አንድዬን ያሳረፈ ማን ይሆን፡ ህ.ግ.ደ.ፍ ወይስ ግንቦት 7?

ካለፈው የቀጠለ … አይሆንም ማለት ትተሽ ይሆናልን ያዢ! (ክፍልሁለት)

አሳልፈህ መሰጠት ሆነ ተላልፈህ መሰጠት ዛሬ በእኛ የተጀመረ አዲስ ነገር አይደለም። ያስቆረቱ ይሁዳን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብዬ አልገምትም። የስሙ ገናናነት ያክል ግን ይሁዳ ብሎ ለልጁ ስም ያወጣለት አባት/ቤተ ሰብ አላውቅም። ለምን? ምክንያቱ ግልጽ ነው። ይሁዳ ጌታውን አሳልፎ የሰጠ፡ ባለ አመል፡ በአራድኛ አነጋገር የ እጅ ባለ ሞያ ማለትም ሌባ፡ ከሃዲ፡ ወረበላ … ሰው ነው ብሎ ስለሚታመን ነው።  

እውነት ነው ኢየሱስና ይሁዳ በጠላትነት ዓይን የሚተያዩ ባላንጣዎች አልነበሩም። በሁለቱም መካከል የነበረ ግኑኘት በመምህርና በደቀ መዛሙር ከሚታየው ግኑኝነት ያለፈ የጠለቀ በወንድማማችነት ሰማያዊ ፍቅር የተሳሰረ ግኑኝነት የነበራቸው ሲሆን ይሁዳ ገንዘብ ከመውደዱ የተነሳ ግን ሰይጣን ገብቶበት የሚፈጥረው ነገር ላይኖር ታላቁ መምህሩና ወንድሙ የሆነው ኢየሱስ በመሳም አሳልፎ ሰጥተዋል።

    • image002 image004

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተላልፎ መሰጠት በተያያዘ ግራ የተጋባ ዜጋ ነገሩ እንዴት ሊሆን ይችላል/ቻለ ሲል  ትንግርት የሆነበት ክስተት ከምንጩ ለመረዳትና ለማወቅ በቆመበትና በተቀመተበት ወጥቶ በሚወርድበት ሰዓት ኢቲቪ ከግማሽ በላይ መንገድ ተጎዞ በጣት በሚቆጠሩ ቃላቶች የዜጎች ሸክም ሲያቀል እንዲህ ይላል።

“… በዚህም መሰረት የዚህ ተፈላጊ ወንጀለኛ ግለሰብ የጉዞ መስመርና የሚጋዝበትን ዕለት አስቀድሞ መረጃ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሐራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መረጃው ለአጋር የየመን ብሔራዊ ደህንነት ቢሮ በማሳወቅ በሰንአ በኩል ወደ ኤርትራ ሊገባ ሲል ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ/ም በቁጥጥር በዚያው ዕለት ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥታል፡፡” አማርኛምሽት 2 ሰዓት ዜና ሐምሌ 01/2006 ዓም ዜናውን ለማዳመ ጥሊንኩን ይጫኑ [http://www.youtube.com/watch?v=_4cbrQNf6GY]

ኢቲቪ “የዚህ ተፈላጊ ወንጀለኛ ግለሰብ የጉዞ መስመርና የሚጋዝበትን ዕለት አስቀድሞ መረጃ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሐራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት” እንዲል የየመን መንግስት የወሰደውን ግልጽና ቀጥተኛ እርምጃ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነትና በተፈራረመው ሰንድ መሰረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሐራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መረጃው ያቀበለ አካል ምንም እንካ ኢቲቪ ባይነግረንም –

በነገራችን ላይ ዜናው “አስቀድሞ መረጃ የደረሰው” ይላል እንጅ “የኢትዮጵያ ብሐራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደርገው እልህ አስጨራችና ከፍተኛ ክትትል አይልም” ታድያ ይህ ማለት የአቶ አንዳርጋቸው በተመለከተ ዝርዝር ቀዳሚ መረጃ የሰጠ አካል አንድም ሁለቱ ማለትም ግንቦት 7 ወይም ዶ/ር ብርሃኑ ራሱ ከኤርትራ መንግስት በመመሳጠር በቅንጅት የሰሩት ስራ ነው፤ አንድም ከሁለቱ ያለፈ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የጉዞ የጊዜ ሰሌዳ በቅርበት የሚያውቅ ሌላ አካል ሊኖር አይችልምና ከሁለቱ አንዳቸው በተናጠል ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው በሰጡት መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ብሐራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መረጃው ለየመን አቻውን በማስተላለፍ ባደረጉት የመረጃ መለዋወጥ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል ችለዋል። አይመስሎትም? ከዚህ ያለፈ በእርግጠኝነት ለመናገር የሚቻል ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ብሐራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መረጃው ነፋስ እንዳላቀበለው ብቻ ይሆናል። ትላልቆቹ የስለላ ድርጅቶች የሚጠራ ሰው ካለ ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው የሚሆነው።

ጠርጥር በገንፎ ውስጥ አይታጣም ስንጥር!

ምዕራባውያን ከደማቸው ይሁን ከስልጣኔአቸው ጋር የተያያዘ ለመሆኑ በጥናት ባልደርስበትም ወንጀል በራሳቸው፡ በቤተሰቦቻቸው፡ በአከባቢያቸው … ወዘተ ሲፈጸም ሌላው ይቅር ባል ሚስትን ሚስት ባልን፤ ልጆች ወላጆች ወላጆች ልጆቻቸው ሳይቀር የመጠርጠርና ጥያቄ ውስጥ የማስገባት ባህል አልቸው። ሚስቴናትና፤ ባሌ/ልጄ ነውና ወላጆቼ ናቸው ይህን ወንጀል አትፈጽመው፡ አይፈጽመውም፡ አይውሉትም ብሎ ነገር የለም፡፡ አልፈጠረባቸውም። የሦስተኛ ዓለም ዜጎች ስንባል ደግሞ ተፈጥሮአችን ወዲህ ነው። የቅርባችን ሰው መጠርጠር ጨርሶ አልፈጠረብንም።

ግንቦት 7 አቶ አንዳርጋቸው አሳልፎ በመስጠት የሚያገኘው የላቀ ጥቅም ካለው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ሳልፎ የማይሰጥበት ምክንያት ምንድ ነው? ግንቦት 7 ማለት እኮ “ለጽድቅ” የተቃቃመ ድርጅት አይደለም። ግንቦት 7 ደም በማፋሰስ፡ በሁከትና በሽብር ድርጊቶች መንግስታዊ በትረ ስልጣን ለመጨበጥ የተነሳ የወረበላ ቡድን ነው። እንግዲያውስ “ሁለገብ” ሲባል ይህን ጭምር (መሪህን አሳልፈህ መስጠት) እንደሚያጠቃልል ልንገነዘብ ይገባል። ግንቦት 7 አባላቶቹን አሳልፎ መስጠት ዛሬ አይደለም የጀመረው። ሲሰራበት የመጣና ያለ የድርጅቱ ስትራቴጂ ነው።

አውራ ቂሱ ዶ/ር ብርሃኑ “መንፈስ ነው፡ ነፋስ ነው!” እየተባለ ብዙ የተነገረት ቅንጅት ሳይቀር እንደ ቅርጫት ስጋ የበጣጠሰና ግለሰቡ የራሱ ጥቅምና ክብር የማያስከብርና የማይጠብቅ ሆኖ የተሰማው ሁሉ አንድ የነበረውን በመበታተን ረገድ ከፍተኛ ልምድ ያዳበረ ባለሞያ ለመሆኑ የቀድሞ ወዳጆቹና ባለደረቦቹ በቃልም በጽሑፍም የሰጥዋቸው በርካታ ምስክርነት አንብበናል። ታድያ ድርጅት የሚያክል በታትኖ ሲያበቃ ዛሬም ሳያፍር እኔ “አውቅላሃለሁ!” የሚለው ግለሰብ አንድ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ ከመስጠት ምን ይመልሰዋል? ምንም።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

July 9, 2014

Advertisements