የመቼው አንዳርጋቸው ጽጌ ኖት፡ የድሮ ወይስ የዘንድሮ?

የጽሑፉ ይዘት፡

በዕቅድ ሳይሆን ዘወትር የትግሉ ምዕራፍ በድንገት የሚበቅለውና የሚደርቀው ግንቦት 7 የቀድሞ የድርጅቱ (የግንቦት 7) ዋና ጸሐፊ ነበር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ “ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!” ሲል በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ሰኔ 29 ቀን 2006 ዓ/ም ያሰማው መርህ ቃል ሃይለ ቃሉ ጥያቄ ስለ ፈጠረብኝ “አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያውቁ ኖራል?” በሚል ዙሪያ የሚያጠነጥን ንፅፅራዊ ጽሑፍ ይሆናል።

ድሮ አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት፡

  • ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች በማበር የገዛ አገርህና ወገንህ ለማውደምና ለማተረማመስ መሰልፍ ነበር፡
  • የሌለህን አለኝ ያልሆንከውን ነኝ በማለት ለውሸት ራስህን አሳልፈህ መስጠት ነበር፡
  • በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ሁከት ለመዝራት፡ ብሎም የጥፋት አጀንዳ ለማስተዋወቅ እንቅልፍ ማጣት ነበር፡
  • ዘርዋን የምታመክንና የምትበላ ምድራዊት ሲዖል የኤርትራውያን ነባራዊ ሁኔታ መሸምጠጥ ነበር፡
  • በቂምና በበቀል ተሞልተህ ለጥፋት መሰለፍ፡
  • ራስህን አድርባይነትን ማለማመድ፡
  • የቁራ መልዕክተኛ መሆን፡
  • ህሊናህን ጥለህ በቅጥፈት ጎዳና መሰማራት ነበር። እንግዲህ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያደረገው፡ በተጨባጭ ሆኖም ያየነው ይህንኑ ነበር። ለበለጠ መረጃ ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ [http://ethsat.com/video/esat-yesamintu-engida-ato-andargachew-tsege-sep-2013-ethiopia/]

ዘንድሮ አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት፡

  • “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ። እውነቴን ነው የምልህ እኔ እንደምርቃት ነው የተቀበልኩት።” እንዲል አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት ሰላምን አጥብቀህ መሻት ብሎም ከራስ ጋር መታረቅ ነው! (የአደራ መልዕክት ለዳያስፖራ)
  • “አሁን የሚያስቸኩለኝ ነገር የለም። ጥሩ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም በጣም በጣም ደክሞኛል … ሰልችቶኛል።” አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት: እንደ አንስት አንበሳ በእርጋታ ተዘለህ የምትቀመጥበትና የምታርፍበት ስፍራ ለይተህ ማወቅ ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት: በዳያስፖራ የጎጥ፡ የጥላቻና የደም ፖለቲካ መሰላቸች ነው።
  • “እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታነው። ምንም ዓይነት ጥላቻ በውስጤ የለም። ምንም ዓይነት ብስጭት የለኝም። ምንም ዓይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም። በቃ የመጨረሻ እርጋታና እረፍት ውስጥ ነው ያለሁት”  እንግዲያውስ አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት: ቀበሌ ተኮር ከሆነው የኢሳት ፖለቲካ ራስን በማላቀቅ፡ ከጥላቻ፡ ከአመጻና በልዩ ልዩ ምክንያቶች እርስ በርስ ከመከፋፈል ህይወት መውጣትና ራስህን መጽዳት ነው። በመጨረሻ አንዳርጋቸው ጽጌ መሆን ማለት በስሙ የሻማ ማብራት ፕሮግራም/ስነ ስርዓት ማዘጋጀት ማለት ሳይሆን ከራሱ ከአንዳርጋቸው ጽጌ መማር/ትምህርት መውሰድ ነው። ለበለጠ መረጃ [http://www.youtube.com/watch?v=_4cbrQNf6GY]

ጥያቄው፡ እርስዎ “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ !” ሲሉ በእውነቱ ነገር የመቼው አንዳርጋቸው ጽጌ ኖት? የድሮ ወይስ የዘንድሮ?

 

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

July 10, 2014

Advertisements