አይሆንም ማለት ትተሽ ይሆናልን ያዢ!

ዜናው ልብ ብለው አድምጠውልኛል?

“በየመናና በኢትዮጵያ የመረጃና የደህንነት ተቃማት ማዕከላት መካከል የጸረ ሽብር ትግሉ ተቀናጅቶ ለመስራት በተደረሰው ስምምነት ሁለቱም ተቃማት አሸባሪዎችን በመያዝና በመለዋወጥ በጋራ እንደሚሰሩ ይታወቃል። በዚህም መሰረት የዚህ ተፈላጊ ወንጀለኛ ግለሰብ የጉዞ መስመርና የሚጋዝበትን ዕለት አስቀድሞ መረጃ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መረጃው ለአጋር የየመን ብሔራዊ ደህንነት ቢሮ በማሳወቅ በሰንአ በኩል ወደ ኤርትራ ሊገባ ሲል ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ/ም በቁጥጥር በዚያው ዕለት ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥታል” አማርኛ ምሽት 2 ሰዓት ዜና ሐምሌ 01/2006 ዓም ዜናውን ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ http://www.youtube.com/watch?v=_4cbrQNf6GY

የጽሑፉ ይዘት፡

ጽሑፉ በይዘቱ እጅግ አጠር ባለ መልኩ በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ሁለት ዓበይት ጉዳዮች የሚዳስስ ሲሆን

አንደኛ፡ በሁለቱ ሉዓላዊ አገሮች (በኢትዮጵያና የመን) መንግስታት መካከል አሸባሪዎችን በመያዝና በመለዋወጥ በጋራ የተደረገውን ስምምነት በተመለከተ ከወቅታዊ ጉዳዮች በተያያዘ የሚመለከት ሲሆን

ሁለተኛ፡ የአቶ አንዳርጋቸው የጉዞ መስመር በተመለከተ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መረጃውን ያቀበለ ማን ሊሆን እንደሚችል የሚዳስስ ክፍልም በክፍል ሁለት ይቀርባል።

ቅምሻ፡

ደግሞስ ማን ያውቃል? ወዲ አፎም (ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለማለት ነው) ከራሳቸው ጥላ ሳይቀር የሚጣሉና የሚጋጩ የሲዖል ፈላስፋ እንደ መሆናቸው መጠን የሚወስኑት ውሳኔ ስለማይታወቅ አቶ አንዳርጋቸውን “እነሆ፥ ለዛሬ ተርፈሃል። ወደፊት ግን እንዲህ ዓይነት ስህተት እንዳይደገም።” መልዕክት ያዘለ የሞቀ አቀባበል አድርገው ይቀበሏቸው ይሆናል። በግሌ ሰው ክፉ ስለ ሆነ ክፉ ተመኝለት የሚል የህይወት መርህ የለኝም።ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ያለኝ ግኑኝነት እንደሆነም የሃሳብ ልዩነት እንጅ  ሌላ ነገር አይደለም። ለማንኛውም “ጥሩ ውኃ የጥቅምት ነበርሽ ማን በጠጣሽ፡ ጥሩ ምክር የደሃ ነበርሽ ማን በሰማሽ”  ካልሆነ በስተቀር አቶ አንዳርጋቸው ዕድሉን ተጠቅመው ጨርቄ ማቄ ሳይሉ ከኤርትራ ምድር ካልወጡ ወዲ አፎም እንደሆነ ብልጭ ያለው ዕለት ራሱ ገድሎ ሲያበቃ “በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚመራ ሰራዊት በዛሬው ዕለት በ … ግንባር ከወያኔ ጋር ባደረገው የቶክስ ልውውጥ የአውሮፓ ኑሮአቸውን ትተው ወደ በርሃ የወረዱ፣ ታዋቂ፣ “አዋቂ”፣ “የፖለቲካ መምህርና” “አዋጊ” “አርበኛው” አንዳርጋቸው ጽጌ “በመስዋዕነት” አልፏል!”ብሎ በድምጺ ሐፋሽ ኤርትራ የሬድዮ ጣቢያ ጡሩምባ ነፍቶ ለማስነፋት ችግር የለበትም።”

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Oct 3, 2013

የተፈራው ነገር አልቀረም ዛሬ ቀኑ ደረሰና በየመን ሰንአ አየር ማረፊያ/”ጦር ግንባር” የጥይት ድምፅ ሳይሰማ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከነነፍሳቸው በቁጥጥር ስር ውሎዋል። የምስራቹ ያበሰረንም በኤርትራ መንግስት የፋይናንስ ድጎማ የሚቀሳቀስ የፕሮፖጋንዳ ማሰራጫ ማዕከል ኢሳት መሆኑን ጉዳዩን አጠናክሮታል። ግለሰቡን የአርበኝነት ቀምስ አልብሶም ይሄው ከወዲሁ አሰላችቶል። ግንቦት 7 (ዶ/ር ብርሃኑ) እንደሆነም ከደሙ ንጹህ ነው ብሎ ማሰብ ለሌላ የባሰ ስህተትና ኪሳራ ራስህን መማገድ ነው የሚሆነው። ይህን እንደሚከተለው አብራራለሁ።

አይሆንም ማለት ትተሽ ይሆናልን ያዢ!

“በየመናና በኢትዮጵያ የመረጃና የደህንነት ተቃማት ማዕከላት መካከል የጸረ ሽብር ትግሉ ተቀናጅቶ ለመስራት በተደረሰው ስምምነት ሁለቱም ተቃማት አሸባሪዎችን በመያዝና በመለዋወጥ በጋራ እንደሚሰሩ ይታወቃል።” እንዲል [ኢሳት ወይም ሞት! ባይ ዓይነት ግልሰብ ካልሆኑ በስተቀር ስምምነቱ ጎልግሎው ማረጋገጥ ይችላሉ]

በግሌ ስምምነቱን በተመለከተ ሊኖር እንደሚችል ከመገመት ያለፈ “አለ” ወይም “የለም” በማለት ሽንጤን ገትሬ ለመመጎት አይቃጣኝም። በነገራችን ላይ ስምምነቱ በተመለከተ ሁለቱም አገራት እ.አ.አ ጥቅምት 24/1999 መፈራረማቸውን ባደረግኩት መጠነኛ ፍለጋ ለመረዳት ችያለሁ። ይህ በእንዲህ እያለ ግንቦት 7 “የየመንመንግሥት የዓለም ዓቀፍ ህግም ሆነ የየመን የራሷን ህግ በመተላለፍ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል።” የሚለው የትኛው ዓለም አቀፍና የየመን የራሷን ህግ ይሆን የተጣሰው? የሚለው የዜጎች ጥያቄ አፋጣኝ መልስ የሚሻው ነው።

    • ድርጅቱ (ግንቦት 7 ማለቴ ነው) ወዮልሽ የመን! ወዮልሽ ብሪታኒያ! … ሲል በለቀቀው ፍሬቢስ የዛቻና የሽብር ድስኩር የመንን በተመለከተ ያስተላለፋቸው 5ት የጥቃት ነጥቦች መካከል የተመለከትን እንደሆነ አንዳቸውም ህጋዊ መስመር የተከተሉ አይደሉም። ለምን? ሲሉ ራስዎን ጠይቀዋል?
    • ለመሆኑ ግንቦት 7 ይህን መግለጫ ሲወጣ እንዲሁ በድንገት የሆነ ነገር ይመስሎታል? ግንቦት 7 እያሰማው ያለ ቀረርቶና ሽለላ የትም የማያደርስ የሽፍጥ መንገድ መሆኑን እያወቀ በዚህ መልኩ ጉዳዩን ለመያዝ የመረጠ የማን ወንጀል ለመደበቅ/ለማድበስበስ ይሆን? በማለት ራስዎን ለመጠየቅ ካልቻሉ በእውነቱ ነገር ከእርስዎ ላይም ችግር አለ፡፡
    • ግንቦት 7 የመንን መንግስት ቀደም ሲል ከበርካታ ዓመታት በፊት መሆኑ ነው አሸባሪዎችን በመያዝና በመለዋወጥ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ በደረሰውና ባደረገው ስምምነት መሰረት የወሰደው እርምጃ ትክክለኛ፡ ህጋዊ መሰረት ያለውና  ህጋዊ መንግድ የተከተለ መሆኑን እያወቀ ማንን ለማድከማና ለማወናበድ አስልቶ ይሆን ግርግርን የሙጥኝ ያለ?

ቀለል ባለ አማርኛ ግንቦት 7 ህጋዊ መንገድ ተከሎ የየመን መንግስት በህግ ፊት በማስቆም ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ከማድረግ ይልቅ የሰው አገር ባንዴራ ለማቃጠል ጥሪ ያቀረበበት ምክንያት የየመን መንግስት የወሰደው እርምጃ ትክክለኛና ህጋዊ መስመር የተከተለ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ግንቦት 7 በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የየመን መንግስት በሕግ ፊት ለማስቆም/መክሰስ የሚያስችል ህጋዊ መሰረት እንደሌለው ጭምር ያውቃል ማለት  ነው? [ነጥቦቹን በተመለከተ በዝርዝር እመለስበታለሁ] ጎበዝ! እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ግንቦት 7 በማለት ራሱን የሚጠራ አጀበኛ በሌለው ህልውናና እቅም “ህዝባዊ ነኝ” እያለ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ቁማር ሲጫወት የምናገኘው።

ይቀጥላል …

መንቃትንና ጥያቄ መጠየቅ ለራስ/ህ ነው!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

yetdgnayalehe@gmail.com

July 8, 2014

Advertisements