የስራ ማስታወቂያ ሲያነቡ አይተሃቸው ነው። ከመሳይ ከበደ መልዕክት ይልቅ ግን ፕሬዝዳንቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ “የህሕቡ ሁኔታ” ነው ሲሉ የሰጡት መልስ ፕሬዝዳንቱ አሽቃባጩ መሳይን ደህና አድርግገው መርፌ ወግተውልኛል።

 • ጎበዝ!
 • ተኮሶ የሚገድል፣
 • ቡጢ ሰንዝሮ የሚዘርር፣
 • አደናቅፎ በአፍ ጢም የሚደፋ፣
 • አንቆ የያዘ እንደሆነም ትፋሽ የሚያሳጣ፣
 • ድንጋይ ወርውሮ የሚፈነክትና የሚያደማ፣
 • ዱላ ይዞ አናት የሚያፈርስ ትውልድ – ምድሪቱ የምትባላ እሳት ሆናችበት ጥሎ በኮበለበት ዘመን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ምን አጀባ ያስፈልገዋል? ከራሱ ጥላ ጥቃት እንዳይደርስበትና እንዳይፈፀምበት? ኤርትራ ውስጥ ደም ያለው ውሻ ተፈልጎ አይገኝም አይደለም ደም ያለው ወጣት ሊገኝ ቀርቶ። ወይ ኢሳት! ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮሃለች።

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ “አጀባ የላቸውም” በሚል ርዕስ ዙሪያ በሰጡት መልስ “የምዕራባውያን” ጉዳይም አንስተዋል። ይህ ለማናችንም ቢሆን አዲስ ነገር አይደለም። ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን መስኮት በቀረቡ ቁጥር ስለ እርሻ እያወሩም እንደ ምንም ምዕራባውያን ሳይራገም ያለፈበት ዘመን ተፈልጎ አይገኝም። በእውነቱ ነገር ኤርትራ የገብስ ገለባ ያክል ክብደት የሌላት የበነነች አገር ለመሆንዋ ጥያቄ የለውም።

ኤርትራ እንደ አገር የተረሳች አገር ናት። የኤርትራ ባለ ስልጣናት መሆን እንቢ ሲላቸው ዓለም ታስታውሳቸው ዘንድ ያደረጉት ነገር ቢኖርም የንፁሐን ዜጎች ደም ማፈሰስ የሚያረካው “አልሽባብ” ካለበት ድረስ በመሄድ ዝምድና መመስረታቸው ነው። ከዚህ ያለፈ ኤርትራ እንደ ሀገር ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደ አገር መሪ ስመ ዝክራቸው የሚያነሳቸው ሆነ የሚያወሳቸው አካል የለም። እንዲህ ባለ አሳፋሪ ሁኔታ የምትገኝ አገር ማን ነው ድንበር አቋርጦ ስራ አጥ የኤርትራ ባለ ስልጣናት የሚተናኮል? መሳይ ከበደ – እውነት የሚቀበል ልብ ሆነ የሚያስብ አእምሮ አልፈጠረብህም እንጅ ዓለም – የኤርትራ ባለ ስልጣናት በተመለከተ እዛው ችጋርና ርሃብ ይግደላቸው ብላ በኤርትራ ላይ ፊትዋ ካዞረች ዓመታት ተቆጥረዋል።

*********

 ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደ መልከ ፃዲቅ?

“ወደ ልጅነትዎ አስተዳደግ ልመለሶና እኛ ብዙ አናውቅም የትግል ህይዎትዎን እናውቃለን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ማን ናቸው? አስተዳደጋቸው ወደዚህ ትግል እንዴት ገቡ እስቲ እንደው የልጅነትዎ አስተዳደግ የተማሩትን ከዛ ወደ ትግል እንዲገቡ ያደረጎት እንደው እስቲ ይንገሩን።” ፋሲል የኔዓለም

አስተዳደግህ? የልጅነት ህይወትህ ምን ይመስላል? ሲባል “የትግል ፍሬ ነኝ .. የሃምሳ ዓመታት ውጤት ነን” ብሎ ነገር መቀላቀል ምን ይሉታል? ተጋዳላይ ኢሳይያስ ተብሎ ከመጥራቱ በፊት ኢሳይያስ ህይወት አልነበረውምን? ይህ ሰው ከሰው አልተወለደም? በእውነት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አባትና እናት ወንድም እህት የሉትምን? ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ተለይቶ የሚታወቅ የተወለደበትና ያደገበት አከባቢ የለውምን? እንደ ማኛውም ሰው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ እድገቱንና ትውልድ ቦታውን በተመለከተ ለሚቀርብለት ጥያቄ ዘመኑን በሙሉ በማጭበርበና ጥያቄውን በማድበስበስ ከማለፍ ይልቅ “ተወልጄ ያደግኩት ጅብሩኽ መቐለ ነው።” በማለት መልስ ቢሰጥ ምን ይሆናል? በኤርትራውያን አንደበት “ኢሳይያስ ዓጋመ ነው” መባሉ እንደሆነ አልቀረም። ነገሩ እንዲሁ ተድበስብሶ የሚድበሰበስ አይደለምና።

በአጭሩ ከዚህ ቃለ ምልልስ በተለየ መልኩ ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ግለ ሰብዕና የተማርኩት ነገር ቢኖር ግለሰቡ በግለሰብ ደረጃ ግልፅነት የጎደለበት፣ ለህዝቡ የማይታመን፣ አመኔታ የማይጣልበት፣ በራሱ የማይታመንና የሚያፍር፣ የማንነት ቀውስ ያለበት – አስመሳይና ተመፃዳቂ ግለሰብ ሆኖ ነው ያገኘሁት። አቦይ ስባት አይደለም ጥያቄ አቅርበህለት ባትጠይቀውም “በእናቴ ኤርትራዊ ነኝ … በእናትም በአባትም በኩል ሙሉ በሙሉ ኤርትራዉያን የሆኑ ከፍተኛ ባለ ስልጣናትና የህወሐት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት በእኛ መካከል አሉ” በማለት መልስ ይሰጣሃል።

ኤርትራ – ማርና ወተት የሚፈስባት አገር?

“ወደ ባለሰልጣናት ወደ እርስዎም ልምጣ። በጣም ቀላል የሆነ ህይወት ነው የምትኖሩት። አሁን እርስዎን ራስዎት ያገኘኖት በዚህ በበርሃ ውስጥ እንደማንኛውም ዜጋ ስራ እየሰሩ ልብስዎ አጠቃላይ ሁኔታ እንደማንኛውም ሰራተኛ ነው ሆነው ያገኘንዎትና ይሄ የኤርትራ ህዝብ የማንነት መገለጫ እንዲሆን እያደረጋችሁት ነው?” መሳይ ከበደ

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ኤርትራ የአማራ፣ ኦሮሚያና የትግራይ ጠቅላይ ግዛቶች ዕድገትና ስልጣኔ ሊኖራት ቀርቶ አናሳ ብሄሮች ተብለው የሚታወቁ የእነ ቤንሻንጉል ጉምዝና የአፋር ክልሎች ጫፍ የሚደርስ መሰረተ ልማት የላትም። ሌላው ቀርቶ የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ የሆነችው አስማራ በምሳሌነት የወሰድን እንደሆነ ከተማይቱ ወሃ በቦቴ፣ ወተትና ዳቦ በቀበሌ የሚታደልባት ዘይት እርም የሆነባት ሳትበቅል የጠወለገች አገር ለመሆንዋ ድፍን አለም የሚያውቀው ሐቅ ነው።

የማይገባኝ ነገር ቢኖር ባዕድ ጠፍጥፎ የሰራት አገር ተይዞ “ዘራፍ!” ማለት ነው። ኤርትራ እንደ ፕሬዝዳንቱ ሰውነት የጠወለገች አገራት ናት። የአስመራ ስም በተነሳ ቁጥርም ጣሊያን የሰራው መንገድ፣ ካቴድራል፣ የነዳጅ ማድያ … መወሳታቸው የማይቀር ነው። ቁምነገሩ እነዚህ የጣሊያን ውጤቶች በአሁን ሰዓት ከሚሰጡት አገልግሎት ይልቅ በጥገና ብዛት የተዳከሙ ናቸው። ሻዕቢያ ሰራሁት የሚለው ሰንበል አከባቢ ኮሪያ የገነባቸው በጣት የሚቆጠሩ ህንፃዎች እንደሆነም በኢትዮጵያ ብር የተሰራ ዛሬ የአይጥና የሸረሪት መተላለፊያ/ምሽግ ሆኖዋል። ከነተረቱ “ማሽላ እያረረ ይስቃል” እንደሚባለው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ዕድገትና ለውጥ እንዲህ የሚያስፏጨው ምክንያት ቅናትና ምቀኝነት ከመሆኑ ያለፈ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም።

የኤርትራ ሕዝብ መገለጫማ ፍዳ፣ የመረረ ዋይታ፣ ስደት ብሎም ሞት ነው። ኤርትራዊነት ስደት ነው። የኤርትራ ሕዝብ የት ነው ያለው? ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ሊብያ፣ ጣሊያን፣ እስራኤል … እንደ ጨው የተበተነ መከረኛ ህዝብ ኤርትራዊ አይደለምን? ላምቤዱዛ ውቅያኖስ የዋጠው ሕዝብ (367) ኤርትራዊ አይደለምን? በመላ ዓለም የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያዎች ያጣበቡ ኤርትራውያን አይደሉምን?

የኤርትራ ሕዝብ ጥጋብ አንቆት ነዋ የአራዊት ቀለብ እየሆነ ያለው? ኤርትራዊ በወጣበት መቃብር እየተቆፈረ እየተቀበረ ያለው አስመራ በልማት ብትጣበብ ነዋ? አካላቱ ተተልትሎ በሲና በርሃ የቀረው ኤርትራዊ አስመራ ውስጥ ልማት፣ ፍትህና ሰላም ቢኖር ነው? አስራ ሁለት ሚኒትሮችዋ ውጣ አስቀረች አገር በልማት ብትሰክር ነዋ? ውድ አናባቢ ሆይ! እውነት መናገር ያልፈጠረበት ኢሳት ስላለ ሳይሆን እርስዎ ስለ ኤርትራንና ኤርትራውያን ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያውቁትን ለኢሳት መልሰው ይንገሩልኝ።

ላለፉት በርካታ ዓመታት ዘርዋን እየዋጠች፣ ደም እያስለቀሰችና እየመነጠረች የምትገኘው ምድር – ኢሳት “ኤርትራ በልማት ሰክራለች” ማለቱስ እርስዎን መስደቡ አደለምን? ኢሳያይስ አፈወርቂ አትበላ አትጠጣ ያደረጋት አገር ኢሳት ኤርትራ በልማት ብዛት ሰክራልች በማለት ማሽሟጠጡ ከምንም በላይ ለኤርትራውያን ትልቅ ስድብ ነው።

*********

የራሷ አሮባት የሰዉ ታማስላለች!

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የተጠየቀው ጥያቄ ትቶ እዚም እዛም መርገጥ፣ ነገር መዘበራረቅ፣ ከተነሳ ጥያቄ ምንም ተያያዥነት የሌለው መልስ መስጠት፣ ወጥነትና ተፋሰስ አለመጠበቅ፣ ጥያቄውን ጨርሶ የመርሳትና የነገር ማስረዘም የተመደ ነው። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በበላይነት ከሚመሩት ፀረ የትግራይ ሕዝብ የእልቂት ዳንኬራ በመምታት የሚታወቀው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በከፊል ፕሬዝዳንቱ አዲስ ማንነት ይዘው ብቅ ብለዋል። ይኸውም ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በሚገርም ሁኔታ የባህል አስተማሪና ተቆርቃሪ ሆኖው መቅረባቸው ነው። በፕሬዝንዳቱ በኩል የተነሱ ነጦቦች ምንም ችግር የለኝም። ችግሩ በብተኝነት የሚመራት ኤርትራ በማንነት ቀውስ የታመሰች አገር ሆና ሳላች ሌሎች የአፍሪካ አገራት ለመውቀስ መድፈሩ ነው።

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ስለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የባህል መዛባት ለመናገር ሙሉ ሰው አይደለም። የሞራል ብቃት የለውም። አባባሌን በጭብጥ ላስደግፍ – ኤርትራ የራስዋ የዘመን አቆጣጠር የሌላት እንግሊዝና ጣሊያን ሲፈራረቁባት የወለደችው ዲቃላ እንደያዘች የምትገኝ አገር ናት። ኤርትራ በፈረንጅኛ ነው የምትቆጥረው።

መች ይሄ ብቻ ኤርትራ አንድም ዓረብኛ ተናጋሪ ብሔር ሳይኖራት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ወደ ስልጣን ከወጡ ዘመን ጀምሮ (አሁን ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ባላውቅም) ዓረብኛ የአገሪቱ መንግስታዊ ቋንቋ እስከመሆን ድረስ ሲራገብ እንደነበር የትናንት ትውስታች ነው። ጎበዝ! ከዚህ በላይ የማንነት ቀውስ ምን አለ? ፓስታ መብላት ለኤርትራውያን የስልጣኔ መገለጫ ነው። የራስዋ ባልሆነ ነገር በክፉ ትምክህት የተወጠረች አገር ተይዞ በሌሎች ላይ አፍህን ማላቀቅ ምን አመጣው? አመል ነው እንጅ። የማያረጅ ክፉ አመል።

********

ኢሳይያስ ተናገረ አልተናገረ ..

በሁለቱም አገራት ማለትም በኢትዮጵያ በኤርትራ መካከል ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ያብራሩ ዘንድ በቀረበ ጥያቄ ፕሬዝዳንቱ ስፊ ጊዜውን ያጠፋው የኢትዮጵያ ገፅታ የጥላሸት በመቀባት ነበር። የኢትዮጵያ ከበርካታ የበለፀጉ ምዕራባውያን አገራት ያላት መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት እድሉ የተነፈጉ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የኢትዮጵያ መንግስት መመጠቅ ክፉኛ አበሳጭተዋል።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ኢትዮጵያ ተጓራባች አገሮች ጨምሮ ከምዕራቡ ዓለም ያላት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ወታሃደራዊ ግንኙነቶች የበለጠ መዘርጋት እንደሚጠበቅባት ሳይዘነጋ ሆኖም ግን በአመርቂነቱ የሚነሳ ዕድገት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ምነው የእግር እሳት ሆነበትሳ? የኤርትራ መንግስት ገበያ አልሆን ብሎት ነገሩ ከስሞበት ነው እንጅ’ኮ የገዛ አገሩ አንዴ ለኢራን ሌላ ጊዜ ለእስራኤል አሁን ደግሞ ለራሽያ ለማከራየት፣ ለመሸጥና ለመለወጥ ያላንኳኳው ደጅ፣ ያልተማፀነው የአገር መሪ፣ ያላደረገው ያልሆነውና ያልሞከረው ሙከራ የለም። ሳይቀናው ሲቀር ግን የቀናት አገራችን ማተረማመስና የሕዝባችን ሰላም ለማደፍረስ ይሄው አፉን ለማላላቀቅ እንኳን አላፈረም።

እኔ’ምለው! ኢሳይያስ ተናገረ አልተናገረ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚፈጥረው ተአምር ምንድ ነው? ኢሳት “መዋቹ አብርሃም አፈወርቂ ነጠላ ዜማ ለቀቀ” በማለት ዜና ቢሰራ “ኢሳይያስ አፈወርቂ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ” ከሚለው ቀልድ ይልቅ ክብደት እንደሚኖረው ምንም አያጠራጥርም። ኖረም አልኖረም ህልውናው ትርጉም ለማይሰጠው ሕዝብ “ኢሳይያስ አፈወርቂ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ” ብትለው ምን ትርጉም ይሰጠዋል? ኢሳይያስ አፈወርቂ ኖረም አልኖረም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰጠው ትርጉም የለውም። ለመሆኑ ኢሳይያስ ለኢትዮጵያ ምንዋ ነው? አቦ ኢሳት! ለነገሩ በጥላቻ የታወረ ልቦና እንዴት ፖለቲካ ይገባዋል። ወጣም ወረደ ኢሳይያስ ተናግሮ የሚያሰማው ሕዝብ እንደሌለ የአደባባይ ምስጢር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነም ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወቂን የሚያውቀው በዚህ መልኩ ነው፣

 • ከጎረቤት አገሮች ሰላም የሌለው ሰላምን የማያውቅ ፀበኛ፣
 • ስድስት ሚልዮን ህዝብ መምራት ተስኖት ኤርትራ አገር መሆንዋ ቀርቶ ወደ ጣራ አልባ እስር ቤት የለወጠ፣
 • ግራና በቀኝ ትክሻውን ደግፈው እዚህ ያደረሱት ጓደቹን ያለ ርህራሄ ጉድጓድ ቆፍሮ የቀበረ ደመኛ፣
 • ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ቅርጥፍ አድርጎ የበላ ነፈሰ ገዳይ፣
 • ስራ መስራት ሲያቅተው የሚሰራ ህዝብና መንግስት ለማደናቀፍ አድፍጦ የተቀመጠ አሽክላ፣
 • ስራ ከመስራት ይልቅ ዘመኑን በመግለጫ ብዛት የጨረሰ ወሬ የማይልቅበት የወሬ ጎተራ፣
 • ግለ ፍልስፍና (አንድ ግለሰብ እንደ ግለሰብ የሚያምነው እምነት/የሚያራምደው አቋም ማለት ነው) ከማህበረ ሰብአዊ እንዲሁም መንግስታዊ ፍልስፍና ጋር የተምታታበትና የተቀላቀለበት ባለ አመል፣
 • ብልጭ ያለውን የሚያደርግና የሚፈፅም ራዕይ አልባ መሪ መሆኑን ነው በተጨባጭ የሚያውቀው። ታድያ ድፍን 80 ሚሊዮን ሕዝብ የሚያውቀው ሸክላ የወርቅ ቅብ መቀባት ትርፉ ምንድ ነው? እንግዲያውስ እንዲህ ያለ የኢሳት እብደትና ቅሌት ሌላው ቀርቶ ደጋፊዎቹ ሳይቀሩ የሚያንገሸግሽ ከንቱ ልፋት ከመሆኑ ያለፈ “ኢሳይያስ አፈወርቂ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ” ብሎ ዲስኩር ምንም ዓይነት አጥጋቢ ፖለቲካዊ አንድምታ የለውም ሊኖረውም አይችልም።

እውቀት ወይስ ምቀኝነት?

“እርስዎ የዚህ የአሁን የኢትዮጵያ ፌደራል ስርዓት መሃንዲስ እንደሆኑ የእርስዎ ሃሳብ እንደሆነ ኢትዮጵያን ለማዳከም ብለው እንደ ከሌሎች የቀኝ ፖለቲካ አራማጆች እንደ ኢህፓ መኢሶን ከመሳሰሉት ይልቅ ወያኔን አቅርባችሁ ወያኔን ደግፋችሁ ወያኔን አሳድጋችሁ ለዚህ ስልጣን አበቃችሁ። ከዛም በተጨማሪ ህገ መንግስትቱን በተመለከተ እርስዎ አቶ ሌንጮ ለታና አቶ መለስ ዜናዊ በጋራ እንዳረቀቃችሁትና ይሄ ሁሉ የእርስዎ የአእምሮ ውጤት እንደሆነ በታሪክ የሚቀርበው።”

ጥያቄው ሆነ መልሱ ግልፅ ነው። በፋሲል/መሳይ በኩል የተሰነዘረው ጥያቄ ቀዳሚ ዓላማ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የማጀገን (ታላቅ አዋቂና ሊቅ የማድረግ) ነገር ሲሆን። በፕሬዝዳንቱ በኩል የተሰጠ መልስም “እውነት ነው! እንደ እኔ ያለ አዋቂ የለም!” የሚል ነው። በእውነቱም ከተቀረፀው ምስል በግልፅ እንዳይየነው የቀረበላቸው ውዳሴ ከአንዴም ሁለቴ ፈገግ አስብሎቸዋል። አሁን ደግሞ ጥያቄው ሆነ የተሰጠ መልስ ፀረ ሀገርና ፀረ ሕዝብ የተሰራ የኢሳት ከንቱ ድራማ መሆኑን ላሳዮት።

ኢሳት ጨመሮ በአንድ ብሔር የበላይነት የሚያምኑና በኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ህልውና የማይቀበሉ ትምክህተኞች በኢፈዲሪ ህገ መንግስት ላይ ያላቸው ጥላቻና የሚያራምዱት ጨለምተኛ አቋም ለሁላችን ግልፅ ነው። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብትና ስልጣን ያረጋገጠ ህገ መንግስት አንቀበልም ባዮችም ናቸው። ይሁንና ዛሬ ደግሞ ኢሳቶች በአደባባይ ይህን የመስለ የመጠቀ የአእምሮ ውጤት ያበረከቱልን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ናቸው ብሎ ፕሬዝዳንቱን ሲያሞካሻቸው በውዳሴ ከንቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ሰያቆላጵጵስ እየተመለከትን ነው።

አሁን የኢሳት ነገር ሳይምታታቦት አይቀርም። አልፈርድቦትም። በዚህ መልኩ እናስቀምጠው። ኢሳይያስ ማን ነው? የትና ምንስ ተማረ? ከእኩያዎቹ በተለየ መልኩ ምን የተለየ እውቀትና ችሎታ አለው? ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው። ኢሳይያስ ስለ ራሱ ታላቅነት ካድሬዎቹ አሰማርቶ የሚነዛውን ወሬ በመቀበል ያስተጋቡ እንደሆነ ግን እውነትም ገደል ገብተዋል። ቀደም ብሎ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አሁን ደግሞ የመሳይና ፋሲል ሩጫ ኢሳይያስ አፈወርቂ ትውልድ ሐረጉ ከሰው ያይደለ ከመላዕክት ዘር ነው ብለን እንድናምንና አምልኮና መስዋዕት ለፕሬዝዳንት ኢሳይያስ እንድንገብር ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የማይቀበሉና ፀረ የትግራይ ሕዝብ ፖለቲካ ለሚያራግቡ ዜጎች በሙሉ ፈጣሪያቸው ነውና።

ኢሳይያስ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ማርቀቅ ቀርቶበት ሆነ ሃሳብ ለማዋጣትም አቅሙም እወቀቱም የለውም። ምን ነው ቢሉ እውቀትና ወሬ ለየቅል ናቸውና። ካድሬዎቹ አሰማርቶ በሚለቀው ወሬ “አዋቂ ነኝ” አለና አዋቂ ነው ማለት ነው እንዴ? ቁምነገሩ ኢትዮጵያ በህግ የምትተዳደር አገር ለመሆን መብቃትዋ ነው። ትምክተኝነት መቀበሩ ነው። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በማንነታቸው እኩል ንፁህ አየር ለመተንፈስ ዕድል ማግኘታቸው ነው ድሉ። ኦሮሞ በኦሮምኛ ትግራዋይ በትግርኛ አፋር በአፋርኛ ሀረሬ .. ሁሉም ባህሉን፣ ሃሳቡንና አመለካከቱን በራሱ ቋንቋ ለመግለፅ መብቃቱ ነው ዋና ቁምነገሩ።

ህገ መንግስት የለሌት፣ ላለፉት “24” ዓመታት አንድ ግለሰብ በላይነት የሚመራት አገር መሪ የሆኑት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ትናንት ህልውናቸው ተዘንግቶ የነበሩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዜግነታቸው የምድሪቱን ፍሬ እኩል ተቋዳሾች ያደረገ፣ ብሔር ብሔረሰቦች በማንነታቸው እኩል የህግ ከለላ ያጎናፀፈ፣ በራስ ቋንቋ መናገር እንደ ወንጀል የነበረ ዘመን ታሪክ ያደረገ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ለመተቸት መድፈሩ የግለሰቡ የዕብደት ደረጃ ነው የሚያሳየው። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣

 • እኔ በህይወት እያለሁ ለኤርትራ ሕገ መንግስት አያስፈልጋትም፣
 • ለኤርትራ ህገ መንግስት ካስፈለጋትም ከህገ መንግስት በላይ “እኔ አለሁ!”
 • ህገ መንግስት የሞኞች ነው፣
 • ህገ መንግስት ቀልድ ነው፣
 • ህገ መንግስት በኤርትራ ተግባራዊ ማድረግ ማለት ለምዕራባውያን እጅ መስጠት ነው፣
 • ህገ መንግስት የምዕራባውያን መንግስታት መሳሪያ ነው – ብሎ የሚያምንና የሚመፃደቅ ነውር የማያውቅ ትምክህተኛ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በማስመልከት ለዚህ አጉል ፈላስፋ ጥያቄ ማቅረብ ምን ማለት ነው? ለመሆኑ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በማስመልከት ምን እንዲል ነው የሚጠበቀው? ምንም በማይመለከተው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በማስመልከት ጥያቄ ከማቅረብ ይልቅስ ስለ ኤርትራ “ተንቀሳቃሽ ህገ መንግስት” ምን እንደሚመስል ጥያቄ ማቅረብ አይቀልም ነበር? ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ እውነትም ክፉ ባለንጀራ ነህ።

የኢሳት ዓላማና ድርሻ V የትግራይ ሕዝብ

የኢሳት ዓላማና ድርሻ አንድና አንድ ነው። ይኸውም የትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ የእልቂት ነጋሪት መጎሰም ነው። ይህ ፍጥጥ ያለ ሐቅ ማለትም ኢሳት በትግራይ ሕዝብ ላይ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻና የደም ማፋሰስ አጀንዳ የሚጠራጠር ዜጋ ይኖራል ብዬ አላምንም። ቀደም ሲል “የኢትዮጵያ ፌደራል ስርዓት መሃንዲስወያኔን አሳድጋችሁ ለዚህ ስልጣን አበቃችሁይሄ ሁሉ የእርስዎ የአእምሮ ውጤት እንደሆነ” ወዘተ ኢሳያይስ ለማወደስ በተሰላ ስሌት ይህ ሁሉ መሽኮርመም ዋና ዓላማ የትግራይ ሕዝብ ማሳነስ፣ የትግራይ ሕዝብ ማዋረድ፣ የትግራይ ሕዝብ ማቃለል ለመሆኑ ማን ይስተዋል?

ኢሳት – የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዳይኖር በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ ነው እኮ ዛሬ አይደለም። ኢሳት ከኤርትራ መንግስት የተቀበለው ቀጭን ተልዕኮ በትግራይ ሕዝብ ላይ መዝመት ነው። ከኤርትራ መንግስት ለኢሳት የሚመደበው በጀትም ኢሳት በተለይየ መልኩ በትግራይ ሕዝብ የሞት መለከት እንዲነፋ ነው። ይህ የሚነገር ታሪክ ያለው ሕዝብ (የትግራይ ሕዝብ) አድላዊ፣ ጨቋኝ፣ ፍረደ ገምድልና ሰው በላ የደርግ መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ከትክሻው ላይ አሽቀንጦ የጣለው በመፎክር/በጩኸት/በስድብ/በሰልፍ ብዛት አልነበረም። በስለትም አልነበረም። ታድያ የዚህ ደም ያለው ሕዝብ ቆራጥነት፣ ጀግንነትና በደሙ የፃፈው ታሪክ በቃላት ብዛት ለማቃለል መሞከር ትርፉ ከንቱ ልፋት ነው። በሕዝቡ ማነንት ሆነ በሕዝቡ ፅናት ላይም የሚፈጥረው አንዳች ተፅዕኖ እንደሌለ በዚህ አጋጣሚ ሊሰመርበት ይገባል እላለሁ።

የትግራይ ሕዝብ እንደ የሴት ጡት የተንጠለጠለ ልብ የለውም። የትግራይ ሕዝብ ልብ እንደ ዓለት የፀና ልበ ፅኑ ህዝብ ነው። በዚህ ማንነቱ ደግሞ ተለይቶ ይታወቃል። እየሞተ እዚህ የደረሰ ሕዝብ ለሞት በተዘጋጁ ልጆቹ ደግሞ ማንነቱን እንደጠበቀ ይኖራል።

Dn. Mulugeta Weldegebrial

Email – yetdgnayalehe@gmail.com

February 22, 2015                

Advertisements