ኢሳት የእኔ ሊሆን አይችልም!

ንብረትነቱ የአንድ በጦርነት፣ በሁከትና በብጥብጥ የሚያምን፤ አንድን ሕዝብ (የትግራይ ሕዝብ) ነጥሎ/በጠላትነት ፈርጆ የሚንቀሳቀስና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብሔር ለማጥፋት የተደራጀ ቡድን ልሳን ሆኖ ሳለ “ፍትሐዊ፣ ገለልተኛና ነጻ ሚድያ” በሚል ፈሊጥ ሕዝብ እርስ በርስ ለማጨራረስና አገር በደም ለማጨቅየት ታጥቆ የተነሳ ጸረ የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የፕሮፖጋንዳ ማዕከል ኢሳት ይህ የማታለያ ታፔላ [“ፍትሐዊ፣ ገለልተኛና ነጻ ሚድያ” የሚለው ማለቴ ነው] ከላዩ ላይ እስካላነሳ ድረስ በቀላሉ መላቀቅ አይኖርም። ኢሳት “ነጻ ሚድያ” ነኝ እያለ ማጭበርበሩን እስካልተወ ድረስ የአመጻ ሥራዎቹን ከሥር ከሥር እየተከታለን አጀንዳውን የማጋለጥ፣ የማራቆት፣ የማክሸፍ፣ የማምከንና የማኮላሸት ድርሻ የዜጎች ሁሉ ግዴታ ነውና። 

ESAT TV

ኢሳት በተራ ግለሰቦች ታጅቦ በደመ ነፍስ እውቀት ሕዝብንና ሀገርን ለማታለል ቆርጦ ከተነሳ ሀገር ወዳድ ዜጎች ደግሞ በፊናቸው በተፈተነ እውቀት ኢሳት ዳግም በማያንሰራራ መልኩ አመድ አልበሰው ለመቅበር ቆርጠው የማይነሱበት ምንም ምክንያት አይኖራቸው። ውሸት ለጊዜው ጥቂቶችን ያታልል እንደሆነ ነው እንጅ የውሸት ዕድሜ አጭር ነው። በጊዜ ውስጥ ኃያልነቱንና የበላይነቱን የሚያረጋግጥ እውነት ደግሞ ምን ጊዜ እውነት ነው። ሲገለጥ ደግሞ በሐሰት የተለከፉ ወረኞች መደናበራቸውና በእውነት የፍርድ ወንበር ላይ መቅረባቸው የማይቀር ነው።

ኢሳት ማን ነው?

ኢሳት የጥቂቶች ጥቅም ማዕከል አድርጎ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለማዘናጋት፣ ለማኮላሸት፣ ለመዝረፍ፣ ለማራቆት፣ ለማታለል ብሎም ሽባ ለማድረግ የሚተጋ ድምጽ እንጅ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለመጥቀምና ለማበልጸግ ታስቦ የተቋቋመ አይደለም። ሌባ ሊሰርቅ፣ ሊያርድና ሊያጠፋ እንጂ ስለ ሌላ እንደማይመጣ ሁሉ በዋናነት የሌቦች መሳሪያ የሆነ ኢሳትም እርስዎንና ቤትዎን ለማጥፋት እንጅ ህይወትዎና ቤትዎ ያቆም ዘንድ ደጃፍዎን አያንኳኳም። ከኢሳት እማራለሁ፣ ከኢሳት እውነቱን አውቃለሁ፣ ከኢሳት አተርፋለሁ ብለው የሚያስቡ ከሆነም በእውነቱ ነገር በእንቅልፍ ልብዎ መሆን አለበት። 

ሕዝብን በበሬ ወልደ ዜና ማወክ፤ በጥሬ ትንተናዎችና ሐተታዎች ዜጎችን ግራ ማጋባት፤ በፈጠራ ድርሳንና አዳዲስ ታሪኮች ሰሚ ጆሮ ማወናበድ፤ እውነተኛ ክስተቶች ደብዛቸውን በማጥፋት እንዲሁም ነገሩን ማስቀየስና የአድማጭ ልብ ማወለል በጥቂቱ የኢሳት ቀዳሚ ዓላማዎችና ግዴታዎች ናቸው። ጽድቅ ለኢሳትና ለኢሳት ሰዎች ሕዝብን በመዋሸትና በማታለል የሚገኝ ትርፍ ነው። 

ኢሳትን የምቃወምበት ምክንያት:

ኢሳት የማልደግፍበት ብቻ ሳይሆን የምቀወምበት ምክንያት እጅግ በስሱ፣ ግልጽና አጭር በሆነ አገላለጽ በማስቀመጥ የኢሳት ዓይነቱ የፕሮፖጋንዳ ጣቢያ ደጋፊዎች አእምሮአዊ ስብዕና ምን እንደሚመስል በመጥቀስ ጽሑፌን እቋጫለሁ። ዓይኑን ከፍቶ ማየት ለሚፈልግ ዜጋ ደግሞ ኢሳትና ሰይጣናዊ ስራው ከዕይታ የተሰወረ አይደለምና መልዕክቴን ተከትሎ አፍቃሬ ኢሳት ራሱንና መንገዱን ይመረምርና ይሰልል ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በግሌ ኢሳትን አጥብቄ የምቀወምበትንና ጮኽ ብዬም ፊት ለፊት ተቃውሞዬን የማሰማው አወቃቀሩም ሆነ ዓላምውና ግቡ ለሀገርና ለወገን የማይበጅ ይልቁንስ አጥፊና አውዳሚ ከሆነው ከጨለማ ሥራው ጋር ምንም ዓይነት ሕብረትም ሆነ ወዳጅነት ስለሌለኝ ነው። በተጨማሪም በጥላቻ ፖለቲካ፣ በግርግር፣ በአመጽ፣ በሁከት፣ በነውጥ፣ በጦርነት፣ ሕዝብንና ሀገርን በማሸበር ለውጥ ይመጣል ብዬ ስለማምን ነው። ከዚህ ውጭ ሌላ ምንም ዓይነት ምክንያት የለኝም። ታቃውሞዬ የአመለካከት ልዩነት መሰረት ያደረገ እንጅ ግላዊ አይደለም። የኢሳት ቅጥረኞች ሆኑ የጣቢያው የበላይ አመራር አባላት አንዳቸውም በአካል አላውቃቸው። በግል የሚያገናኝ ነገርም የለኝም። ሀገሬን እወዳለሁ ለህዝቤም መልካሙን ሁሉ እመኝለታለሁ እንጅ ከኢሳት ጎን በመሰለፍ አገሬን አላወድምም ሕዝቤንም አላተረማምስም። 

አፍቃሬ ኢሳትና አእምሮአዊ ስብዕናው፥ 

 • ፊደላት ከማንበብ ያለፈ ማጣጣም ያልተማረ፤
 • ድምጽ ከመስማት ያለፈ ድምጽን መለየትና ማሰላሰልን ያልተለማመደ፤ 
 • የሚሰማውን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል በአጠቃላይ ማሰብ ያቆመ፤
 • ሚድያ ነጻ፣ ሚዛናዊና ገለልተኛ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ግንዛቤ የሌለው፤
 • የሚድያ ምንነት ያልተገነዘበ፤
 • ለሚሰማው፣ ለሚያየውና ለሚያነበው መልዕክት ጥያቄ የመጠየቅ አቅምም ሞራልም የሌለው፤
 • የፕሮፖጋንዳ ጽንሰ ሃሳብ ያልተረዳ፤
 • ለማሰብ ያልታደለ፤
 • አእምሮው የከዳው፤
 • የእኔ ነው የሚለው አስተሳሰብና አመለካከት የሌለው፤
 • በራሱ የማይተማመንና በራሱ መቆም የማይችል ጥግተኛ፤
 • በሰዎች አጀንዳ ውስጥ ተጠቅልሎ ለመኖር ሳያስበውና ሳያውቀው ራሱን የሰጠ ባለ ዕዳ፤
 • በራሱ ምንም ዓይነት እምነት የሌለው፤
 • ለሚሰራው ሥራ ኃላፊነት የማይወስድ፤ 
 • በጥላቻ የሰከረ ግለሰብ አገሩንና ሕዝቡ ለማተረማመስ፣ ለማውደም፣ ደም ለማቃባትና ለማጨራረስ “ኢሳት የእኔ ነው!” በማለት ድጋፉን ለመግለጽ ሰልፍ ቢወጣ ምን ይደንቃል? ምንም አይደንቅም። ምን ነው? ቢሉ ሰው የሚያውቀውን ያክል ነው የሚኖረውና። ሰው ያልዋለበትንና ያላለፈበት እውቀት ይኖር ዘንድ አይቻለውም። መሆን የሚችለውም እስከዚህ ድረስ ነው። 

በመጨረሻ ለአንባቢያን ማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት ቢኖር ዘመኑ ሰው ትክሻ ላይ ተንጠላጥለው ማለትም ከሰው በሚሰሙትና በሚቀበሉት በስማ በለው ወሬ የሚያልፉት ዘመን ሳይሆን ራስዎን በእውቀት በማስታጠቅ የሚሻገሩት ዘመን መሆኑን ስገልጽ በአክብሮት ነው።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

Nov 24, 2013

Advertisements