መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ “NSA” የዒላማ መዝገብ ስማቸው ተገኘ

የ“ebay” አየር ባየር ገበያ መስራች ፔሪ ኦሚድያር ዕርዳታና እገዛ የካቲት 2014 የተቋቋመ “ዘ ኢንተርሰፕት” በየሳምንቱ ከአንድ ሚልዮን ኮፒ በላይ የሚቸበቸበው በጀርመን ሃምበርግ የሚታተመው ስፔግል ሳምታዊ መጋዚን ዋቢ አድርጎ “NSA Put Merkel on List of 122 Targeted Leaders” በሚል ርዕስ እ.አ.አ መጋቢት 29, 2014 የአሜሪካ መንግሥት በቅርብ ርቀት ውሎ ማደራቸውን የሚከታተላቸና እያንዳንዷ እንቅስቃሳቸው የሚሰልላቸው የአገር መሪዎች ስም ዝርዝር “የኤን.ኤስ.ኤ” የስለላ መዝገብ ለንባብ አብቅቷል።

#PM Meles@Salsay Woyane

ይህ “Target Knowledge Database (TKB)” ተብሎ የሚታወቀው አዲስ ጥቁር መዝገብ አሜሪካ በቅርብ ርቀት የምትሰልላቸውና የምትከታተላቸው 122 የአገር መሪዎች ስም ዝርዝር የያዘ ሲሆን በዚህ ጥብቅና ሚስጢራዊ ጥቁር መዝገብ የምዕራባውያን የባህልና የኢኮኖሚ ወረራ በግንባር ቀደምትነት በመቃወም የሚታወቁ፤ ሌሎች የአፍሪካ አገር በማስተባበር ረገድም የአፍሪካ ህብረት ነፍስ የዘሩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይገኙበታል። “ዘ ኢንተርሰፕት” የአሥራ አንድ ሰዎች ስም ዝርዝር ብቻ ይዞ የወጣ ሲሆን የተቀሩት ሊንኩን ተጭነው መመልከት ይችላሉ። [http://cryptome.org/2014/03/nsa-nymrod-spy-cos.pdf

በዚህ አጋጣሚ ከካንሰር ጋር በተገናኘ የአገር መሪዎች ሞት በጥቂቱም ቢሆን ጥርጣሬ ብጤ የሚያሳድር ሆኖ ስላገኘሁት እጅግ በጨረፍታው አንዳንድ ነጥቦች አንስቼ ለመዳሰስ እፈልጋለሁ። የሰው ልጅ በሥጋ የሚያስተናግዳቸው የበሽታ ዓይነቶች ሁሉ ተፈጥሮአዊ ነው ማለት አይቻልም። ተፈጥሮው ራሱ ለበሽታ የተጋለጠ ከመሆኑ የተያያዘ ሰው ሰራሽ ለሆኑ ጠንቆችም የተጋለጠ ነው። ሰው ሰራሽ ወይም የላባራቶሪ ውጤት በሽታዎች መዘርዘር የጽሑፉ ዓላማ ባይሆንም ሰው በረቀቀ መልኩ የሰዎች ዓላማ ሊሆን እንደሚችል ግን በማስረጃ አስደግፌ አንድ ምሳሌ ላቅርብ። 

ምጡቅ አስተሳሰብ ያላቸው፣ የለውጥ ሰዎች፣ በራስ መተማመን የማይታሙ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ከምዕራቡ ዓለም አገራት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎትና ምኞት በተያያዘ ግልጽ አቋም ያላቸው የአገር መሪዎች በካንሰር በሽታ ሲያልቁና ሲሰቃዩ እያየን ነገሩ ከፈጣሪ ነው ብሎ ማመን ምክንያታዊ ነው ብዬ አላምንም። እ.አ.አ 1975 ዓ.ም የአሜሪካ ሴኔት ሲ.አይ.ኤ የሚፈጽማቸው የግድያ ድርጊቶች በተመለከተ በዋለው የማጣራት ጉባኤ ሲ.አይ.ኤ የአገር መሪዎች ያነጣጠረ ካርሰርና የልብ ድካም በሽታ የሚያስከትል እጅግ የረቀቀ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ መሳሪያ እንደሚጠቀም ለማረጋገጥ ችሏል። [http://www.infowars.com/cia-developed-a-sudden-cancer-gun-back-in-the-1970s/]

ካንሰር እና ለምዕራባውያን ጥቅም የማይንበረከኩ የአገር መሪዎች እልቂት፡

ወደ ስልጣን ከመጡ ከ1959 ጀምሮ ለ638 ጊዜያት ልዩ ልዩ ሳይንሳዊ የግድያ ሙከራዎች የተደረገባቸው፤ “If surviving assassination attempts were an Olympic event, I would win the gold medal.” ሲሉም በምዕራባውያን መንግሥታት ላይ በሟሸፍ የሚታወቁ፤ ከድህረ ሶቬት ሕብረት መፈረካከስም ቢሆን ለምዕራባውያን አጀንዳ ያልተንበረከኩ የቀድሞ የኩባ ፕሬዝዳንት የኮሚኒስት አብዮታዊ ፊደል ካስትሮ የሆድ ካንሰር ተጠቂ ሲሆኑ ሌሎች ለምዕራባውያን አጀንዳ ያልተንበረከኩ በርካታ የላቲን አሜሪካ የአገር መሪዎች የካንሰር በሽታ ሰለባዎች ናቸው።

  • በተባበሩት መንግሥታት ዓመታዊ ጉባኤ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጅሮጅ ቡሽ “The Davil” ሲል ባደርገው ንግግር የሚታወቀው፤ በዜጎቹ አንደበት “የድሆች አባት!” ተብሎ የሚሞገሰው የ58 ዓመት መዋቹ የቬኑዝዋላው ቻቬዝ ጨምሮ (ያልታወቀ ካንሰር)፤ የቀድሞ የአርጄንቲና ፕሬዝዳንት ኔስቶር (‘ኮሎን’ ካንሰር)፤ የብራዚል ፕሬዝዳንት ዲልማ ሮስፍ (‘ሊምፎማ’ ካንሰር)፤ ተተኪያቸው ሉዝ ልናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ (‘ትሮት ካንሰር)፤  ከ2008 – 2012 የፓራጓይ ፕሬዝዳንት ነበር ፈርናንዶ ሉጎ (‘ሊምፎማ’ ካንሰር)፤ ከ2006 ጀምሮ የቦሊቭያ ፕሬዝዳንት ኢቮ ሞራሌስ (‘ናሳል’ ካንሰር) በካንሰር በሽታ ከዚህ ዓለም በሞት የተሰናበቱና እየተሰቃዩ የሚገኙ ተጠቃሾች ናቸው። 

የቀድሞ የኢፌዲሪ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ገዳይስ ማን ይሆን? ለሚለው ጥያቄ አቦይ ስብሃት የወደዱ ዕለት ይነግሩን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። በተረፈ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በተያያዘ ከፍታ ላይ የወጡ አቶ አበበ ገላው ስለ ተባሉ ግለሰብ ሥነ መልኮታዊ ዓይን ከፋች ምስጢር ላካፍላችሁ። 

አቶ አበበ ገላው Vs. የአስቆረቱ ይሁዳ

የአስቆረቱ ይሁዳ ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ ግንዛቤ ይኖሮት ዘንድ መጠነኛ ማብራሪያ ልስጦት። ይሁዳ የስሙ ትርጓሜ ምሥጋና ማለት ነው። ይሁን እንጅ ሰው የማያውቀው ልብና ኩላሊትን የሚመረምር ጌታ የገለጠው ድብቅ ተግባሩና ማንነቱ ግን ፍጹም የተለየና እውነትም ነፈሰ-ገዳይ ዓይነት ሰው ነበር። ይሁዳ ቀን እስኪለይ ድረስ እኩል ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር ይጓዝ የነበረና ጉባኤው ትልቅ ሃላፊነት የጣለበት ሰውም ነበር። ይሁዳ የሂሳብ ሰው/ሊቅ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ የሥነ መለኮት መምህራን። ለዚህ አባባላቸው እንደ አንድ ጭብጥ አድርገው የሚያቀርቡት በጉባኤው (በክርስቶስ ኢየሱስ አገልግሎት) የሂሳብ ሹም ሆኖ መሾሙ ነው ያላሉ። እውነት ነው ይሁዳ ማለት የሐዋርያት ገንዘብ ያዥ ነበር። 

ይሁዳ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ወጪና ገቢ በማምታት የመስረቅ፣ የመመንተፍ፣ የማጭበርበርና የማደናገር አመል የነበረው ዓይነት ሰው ነበር። ይሁዳ ልቡ በሚያውቀው በተደጋጋሚ ጌታ ያስጠነቀቀው ሲሆን አንድ ጊዜ ገንዘብ ስለለመደ ግን የጌታን ግሳጼ ልብ ባለማለቱ ጭራሽ ሰይጣን ገብቶበት የቀረበት ሂሳብ ለማካካስ ጌታውን ለመሸጥ የበቃም ነው (ማቴ. 26፥20-25, ዮሐ. 13፥2, 21-30 ይመልከቱ)። 

ይሁዳ ከሌሎች ይልቅ እሱ ብቻ ስለ ድሆች እንደሚያስብና እንደሚቆረቆር “እንዴ! ሰዎች የሚላስ የሚቀስም አጥተው በርሃብ አለንጋ ሲገረፉ ይቺ ደግሞ ይህን 300 ዲናር የሚያወጣ የከበረ ሽቶ ሰብራ እግሩ ላይ ትደፈዋለች እንዴ?” ብሎ/እያለ ሲሞግት እንግዲህ እርስዎ የዋኅ ካለሆኑ በስተቀር “እውነት ነው! ሽቶው ተሽጦ ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው አረጋውያን፣ ያለ አሳዳጊ ለሚንከራተቱ ህጻናት እርዳታ መዋል ይገባው ነበር” በማለት ድምጽዎትን ለይሁዳ ይሰጡ ይሆን? እንግዲህ መጽሐፍ ይሁዳ “ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።” (ዮሐ. 12፥6) ሲል ምን ይሰማዎታል?

  • እንግዲያውስ የሚያሳድደው፣ የሚፈልገው፣ የሚከታተለው፣ ዞር ብሎ የሚያየውና የሚስታውሰው ሰው ሳይኖር እንዲሁ እምሮው በተፈጠረው ቀውስ ብቻ እንደ ቃኤል “ያገኘኝ ሁሉ ይገድለኛ!” ሲል ራሱን እያሰቃየ፣ እየገረፈ፣ እያሳበደና እያሳደደ የሚገኘው አቶ አበባ ገላው እንደ ይሁዳ ሲያንቀለቅለው ስምና ዝና ፈላጋ በማኸል የገባ ጥላቻና ጭፍን አስተሳሰብ የነገሰበት ተራ ግለሰብ እንጅ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ሞት ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ የለውም።በሃሳብ ደረጃ መነሳቱ ራሱ ዝቅጠት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃየኢየሱስ መሰቀል ከይሁዳ ተግባር ጋር ምንም የሚያገናኝ ሥነ መለኮታዊ ይዘት የለውም። ይሁዳ እዚህ ስፍራ ላይ ገባ አልገባ (ይሁዳ ካደ አልካደ) ኢየሱስ ከስቅላት አያመልጥም። ኢየሱስ ሥጋ ለብሶ ከሴት የተወለደበት ዋና ዓላማ ስለ የሰው ልጆች ኃጢአት ለመሰቀል ነው። እዚህ ላይ የይሁዳ መኖር አለመኖር የሚያመጣው ለውጥ የለም። መስቀል ለኢየሱስ የማይቀርለት ሰማያዊ አጀንዳ ነው። በአጭሩ ይሁዳ ማለት ገንዘብ ተከትሎ በራሱ ጊዜ የተጠበሰ ሰው ነበር። 

ይሁዳ ለገንዘብ የነበረው ፍቅር አንቀልቅሎ እዚህ መኸል ውስጥ ጨመረው እንጅ እንደሌሎች ወንድሞቹ እጁና እግሩ ሰብስቦ ቢቀመጥ ኖሮም ኢየሱስ እንደሆነ መሰቀሉ አይቀርለትም ነበር። ምስኪኑ ሰው የአቶ አበበ ጉዳይም በተመሳሳይ በይሁዳ ቅሌትና ውድቀት ይመሰላል። የአቶ አበበ የማሰብ ችሎታ ለማየት ዕድሉ የገጠመኝ ሰውዬው በሞቅታው ቀልጠው ጭራሽ ቤተ ክርስትያን መድረክ ላይ ቆመው “ቅዱስ ገብርኤል በህልም ተገልጦ የሰጠኝ አጀንዳ ነበር ሲሉ” ጉዳያቸው መለኮታዊ ይዘትና ቅርጽ ለማስያዝ የደፈሩ ዕለት ነበር። በእርግጥ አቶ አበበ በተሳሳተ ስሌት ስሜን እገነባለሁ ብሎው ወጥተው ኑሮአቸውንና ሰላማቸውን ያደፈረሱ ምስኪን ሰው ናቸው። 

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በተመለከተ፡

በእውነቱ ነገር ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ስማቸው “በሊቃውንት” መዝገብ አለመገኘቱ ስገልጽ በአክብሮት ነው። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በተመለከተ ስማቸው በመዝገብ ተጽፎ አልተገኘም። ይሄ ለፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ትልቅ ኪሳራ ሲሆን ለደጋፊዎቻቸውም ትልቅ ውርደት ነው። ስማቸው በመዝገብ ተጽፎ ባለመገኘቱም ፕሬዝዳንቱ ምን ያህል ሊያስቆጣቸውና ሊያበሳጫቸው እንደሚችል መገመቱ አያዳግትም። 

ቀደም ሲል ይፋ በሆነው የዊክሊክስ ፕሮፋይሎች ዲፕሎማቱ ኢሳይያስ አፈወርቂን ከራሱ ጥላ ጋር የሚጣላ “ፓራኖይድ” ነው ሲሉ እንደገለጹት ኢሳይያስ አሜሪካ ከቁብ የማትቆጥራቸው፤ ቁጥር ውስጥ የማይገቡ ተራ የአገር አስተዳዳሪ ዓይነት ሰው መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በነጋ በጥባ ቁጥር “ጠላቴ አሜሪካ ነው! ሲ.አይ.ኤ ነው!” እያለ የሚያቦነው አቧራ፤ ሳይፈለግ በብርቱ እንደሚፈለግ የሚደሰኩረው ዲስኩር፤ የሚጮሆው ጩኸትና የሚሰጣችው መንግሥታዊ መግለጫዎች ብዛት ርሃብና ችጋር የጠለፈው የኤርትራ ህዝብ ለማደናገርና ለማምታታት ብሎም ኢሳይያስ ራሱ ለማጽናናት የሚፈጥረው ፕሮፖጋንዳ ለመሆኑ ይህ ግሩም ማስረጃ ነው። ጎበዝ! ሰው ከነገርና ከጸብ ይርቃል እንጅ እንዴት ነው ሰው ጸብ ፍለጋ የሰው ደጅ የሚጸና? 

  • ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በባድመ ላይ የደረሰበት ወታደራዊና ፖለቲካ ኪሳራ ተከትሎ “ጠላቴ አሜሪካ ነው! ሲ.አይ.ኤ ነው!” እያለ የሚያቦነው አቧራ ሳስበው አንድ ድንቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያስታውሰኛል። ይኸውም፡ አቤሜለክ የተባለ ሰባ ወንዱሞቹን ገድሎ የነገሰ የጌድዮን ልጅ ሲሆን ይህ ሰው የሞተው የቴቤስ ግንብ ለማጋየት በተጠጋ ጊዜ አንዲት ሴት ከላይ ሆና በወረወረችው የወፍጮ መጅ አናቱን ስታፈርሰው በሞት አፋፍይ ላይ ሆኖ ጋሻ ዣግሬውን  በመጥራት “እኔን ሴት ገደለችው እንዳይሉ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” ሲል ጕልማሳው ወግቶ የገደለው አቤሜለክ ያስታውሰኛል። ለካ የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ከአሜሪካ ጋር መንጠራራት “በወያኔ እጅ መሞቴ አይቀር፤ ወያኔ አጠፋው እንዳይባል ይልቁንስ አሜሪካ ገደለችው” ተብሎ ይነገርለት ዘንድ ሆኖ ኖሯል። ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮኸለች!

ጥብቅ ማሳሰቢያ፡ ጽሑፉ በይዘቱ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞት ተጠያቂ ያደርገው/የሚያደርገው አካል የለውም።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com 

April 1, 2014

Advertisements