ታማኝ በየነ፡ ፈሪ ብቻ ሳይሆኑ ጎበዝ ተማሪ መሆናቸው ጭምር አስመሰከሩ!

ESAT - loser!“ኢሳት በሚገባው መንገድ ወዶ ሳይሆን ተገዶ እየተማረ ለመምጣቱ ምንም አያጠያይቅም። ከፍ ሲል ከላይ የምንመለከታቸው ሁለት የተለያዩ የኢሳት የዝርፍያ ዝግጅት ማስታወቂያዎች ኢሳት ለጉድ ሲያደነቁረን ከርሞ ሲያበቃ እንደ ወትሮው ግን የዝግጅቶቹ ውሎዎች ምን ይመስል እንደነበር ልያሳየን ያልደፈረበት ምክንያትም ኢሳትና ጭፍሮቹ ለኃያልም ኃያል እንዳለው በማያዳግም መልኩ የመማራቸው ውጤት ነው። የዋህ ካልሆነ በስተቀር ለምን? ሲል የሚጠይቅ ሰው ካለ ኢሳት ከማስታወቂያ ያለፈ ሙሉ የዝግጅቶቹ ይዘት ለማሳየት ያልደፈረበት ምክንያት “ከመቀመጫው ላይ ቁስል ያለበት ውሻ እንደልቡ አይጮህም” ከሚለው የአበው ተረት ለጥያቄው በቂ መልስ ያገኛል።” [ቀደም ሲል “የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው!” በሚል ርዕስ ለንባብ ከበቃ ጽሑፍ የተወሰደ]

ከሳምንታት በፊት “የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው!” በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ኢሳት ውጦ ይስቀራቸው ዝግጅቶች እንቅርቱን ይዤ ማስተፋት ነበርና ለንባብ የበቃ ጽሑፌ ተከትሎም እየከነከነው የቶሮንቶ ሲተፋ አሁን ደግሞ ደም እስያስቀመጠውም ቢሆን በቆይታ የኮሎራዶ ውሎውን ተፍቶዋል። ኢሳት በኮሎራዶ የነበረው የዝርፍያ ውሎ ከወትሮ እጅግ አስገራሚና አስደናቂ ዝግጅት ነበር። ከብዙ በጥቂቱ፥  

  • ኢሳት ከቀድሞ ስህተቱ ይልቅ የባሰና የከፋ ስህተት የፈመበት፤ 
  • ለበርካታ ዓመታት ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት የሚታወቁ ደመ ቀዝቃዛ ተናሪ አዝማሪ ታማኝ በየነ ፈሪ ብቻ ሳይሆኑ ጎበዝ ተማሪ መሆናቸው ጭምር ያስመከሩበት፤
  • በራሱ ላይ የሚቀልድ ድሃ ፈላስፋ! ይዞ ብቅ ያለበትና ያስተዋወቀን ድንቅ ውሎም ነበር። 

ኢሳት በባህሪው እውነት አይስማማውም። ስለሆነም ቢያንስ ቢያንስ ከ3 ስዓት የማያንስ ዝግጅት በ35 ደቂቃ ቅራሬ አለሁ ለማለት በቁሙ መሞቱን አረጋግጦላናል። ኢሳት ዝግጅቱ በሰዓቱ አለማቅረቡና ውጦ ለማስቀረት በመሞከሩ ስህተት መፈጸሙ ሳይበቃ በል አምጣ እንጅ ሲባል ቀድሞ በወሰደው እርምጃ ከመጽናት ይቅል ያለምንም ፍሬ ነገር በ35 ደቂቃ እንተፈንቶ ለመገላገል መሞከሩ የከፋ አዘቅት ውስጥ ራሱን መጨመሩ ማን ይንገረው? ኢሳት የ35 ደቂቃ ዝግጅት ለቆ ይሁላችሁ ማለቱ የንቀት ንቀት መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ አይሞክራትም ነበር። 

ማን እንደሚፈራቸው ለይተው ለመግለጽ ባይደፍሩም በሄዱበት አገርና በወጡበት መድረክ “በእውቀት ሳይሆን ከደረቴ ስለምናገር ሰዎች ይፈሩኛል” በማለት ዝና ያተረፉ አዝማሪ ታማኝ በሚገባ በመማራቸው በራሳቸው ሥራዎች ያፍሩ ዘንድ ግድ ብሏቸዋል። ይሄኔ ዝግጅቱ እንዳይታይ የተደረገበት ምክንያት ታማኝ በየነ በልምድ አዋላጅነታቸው የተመረቁበት የቀድሞ የኢፌዲሪ መንግስት የመዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር ክሊፖች ይዘው እንደ ባልቴት ሲራገም እንደ ቁራም ሲጮህ ይሆናል የዋለው። ይህ ባይሆን ኖሮ እንደ ወትሮው ሲፎክሩ፣ ሲንጣጡና ሲባርቁ ባየናቸው ነበር። 

እውነት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በእውነቱ ነገር ታማኝ በየነ የሚሰድበው/የሚያቃልለው ግለሰብም ሆነ ሕዝብ የለም። በታማኝ በየነ እዚህ ግባ የማይባል የወሬደ አስተሳሰብና በነገር የላሽቀ፣ የነቀዘና የሻገተ አእምሮ የሚዘለፍ፣ የሚነቀፍ፣ የሚዘነጠልና የሚዋረድ ብሔር የለም። ታማኝ አፉ በከፈተ ቁጥር ራሱን ብቻ ነው የሚያስገመግመው የሚያዋርደውም። 

በግሌ እንደ ግለሰብ ለታማኝ በየነ ክብር አለኝ። ታድያ ለሳቸው ያለኝ ክብርና አድናቆት የምገልጸው ኢሳትን በመደገፍ ሳይሆን ታማኝ በየነ ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ በሚደረገው ዝግጅት በመገኘት የአቅሜን በማዋጣት ታማኝ በየነን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ነው። አይመስሎትም?

ሌላው የገረመኝ የሌሎቹን አላየሁም አልሰማሁም በማለት ውጦ ሲያስቀር የአቡነ መልከ ጸዴቅ ንግግር ብቻ ይህም ቆራርጦም ቢሆን ለማቅረብ የደፈረበት አንድምታ በሚገባ ገብቶኛል። የሰው ንግግር ሳዳምጥ ከአሁን ከአሁን ስህተት አገኛለሁ በማለት ጊዜዬን የማባክንና ስህተትን ፍለጋ የተሰማራሁ ግለሰብ አይደለሁም እንጅ ከራሴ ጨምሮ ከሰው ስህተት መቼ ይታጣል ብለው ነው። የሚሰራው ስህተት ማዕከል አድርጎ የሚነሳበት አቅጣጫና ዓላማ ይለያይ እንደሆነ  ነው እንጅ ስህተት ያለ ነገር ነው። 

አቡነ መልከ ጸዴቅ የኢሳት ቅጥረኞች ከሚያስቡትና ከሚገምቱት በላይ የልብ ወዳጄ ናቸው። የግኑኝነታችን ጥንካሬም የነበርኩበት ቦታ ላስቬጋስ ድረስ መጥተው የጎበኙኝ ሰው ናቸው። ታድያ ይህ ሁሉ ፍቅርና ወዳጅነት እውነትን ሊሸጥና ሊሸፍን እንደማይችል እኔም ብጹእነታቸውም አሳምረን እናውቃለን። አጥፍተው በልጅነቴ ብነቅፋቸውና የለም! በማለትም ብገስጻቸው ደስ የሚላቸው ሰው እንጅ በቀላሉ የሚከፉና የሚያኮርፉ  አባት እንዳይደሉ ኢሳት ቢያውቅ ኖሮ ያደረገውን አያደርግም ነበር። 

የሼኩ ንግግርሳ ምን ነው ሳናየው የቀሬው? ሰውዬው ኮሎራዶ ድረስ የከነፉ ፎቶ ግራፍ ለመነሳት ነበር ወይስ አልተናገሩም? እኔን! ታማኝ በየነስ ቢሆኑ ማን በተናገረው ውሎ ነበር ባለቀ ሰዓት ፊታቸው ሰካራም የረገጠው ጣሳ አስመስለው ሪፖርት አቅራቢ ሆኖው ያየናቸው? ወይስ ታማኝ በየነ፡ ፈሪ ብቻ ሳይሆኑ ጎበዝ ተማሪ መሆናቸው ጭምር ማስመስከራቸው ነው? በእርግጥ ከስህተትህ መማር የሚበረታታ ተግባር እንጅ የሚነቀፍ አይደለም። ታድያ አዝማሪ ታማኝ በየነ የተያያዩት ትምህርት ሳይሆን ሽፍጥ ነው። 

ማስታወቂያውስ ቢሆን ኢሳት በኮሎራዶ ለሚያካሂደው የዝርፍያ ፕሮግራም አርቲስት ታማኝ በሪፖርት አቅራቢት ሼኩም በመድረክ አጃቢነት ይገኛሉ ነበር የሚለው? የለም! የለም! ኢሳት የሚዘው የሚጨብጠው ጠፍቶበት ሲምታታበት ነው  እንጅ።

ሌላው አስገራሚው የውሎው ክስተት በራሱ ላይ የሚቀልድ ድሃ ፈላስፋ ይዞ ብቅ የማለቱ ጉዳይ ነው። ስማቸውና በአሜሪካ የስራ ክፍላቸው አልጠቀሰም፤ በዝርፍያው ምሽት ግን የታሪክ ፈላስፋ ሆኖው ያመሹ ግለሰብ ወያኔ ደርግን አሸንፎ አዲስ አበብ አልገባም አሉን።

ጥያቄው ወያኔ አዲስ አበባ የገባ ሽንፈት ተከናንቦ ከሆነ ሰውዬው አሜሪካ ምን ያደርጋሉ? ወያኔን አሸንፈው ምኒልክ ቤተ መንግሥት መግባት እንደማይችሉ ከደመደሙ ተሸንፈው መግባት እንደሚችሉ እንዴት ዘነጉት? ሰውዬው የተማሩት ትምህርትና የትንተና ስልት እስከዚህ ድረስ ነበርና ለደርግ ሽንፈት አሜሪካ ተጠያቂ ሲያደርጉም ትንሽ አልሰቀጠጣቸውም። እንግዲያውስ ውድቀቱን የማይቀበል ከወደቀበት እንደማይነሳ በማከል ለዛሬ እዚህ ልሰናበት።

የአብነት ተማሪ “ስለእመብርሃን ስለ ወላዲተ አምላክ” ብሎ የዕለት እንጀራውን እንደሚያገኝ ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው። ኢሳት የትግራይ ሕዝብ ስም ሳያጎድፍ፣ የጥላሸት ሳይቀባ፣ ሳይቦጭቅ፣ ሳይዘባበት፣ ሳያቃልል፣ ሳይሳደብ፣ ሳይዘረጥጥ፣ ሳይኮንን፣ ሳይራገም፣ ሳያጣጥል፣ ሳያማ፣ ሳይዘልፍ፣ ሳያሽሟጥጥና ሳያዋርድ የሚሰበስባት ዜሮ አምስት ሳንቲም የለችም። [ቀደም ሲል “የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው!” በሚል ርዕስ ለንባብ ከበቃ ጽሑፍ የተወሰደ]

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com 

Nov 18, 2013

Advertisements