በዳያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ “ተቃዋሚ” ተብሎ ለመጠራት ሆነ ለመወደስ፡ መመዘኛው

  • ከምንም በላይ እውነታን መካድና አለመቀበል ነው።
  • ተቃዋሚ መሆን ማለት መራራ/የጥላቻ ሰው መሆን ነው።
  • ተቃዋሚ መሆን ማለት አሳዳጊ የበደለው: ልቅና ተሳዳቢ ሰው መሆንን ይጠይቃል።
  • ተቃዋሚ መሆን ማለት “ብትበርም ባትበርም ጥንቸል ናት!” ብሎ መሞጎት/ሸምጣጭ መሆንን ይጠይቃል።
  • በዳያስፖራው ማህበረሰብ መካከል “አካፋን አካፋ – ማንኪያ ማንኪያ” ብሎ መጥራት ነውር ነው። በአንጻሩ አካፋን ማንኪያ – ማንኪያን አካፋ ማለት ደግሞ እንደ ተቃዋሚ ግዴታህን መወጣት ነው።
  • እንደ ተቃዋሚ ይሁንም አይሁንም የሰማኸውን አሉታዊ ዜና ሁሉ (ከተቻለ ጨማምረህ) ስለ ተባለ ብቻ ሳታጣራ ማስተጋባት/እሪ ማለት የአባልነት ግዴታህን መወጣት ነው።
  • በአንጻሩ ሚዛናዊና ምክንያታዊ ዜጋ መሆን ማለት ጠላትነት ነው።
  • ስለ ኢትዮጵያ በጎ የሆነ ነገር መናገር ሆነ ማሰብ ያስጠረጥራል ያስወግዛልም።
  • እንደ ዜጋ ያልገባህ ነገር መጠየቅ ሆነ አንጻራዊ ሃሳብ በሃሳብ ደረጃ ማንሳት ወያኔነት ነው።
  • ሃሳብህን በነጻነት መግለጽ ፈጽሞ የተከለከለ ነው። [በሳምንት ሰባት ጊዜ እንዳልተመላስኩበትና ጥባጥቤ እንዳልተጫወትኩበት ዛሬ በትየትኛው የዳያስፖራ መካነ ድር ስሜ ሆነ ስራዎቹ ፈልገው አያገኙም።]
  • መሪዎች (የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች) መጠየቅ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። የዋልከው እንደሆነም ዋጋ የሚያስከፍል ኢህአዴግነት ነው።
  • በአጠቃላይ ተቃዋሚ ለመሆን ሆነ “ነው/ነች” ተብሎ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ‘በክብር’ ለመጠራት በጥላቻ፡ በአመጽ፡ በአድማና በክፉ ወሬ መጠመቅን ይጠይቃል።

ይህ ከብዙ በጥቂቱ ነው!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

July 14, 2014

 

Advertisements