ኢሳት፡ አማርኛ ተናጋሪ የሻዕቢያ ቡችላ!

እ.አ.አ የካቲት 25/2014  መሆኑ ነው ዘ ቴሌግራፍ ጋዜጣ በዋናው ገጽ የሚከተለውን ርዕስ ይዞ ነበር የወጣው “Turkey PM says incriminating tapes are fake amid growing phone-tapping scandal” ጋዜጣው በይዘቱ የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐርዶጋን የሥጋ ልጃቸው ከሆነው ከቢላል ጋር አደረጉት የተባለውን የአስራ አንድ ደቂቃ ንግግር ሲሆን ጭብጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐርዶጋን ልጃቸው ቢላልን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲያሸሽ መክረዋል ነው። እንደ ዘ ቴሌግራፍ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊቱን አስመልከተው በሰጡት መግለጫ አስጸያፈና ጋጠ ወጥ ተግባር መሆኑን አክለው ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጸው ጉዳዩ ተከታትለው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱም መናገራቸው አክሎ ዘግበዋል። ወደ ኢሳት ላዝግም።

ኢሳት፡ የሐሰት፣ የፈጠራ፣ ብሎም ያልሆነ መረጃ በማቀበል የኢትዮጵያ ሕዝቦች ደም ለመቃባት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ከሆነው ከሻዕቢያ መንግሥት ቀለብ እየተሰፈረለት ጥላቻን የሚዘራ የግንቦት 7 የፕሮፖጋንዳ ማጉልያ ለመሆኑ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ወፍራሙ ዱሪዬ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም የሳይበር ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ (ዋና ጸሐፊ) በተለያዩ ጊዜያት በሰጡት ነዛዜ ድፍን ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ሐቅ ነው።

አንባቢ ሆይ! ጽሑፉ በይዘቱ የኢሳት ማንነት አተኩሮ የሚያትት እንጅ አቶ አለምነው መኮነን “አሉት” ተብሎ በተሰራጨ ቃል ዙሪያ ጸሐፊው አንድ ጥግ ይዘው “ብለዋል” “አላሉም” ሲሉ አይሞግቱም። የጽሑፉ ዓላማም አይደልም። በተያያዘ ኢሳት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ውስጥ ሳይቀር መረጃ የሚያቀብሉኝ ‘ደጋፊዎች’ አሉኝ ብሎ የሚዘባርቀው ነገር ምንኛ የሚጣረስ ስራ እየሰራ ለመሆኑ ግን ቅሌቱን በማስረጃ አስደግፌ በዋናነት አንባቢን ማንቃት ጎን ለጎን ደግሞ ተቋሙን (ኢሳትን) ማራቆት ይቀጥላል።

አንደኛ፡ ኢሳት አይደለም ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ውስጥ መረጃ የሚያቀብለው ሰው ሊኖረው ቀርቶ የድረ ገጹ ጎብኚዎች ቁጥር ተራ የአማርኛ ድረ ገጾች የማይስተካከልና ክፉኛ በድርቅ ለመመታቱ የሚያጋልጥ የተለቀቀው መረጃ ሁላችን አይተነዋል። ይህ በራሱ በቂ ነው። 

ሁለት፡ ኢሳት የኢትዮጵያ መንግሥት በተመለከተ መረጃ በማቀበል ረገድ አለኝ የሚለው አካል ካለ (የለም እንጅ) በምክትል ማዕረግ የማስታወቂያ ሚኒስተሩ አቶ ሽመልስ ከማል ራሳቸው ናቸው። የኢሳት  የመረጃ ምንጭ ሚኒስተሩ አቶ ሽመልስ ከማል ራሳቸው ናቸው ስል ምን ማለት እንደሆነ ላብራራው። 

ህዳር 29/2006 ዓ.ም በኢፌዴሪ ፌዴረሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት 8ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል መከበሩ የሚታወስ ነው። ታድያ በዓሉ ለኢህአዴግ የደስታና የፌስታ ድግስ ሲሆን አንጻሩ ደግሞ ዳያስፖራ እያወየበ ለሚገኘው ለኢሳት የውርደት ካባ የተከናነበበት ዕለት ነበር። እንዴት ይሉኝ ይሆናል። እንዴት ማለት ጥሩ። ኢሳት ቀደም ሲል ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ካደረሱን ለማወቅ እንደተቻለ በማለት ዓይኑን ሳያሽ የዘገባቸው ሁለት “ዜናዎች” በተከታታይ ላቅርብ። 

አንደኛ፡ “በሶማሌ ክልል  የተገነባ የአቶ መለስ ዜናዊ ሀውልት ፈረሰ”

ሁለተኛ፡ “በብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተዘጋ” ሲል

በኢሳት ቅሌት የተደናገጡና በእጅጉም ያፈሩ በሶማሌ ክልል የጅጅጋ ከተማ ነዋሪዎች “እውነትም እሳት!” የሚል ምጸት ታክሎበት በስልክና በኢሜይል ቅጥፈቱን ሲያጋልጡትና ሲያጣድፉት “ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ኢሳት ዜና – ውድ ተመልካቾች ዜና እርማት አለን” [http://ethsat.com/amharic] ሲል የዘገበውን “ዜና” አብረን እናንብበው።

አንደኛ፡ “ሀውልቱ ከተመረቀበት ጊዜ አንስቶ በህዝብ እንዳይታይ በሸራ ተሸፍኖ እንደሚገኝና እስካሁን እንዳልፈረሰ ለማረጋገጥ ተችሎአል”

ሁለተኛ፡ “የተዘጉት የጅጅጋ ነርሲንግ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እና የጅጅጋ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም እንጅ ዩኒቨርስቲው አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን”

እንግዲህ ኢሳት ሁኔታውን በዓይኑ እንዳየ ሰው “ፈረሰ! … ተዘጋ!” ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የዘገበው ዘገባ ወሬው ያቀበለው በስፍራው ከሚገኝ አንድም “ስንሻው ተገኘ!” እያለ ደስ እያለው ሀወልቱ ስያፈርሱ ከነበሩ ሰዎች ማኸል የነበረ፤ “ተዘጋ!” ሲል ስለ ዘገበው ዩኒቨርስቲም በተመሳሳይ ቤተ መጻህፍት ከመዘጋቱ የተነሳ የቤት ሥራውን መስራት ያልቻለ ተማሪ አልያም ዩኒቨሰርቲው ከመዘጋቱ የተነሳ ሥራ ፈትቶ እቤቱ ቁጭ ብሎ የዋለ የተቋሙ ሰራተኛ አይመስልም? 

አንባቢ ሆይ! አገር ሰላም ሳለ ኢሳት ከመሬት ተነስቶ “ፈረሰ! … ተዘጋ!” በማለት ራሱን ቅሌት አዘቅት ውስጥ ይከት ዘንድ፤ እየተንቀለቀለም አፉን ይከፍት ዘንድ ያልሆነ፣ የተሳሳተና ጭብጥ የሌለው መረጃ በመስጠት ረገድ የኢሳት ደጋፊ ወይም ከስፍራው የሚገኝ የኢሳት ዘጋቢ ነው ይህን ያደረገ በማለት ራስዎን ያታልሉ ይሆን? ኢሳት እሳት ውስጥ ለመጨመር የኢሳት ደጋፊና ታማኝ ሪፖርተር ይህን ቢያደርግ ምን አለበት? ምን ችግር አለበት? በማለት እኔን ይሞግቱ ይሆን? የዘንድሮ ሰው እኮ አይጣል ነው ወዳጄ። ለማንኛውም ብራቮ አቶ ሽመልስ ከማል ብያለሁ።

ለማጠቃለል ያክል ኢሳት የአማራ ጠቅላይ ግዛት ምክትል አስተዳደር “አላልኩም” ሲሉ በቃላቸው ያስተባበሉት ቃል የአዞ ዕንባ እያነባ ለጉድ ሲያራግበው እውነት ኢሳት “የአማራ ሕዝብ ተሰደበ!” ብሎ ህመም ስለ ተሰማው ይመስሎታል? ለመሆኑ የሲዖል ፈላስፋ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ተሰምቶ በማይታወቅ ቋንቋ በጠራራ ጸሐይ ኢትዮጵያን ሲገሸልጥዋትና የኢትዮጵያ ሕዝብ በቁሙ ሲሸልቱት ኢሳት የት ነበር? በማለት ራስዎት ይጠይቀዋል?

አልተሳካለትም እንጅ ኢሳት የኢፌዲሪ መንግሥት ባለሥልጣናት ድምጽ እያስመሰለ ኢትዮጵያውያን ሲያደናግር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ባለሥልጣናቱ ባልዋሉበት ጉዳይ ላይ እየወነጀለ የባለ ሥልጣናቱ ድምጽ እያስመሰለ ዜና መስራት እንደሆነ የኢሳት ሁነኛ መታወቂያ መሆኑን አይዘንጉ። 

 ይቀጥላል

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

March 10, 2012

Advertisements