ሲሳይ አጌና፡ እውን ሲሳይ ወይስ መርገም?

ሰሙኑ አንድ በጡረታ የተገለሉ የግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለ ስልጣን ነበር፥ “አንድ ሶስተኛ የኢትዮጵያ መሬት የግብጽ ነው …” ግብጽ ለኢትዮጵያ መንግሥት የምታቀርባቸው ቀጭኝ አማራጮች ተቀብላ ተግባራዊ የማታደርግ ከሆነች ደግሞ “ዓይናችች እያየን አንሞትም እዛው ግድቡ ሂደን ነው የምንሞተው። ስለሆነም እዛው ድረስ ሄደን ልናጋያቸው ይገባል።” ሲሉ የግብጽ ባለ ስልጣናት በአገራችን በኢትዮጵያ ላይ የደገሱትን የጥፋት ድግስ አስገርሞኝ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይንና ጆሮ” ነኝ የሚለው ቀልደኛ የሻዕቢያ ልሳን ኢሳት ምን ይል ይሆን ብዬ? ጎራ ብዬ ነበር። 

እውነት ለመናገር ኢሳት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ጥፋት እንጅ መልካም ሃሳብ እንደሌለው ስቼው አይደለም። ኢሳት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ክብርና ሉዓላዊነት ቆሞ በጣላቶቹ ፊት ይሞግታል፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ተሰልፎ ጠላቶችዋን ይወጋል የሚል እምነት በውኔ ቀርቶ በህልሜም አስቤው አላውቅም። ታድያ ይህን የመሰለ ጥብስ ሰበር ዜና ትቶ ኢሳት የተያያዘው አገር የማፈራረስና ዜጎች እርስ በርስ ደም የመቃባት አጀንዳ ነውና በተለይ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ የሚነዛው የጦርነትና የጥላቻ ዘመቻ እስኪተነፍስ ድረስ ስራዬ ብሎ እንደ ተያያዘው ነው ያገኘሁት። ያም ሆነ ይህ የኢሳት የዕለት ዕለት ስራዎች ለትግራይ ሕዝብ ግልጽ መልዕክት ለመሆኑ ማናችንም አንስተውም።

በቀጥታ ወደ ፍሬ ነግሬ ከመዝለቄ በፊት ግን በጽሑፉ ዓላማና ይዘት እንዲሁም የጽሑፉ አዘጋጅ ይህን ጽሑፍ ያዘጋጅ ዘንድ ግድ ያለበት ምክንያት ሰፋ ባለ መልኩ ለማስረዳት እሞክራለሁ።

የጽሑፉ ዓላማ፥

አንደኛ፡ በማንኛው ዓይነት መልኩ በትግራይ ህዝብ በተለየ መልኩ ለሚሰዘነዘረው ማንኛውም ዓይነት ጥቃት የትግራይ ሕዝብ ትናንት የማንም እርዳታ እንዳልተቀበለና እንዳልጠየቀ ሁሉ ዛሬም ቢሆን ይህ ሕዝብ ለክብሩና ለሉዓላዊነቱ የማንም ይሁንታ የማይጠብቅ ሕዝብ እንደ ሆነ ቀጥተኛ መልዕክት ለማስተላለፍ፤  
ሁለተኛ፡ ማናችንም ብንሆን ልዩነቶቻችንን አቻችለን ተከባብረንና ተጠባብቀን መኖር ሲገባን ሕዝብ እንደ ሕዝብ አለ ኃጢአቱ በተገኘው አጋጣሚ የሚዘለፍበትና የሚዋረድበት ነገር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቆም ይገባል። በተለይ ኢሳት ስራዬ ብሎ የተያያዘው ጸረ ሕዝብ አቋም ሊያስከትልበት የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ ተገንዝቦ ለአፉ ጠባቂ የከንፈሮቹም መዝጊያ ይጠብቅና ያኖር ዘንድ ተጻፈ።

ማብራሪያ፥

በጽሑፌ መንደርደሪያ ሦስተኛ አንቀጽ ላይ እንዳስታወቅኹት ወደ ዕለቱ መልዕክቴ ዝርዝር ሐተታ ከማለፌ በፊት ጽሑፉ በባህሪው ሊኖረው ስለሚችል ይዘትና መልክ በአንዳድ አንባቢዎች ዘንድ ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ብዥታዎች ለማጥራት ያክል አንዳንድ ነጥቦች አንስቼ ማብራሪያ ለመስጠት እወዳለሁ።

አንድ ሰው ከሃያና ከሣላሳ ዓመታት በፊት የነበረበት ምንነት ተነስተህ “እገሌ ማለት እኮ ትናንት እንዲህና እንዲያ የነበረ ሰው ነው” በማለት የዛሬውን ሰው በትናንት መገለጫው መመዘን የተሳሳተ ነው። ትክክል ነው ብዬም አላምንም። ትናንት ሌባ የነበረ ሰው ዛሬ ሌባ ላይሆን ይችላል። ትናንት ነፍሰ ገዳይ የነበረ ሰው ዛሬ ላይሆን ይችላል። ትናንት ስመ ጥር ዘራፊዎች፣ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች፣ ወረለበሎችና አሉባልተኞች የነበሩ ሰዎች ከቀድሞ የስህተት መንገዳቸው ተመልሰው የሕዝብ አጋልጋዮች የሚሆኑንበት አጋጣሚ ሲፊ ነው። በዚህ ዙሪያ በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ የአገራችን ሰዎች ሞልቶዋል። 

በአንጻሩ ደግሞ ዛሬ በጽድቁ፣ በመልካምነቱ፣ በፍትሐዊነቱና በአገልጋይነቱ የምናውቀው ሰው ነገ ጭራሽ አገር አጥፊና ወመኔ ዜጋ ሆኖ ልናገኘው እንችላለን። ዛሬ በደግነቱ የምንገልጸውና የምናውቀው ሰው ነገ በአንጻሩ መራራ ዓይነት ሰው ሆኖ ልናገኘው እንችላለን። ሰው ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከቀኝ ወደ ግራ ከግራም ወደ ቀኝ የሚቀየስና የሚገለባበጥ ድንቅ ፍጥረት ነው። 

ሌላው ሰው የሚያዋጣውን የሚያውቅ፣ ከስህተቱ ለመማር ከወደደም ከስህተቱ ለመታረም የሚያስችል አቅም ያለው፣ ክፉንና ደጉን ለይቶ የሚያውቅ ብቸኛ ፍጥረት ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጥቅም እስካስገኘለት ድረስ ክፋትንና አመጻን ለጥቅም ሲል ብቻ አጥብቆ የሚይዝ ወንድሙን አጋድሞ በወንድሙ ደም ቤቱን ከመገንባት የማይመለስ ጨካኝ ፍጥረት ሆኖም እናገኘዋለን። ሰው ማለት ይህ ነውና።

የሰው ልጅ ከዕለት ወደ ዕለት የመለወጥና የማደግ ብስለትን የመጨመር ባህሪ እንዳለው ሁሉ የሀገሬ ሰው “በምኒልክ የደነቆረ ምኒልክ ይሙት እያለ ይኖራል” እንዲል ዓለም የቱንም ያህል ብትለወጥ በተለወጠ አገር ተቀምጦም በአስተሳሰቡ እንደ ኩሬ ውሃ ንቅንቅ የማይል ቁሞ የቀረ/የሚቀር ተንቀሳቃሽ ቅርስ ዜጋ በቁጥር ቢሰላ ቀላል አይደለም። ዛሬ ላይ ሆኖ “በጃንሆይ ዘመን ዶሮ በአስራ አምስት ሳንቲም ትሸጥ ነበር!” እያለ በትዝታ የሚኖር ማህበረሰብ ቀላል አይደለም። በፖለቲካ አስተሳሰብ ረገድ እንደሆነም ከሃያ ዓመታት በኋላም 2006 ዓም ላይ ሆነው “ይቅደምና ይውደም!” ከማለት በሽታ ያልተላቀቁ የደርግ ቅሪቶች ቁጥር በቀላሉ የሚናቅ አይደለም። 

“የደርግ ቅሪቶች” የሚል አገላለጽ በደርግ ዘመነ መንግሥት የሥርዓቱ ተጠቃሚ የነበረ ዜጋ ሁሉ ተጠያቂ የሚያደግ አይደለም። በደርግ ዘመነ መንግሥት ተገዶም ሆነ ወዶ በሰራው ስራ ተጸጽቶ ዛሬ በንስሃ በቅዱስ ቁርባንም ተወስኖ ሰላማዊ ህይወት የሚመራ አዲስ ሰው አይመለከትም። ስህተቱን አምኖ የአቅጣጫ ለውጥ ያደረገ ሰው በትንናት ሃጢአቱ አይወቀስም። ይህ ሰው አዲስ ሰው ነው። 

ታድያ ዛሬም ብቱቱውን እንደለበሰ ከሃያ ዓመታት በፊት የትግራይ ሕዝብ በከፈለው የህይወት መስዋዕትነት የተቀበረ ትምክህተኛ የደርግ አስተሳሰብ የሚያስተጋባና ማቀንቀኑን ያልተወ ግለሰብ ሆነ ድርጅት ግን በሚገባው ቋንቋ መነጋገራችን ይቀጥላል። ስለሆነም ይህ በቀድሞ የደርግ ወታደራዊ መንግሥት የቅስቀሳና የፕሮፖጋንዳ ክፍል ሰልጣኝ ሻለቃ ሲሳይ አጌና ስራዎች ላይ ያነጣጠረ ጽሑፍ ሲሳይ የሚያስጽፍ የረባ ቁም ነገር ኖሮት ሳይሆን ለጥፋት የተሰለፈ ኃይል እንደ መሆኑ መጠን ሰፊውን ሕዝብ ለመታደግ በዚሁ መልክ ተዘጋጅተዋል።

ሐተታ፥

ከነተረቱ “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል” እንደሚባል የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ መቆም የሚያጥወለውላቸው የሻዕቢያ መሪዎች ጠፍጥፈው የሰሯቸው የግንቦት 7 ሊሒቃን እንደ ተለመደው ዳያስፖራው ማህብረሰብ የሚያወናውዱበት ድርሰት ሲያልቅባቸው ኢሳት በመሃከላችን በህይወት የሌሉ ሰዎች ከመቃብር እየቀሰቀሰ መዶስኮር ተያይዞታል። ለነገሩ ቀድሞውኑስ ቢሆን መነኩሴ ሥራ ሲኖረው አይደል። ለማንኛውም ወደ ተነሳሁበት ርዕስ ላምራ።

በደርግ ዘመነ መንግሥት የፕሮፖጋንዳና የቅስቀሳ ሰልጣኝ ሻምበል ሲሳይ አጌና ያለ አንዳች ጭብጥ የትግራይ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ እ.አ.አ መጋቢት 05 2014 በፓትርያሪክ ጳውሎስ ባላቀቀው ምላስ እንዲህ ይላሉ “ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረው ችግር ሃያ ሁለት ዓመታት መፍትሔ ሳያገኝ ሃያ ሶስተኛ ዓመት ጉዞውን ጀምሯል።” ይላል [http://ethsat.com/video/esat-news-analysis-march-05-2014/] እዚህ ላይ አራት ነጥቦች አነሳ ዘንድ ወደድኩ፥

  • አንደኛ፡ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ያልነበረ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረው ችግር ምንድ ነው? 
  • ሁለተኛ፡ ለመሆኑ አባ መርቃሪዮስ ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ ምንም ዓይነት ህጋዊ አሰራር ባልተከተለ አካሄድ በደርግ መንግሥት ይሁንታ የተሾሙ ግለሰብ መሆናቸው የኢትዮጵያ ህዝብ አያውቅምን? 
  • ሦስተኛ፡ ሻለቃ ሲሳይ እንደ ተልባ የሚያንጣጣው የቤተ ክርስቲያን ቀነኖ መደፈር ከሆነ አባ መርቃሪዮስ ትቶ በፓትርያሪክ ጳውሎስ ጦሩን የሰበቀበት ምክንያት ምንድ ነው? ሻለቃ ሲሳይ አንድ ማለትን ትቶ ሁለት ብሎ ቁጥር ለመቁጠር የተገደደበት ምክንያት ምንድ ነው?
  • አራተኛ፡ ሻለቃ ሲሳይ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ስለ ተባለ ሰምቶ ከማለት ያለፈ፤ በስማ በለው የሰማውን ተባራሪ ወሬ አላስችል ብሎት መናገር ካለበትም ለሚስቱ ከመቅደድ ያለፈ እንደ አዋቂ ስለ ቀኖና ቤተ ክርስትያን በአደባባይ የመናገርና ተቆርቋሪ ሆኖ የመቅረብ መብት የሰጠው ማን ነው? 

የሀገሬ ሰው “መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ” እንዲል ሻለቃ ሲሳይ በትግራይ ተወላጆች በአጠቃላይ በትግራይ ሕዝብ ያለውን ሥር የሰደደ ጥላቻ ከጥላቻነት አልፎ በትግራይ ሕዝብ ላይ ደም መፋሰስ ይሆን ዘንድ የመርገም አንደበቶቻቸው ከሚያላቅቁ ግለሰቦች መካከል አንዱ ለመሆኑ ሁላችን የምናውቀው እውነታ ነው። ይህ ግለሰብ ምንም ዓይነት የጋዜጠኝነት እውቀትም ሆነ ሥነ ምግባር የሌለውና ያላለፈበት የደም ሰው ሲሆን ቀደም ስል በመጠኑም ቢሆን ለመግለጽ እንደ ሞከርኩት ከሊቅ እስከ ደቂቅ የትግራይ ሕዝብ አንድ ትውልድ የበላ ወታደራዊ የደርግ መንግሥት በካድሬነት ያገለገለ፤ አገሩን ከድቶ ከኮበለለ ዕለት ጀምሮም በትግራይ ህዝብ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ቅስቀሳዎች የተጠመደ የሻዕቢያ ተላላኪ የሆነው ግንቦት 7 ቀለብ እየተሰፈረለት የደም አጀንዳ እያራገበ በታማኝነት ኢሳትን በማገልገል የሚገኝ ሰው ነው።

ሲሳይ አጌና የደርግ ሹሞች እብብቱ ሥር አቅፎ ሲያበቃ ያረፈውን ሰው መቃብር ላይ ቆሞ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የሚስተዋለው ምስጢሩ ሌላ ምንም ሳይሆን ፓትሪያሪክ ጳውሎስ የትግራይ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ነው። ፖለቲካዊ አንድምታውም እንደሆነ ሂትለር “Make the lie big, make it simple, keep saying it, and eventually they will believe it” እንዲል እንዲሁ ነው። ከዚህ ውጭ በአሁን ሰዓት ሲሳይ አጌና/ኢሳት ስለ ፓትርያሪክ ጳውሎስ አንስቶ የምያቀነቅንበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለውም።

ሁለተኛው ዓብዪ ነጥብ የከሰመውን ዕርቀ ሰላም በተመከተ ለማስተላለፍ የተፈለገ መልዕክት የሚያተኩር ብቻ ሳይሆን ሆነ ተብሎ ብዥታ ለመፍጠር ታስቦ የተሰራ ቅጥፈት ጭምር ነው። በሁለቱም አካላት እንቢተኝነት ለዛውም በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች ዕርቅ የወረደ ቅጽበት ህልውና የማይኖረው ራሱን “ማኅበረ ቅዱሳን” በማለት የሚጠራ መንፈሳዊ ካባ ያጠለቀ ጸረ አገር፣ ጸረ ትውልድና ጸረ ቤተ ክርስትያን የሆነ መሰሪ ድርጅት እኩይ ምክር የተነሳ ልዩነቶታቸውን እንዲሰፋ በማድረግ በሁለቱም ተደራዳሪዎች እንቢተኝነት የተበተ ሆኖ ሳለ ሻለቃ ሲሳይ ይህን ሐቅ ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ ያለ አንዳች ተጨባጭ፤ ቢጠየቅ አንዳች የሚያቀርበው ደረቅ መረጃ በሌለበት ሁኔታ ዕርቀ ሰላሙ የተደናቀፈው  በኢ.ህ.ዴ.ግ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ነው የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ያለመ ዲስኩር ነው።

ሙሉ ይዘቱን ልብ ብለው ያደመጡት እንደሆነ ስለ ቤተ ክርስትያን ከቤተ ክርስትያን አባቶችና ሊቃውንት መምህራን በላይ “ይመለከተኛል!” በማለት የሚታወቀው የጥቁር ራስ ስብስብ በሂደቱ መራጭና አስመራጭ ሆኖ ከፊት ለፊት ሲያሸረግድ የነበረው ስለ “ማኅበረ ቅዱሳን” አንዳች ትንፍሽ ያላት ቃል አልነበርችም። ለምን? ያሉኝ እንደሆነ፥ 

አንደኛ፡ የሻለቃ ሲሳይ ዋና ዓላማ የዚህ ሁሉ ትርምስና ዝቅጠት ዋና መሃንዲስ የሆነው “ማኅበረ ቅዱሳንን” ከተጠያቂነት መገላገል ሲሆን፤ 
ሁለተኛ፡ በነበረው ሂደት በጉዳዩ እንደ ማንኛውም የሩቅ ታዛቢ አካል ከተመልካችነት ያለፈ ምንም ዓይነት አውንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተዋጽዖ ያልነበረው የኢ.ህ.ዴ.ግ መንግሥት ደግሞ ባልዋለበት ማጥቆርና መወንጀል ነው። እዚህ ላይ መንግሥት ጣልቃ ገብተዋል የሚል ግለሰብ ካለ መረጃውን ይዞ ይቅረብ።

በመጨረሻ ሲሳይ በሰሚ ጆሮ ላማስረጽ በፈለገው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ የተመልካች ልብ ያጠምድልኛል ሲል አስቦ እንደ ሟሟቂያ አስቀድሞ ያስደመጠን የከራረመ ድምጽ ለምን ይህን እንዳደረገና ህጸጸቹን አጠር አጠር ባለ መልኩ ላስቀምጥና ጽሑፌን አጠናቅቃለሁ።

“በዘረኝነት አንመራም … በዘረኝነት የመጣ ሰው አንፈልግም!”

የሚል ድምጽ ይሰማል። ሲሳይ ይህን ድምጽ ጎልቶ እንዲሰማ የፈለገበት ዋና ምክንያት “አባ ጳውሎስ ዘረኛ ናቸው” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ግልጽ ነው። እንግዲያውስ “ዘረኝነት” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ የሚጓጓ ዜጋ ካለ በደርግ ዘመነ መንግሥት ማለትም በአባ መርቃሪዮስ የፕትርክና ዘመን የቤተ ክህነት ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ብሎ አዋቂን መጠየቅ ከኢሳት ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቁጣ ጭምር እንደሚጠብቆት ስገልጽ በአክብሮት ነው። 

በአሁን ሰዓት አሜሪካ ውስጥ “የጎንደር” “የጎጃም” እየተባለ ጎራ ለይተው እየተቧቀሱና እየተወጋገዙ ያሉትይ ጎጃም ማለት ትግራይ የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው? የሞተ ሰው ከመውቀስ ህያውን መገሰጽ አይሻልህም ነበርን? ለነገሩ አንተም ራስክ እንደሆነ የሞተ ህሊና በመሸከምህ አይደለም ከሞተ ሰው ጋር እንዲህ የሚያራውጥህ። በነገራችን ላይ እኔ አንተን ተከትዬ ስራዎች ህን ሳኮላሽና መና ሳስቀር አንተን ተከትሎ ገደል የሚገባ ትውልድ ለመታደግ እንጅ ከአንተ ጋር መሯሯጥ አምሮብኝ ወይንም ደግሞ ትርፍ ጊዜ ኖሮኝ እንዳይደለ በዚህ አጋጣሚ ለበስርህ እወዳለሁ። 

“… የኢትዮጵያ ሕዝብ አልመረጠውም!” 

አንደኛ፡ ቤተ ክርስቲያን የሰፈር/የእድር ማኅበር አይደለችም፤ ይህ ከሆነ ዘንዳም ተስብስበህ በድምጽ ብልጫ የምትሾመው ሆነ የምትሽረው የቤተ ክርስቲያን አባት ወይም መሪ የለም። ይህ ለሁሉም ግልጽ ይሆን ዘንድ እወዳለሁ።

ሻለቃ ሲሳይ፥ ለመሆኑ ምንም ሳትለፋና ሳትደክምባት ተዘለህ የተቀመጥካባት ምድር እንዲሁ የመጣች አገር ትመስለሃለች? እንግዲያውስ ልንገርህ፥ ሰዎች ከአንደበታቸው በሚወጣ ቃል ትውልዳቸውን ይፈውሳሉ አገራቸውን ይታደጋሉ። እንደ አንተ ያለ በተለወጠ አገር ተቀምጠህ የማትለወጥ፣ ከምትኖርበት ከተማ የማትማር፤ ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላም ያው በአስተሳሰብህ ደርግ፤ ለአገርም ለትውልድም እንደ መጠሪያ ስምህ ሲሳይ ሳትሆን ምንም የማትበጅ አጥፊ፣ አሽክላ፣ መርገምም ነህ።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

March 13, 2012

Advertisements