የኢሳት አመንዝራነት ዕብደትና ቅሌት

በኢሳት ዙሪያ ከጊዜ አንጻር እጅግ አጠር ባለ መልኩ በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ሁለት ነጥቦች አንስተን እንመለከታለን።

  • አንደኛ፡ ኢሳት የተጸናወተው የሐሰት ልክፍት ሳይቸግረውም “በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታቀደው የግድያ ሙከራ ከሸፈ” ሲል ያቦነነው አመድ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን፤
  • ሁለተኛኢሳት እ.አ.አ ኦክተበር 06, 2013 በኮሎራዶ ስለነበረው የዝርፍያና በትግራይ ሕዝብ የከፈተው የጦርነትና የዘር  ማጥፋት ዘመቻ ዝግጅት እንቃኛለን።

ሐተታ፥

በራሱ ጊዜ ራሱን የገደለ ተቅበዥባዡ ውሉደ ቃኤል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በማስመልከት ኢሳት “… የታቀደው የግድያ ሙከራ ከሸፈ” ሲል የነፋው ፕሮፖጋንዳ የደከረተ የዳያስፖራ* የጥላቻና የሁከት ፖለቲካ በማራገብ የሚታወቁ የጭፍን ፖለቲካ አራማጅ ድረ ገጾች ሳይቀሩ “ላሽ ኢሳት መሽቶብሃል!” ሲሉ ተሳልቀው አልፈውታል። ይህም ኢሳት እወክለዋለው ከሚለው የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ልብ ሳይቀር ለመውጣቱ የሚያሳይ ምልክት ነው። እርግጥ ድረ ገጾችቹ ከዚህ ቀደም በየዋኁና ገራገር አቶ አበበ ገላው የተባሉ ግለሰብ የሰራው የቅሌት ድራማ ሳይማሩ ቀርተው ኢሳት ያለውን በድጋሜ ግራ ቀኙን ሳያዩና በሚገባም ሳይመረምሩ ዓይን ያወጣ ፈጣጣ የኢሳት ቅጥፈት በማስተጋባት ቢተባበሩ ነበር የሚደንቀው።

አገናኙ ቀይ መስቀል ይሆን እንዴ የነበረው?

ዝርዝር ቀደዳውን ከመስማቴ በፊት መጀመሪያ ሰበር ፕሮፖጋንዳው ነበር ያገኘሁትና ገና ርዕሱን ስሰማ ወደ አእምሮዬ የመጣ ነገር ቢኖር ሰዎቹ ከአዲስ አበባ አስመራ እንዴት ባለ መስመር ይገናኙ እንደነበር ገርሞኝ “አገናኙ ማን ነበር? ሰዎቹ በምን መንገድ ነበር የሚገናኙ? ስል ራሴን የጠየቅኩ። ለዛውም ተልዕኮ ይዞ ተሰማራ ግለሰብ ተቀማጭነቱ በአስመራ ከተማ መሆኑ ቀርቶ በኤርትራ በርሃዎች መሆኑ ስረዳ ቀደዳው በእንክሮት እንድከታተለው አድርጎኛል።

ዝርዝር ሐተታ ውስጥ አልገባም። የማልገባበት ምክንያትም ከዚህ ቀደም የፕሮፖጋንዳ “ባህሪ” ምን እንደሚመስል በስፋት መወያየታችን እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህም የተነሳ ፕሮፖጋንዳ ማለት ምን ማለት እንደሆነ መጠነኛ ግንዛቤ ይኖረናል ብዬ ስለማምን ሲሆን በዋናነት ደግሞ በጽሑፉ ውስጥ አብረን የምንመለከታቸው/የምናነሳቸው ነጥቦች የኢሳት ሩክሰት፣ አመንዝራነት፣ ቅሌትና ዕብደት በቀላሉ ለማየት ይረዱናል ብዬ በሙሉ ልብ ስለማምን ነው።

ጠቢቡ “የጋለሞታ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች” በማለት እንዳመሳጠረውና አመዝራ ሴት የሰው ሕይወት ለማጥመድ እንደምትወጣ ሁሉ ኢሳትም እንዲሁ የንጹሐን ዜጎች ነፍስ ለመቅጨትና ደም ለማፋሰስ የተሰማራ የክፉ ወሬ መጋዘን፤ የሲዖል ፈላስፋ መቀመጫ ዙፍን፣ ድምጽ ማጉልያ መሳሪያና አንደበት ለመሆኑ ሥራዎቹ ምስክር ናቸው። (ምሳሌ 6፥26)

  • ‘እግዚሃር’ ያስዮት መኖሩን የማይታወቅ፣ ለመኖሩም ምንም ዓይነት ማረጋገጫ የማይቀርብለት፣ “አለ” የሚባለው ቢኖርም የሚበላው የሌለ ወታደር የመንግሥት የደህንነት ቢሮ ምስጢራዊ ግኑኝነት በመጥለፍ፤ በተጨማሪም ማንኛው በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሚለቀቅ የአየር ሞገድ “ያፍናል” እየተባለ በነጋ በጠባ ቁጥር የሚወነጀለው መንግሥት ሲያስቸግር? እንደው ይህን የኢሳት ርኩሰት አሜን ብለው የሚቀበሉ ዜጎች አእምሮአቸውን ለጥጃ ያከራዩ ሰዎች መሆን አለባቸው።
  • በነገራችን ላይ ኤርትራ በርሃ ድረስ “ገዳይ” ያሰማራ ኃይል መልዕክተኛ ተልዕኮውን በአግባቡ ይወጣ ዘንድ መጀመሪያውኑ ምን አስይዞ ነበር የላከው/ያሰማራው? “የኢትዮጵያ መንግሥት” “ተፈላጊው ግለሰብ” (አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ) ከአንጀቱ እንደሚወዳቸው የሚገልጽ የፍቅር ደብዳቤ? ቢሆን ነው እንጅ መልዕክተኛ በዋናነት የተላከበት ተልዕኮ ለማከናውን የሚያስችለው መሳሪያ በማጣት የምጥ ድምጽ ሲያሰማ ባልሰማን ነበር።
  • ለመሆኑ ግለሰቡ ተልዕኮውን ይዞ ወደ ኤርትራ በርሃ የተሰማራ መቼ ነበር? ይህን ጥያቄ ያነሳሁበት ዋና ምክንያት የድምጽ ቀረጻው የተካሄደበት ከ እስከ ነገሩን ፍንትው አድርጎ ስለሚጠቁም ነው። ጊዜው መቼ ነበር? የአምስት ሰዓታት የድምጽ መረጃ ተብሎ የተነገረው እንደ ወረደ የሃያ አራት ሰዓት ውጤት ነው ወይስ የቀናት? የወራትና የዓመታት? የአንድ ቀን ውጤት ከሆነስ ለምን ግለሰቡ ወዲያውኑ ቁጥጥር ስር አልዋለም?
  • ግለሰቡ ለምን ያህል ጊዜ ነበር ሳይፈለግ መፈለግ የሚያምረው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲከታተል የኖረ? የተቀረጸው የአምስት ሰዓታት ድምጽ የተለያዩ ቀናቶች የተደረጉ ውይይቶች ከሆነ ግለሰቡ የተጠለፈበት የመጀመሪያ ዕለት ለምን በቁጥጥር ስር አልዋለም? ከኢትዮጵያ የሚደወለው ስልክ የመጥለፍ ዓቅም ያለው ኃይል ኤርትራ ውስጥ የሚነሳ ስልክ የት ቦታ እንዳለ ለማወቅ ያስቸግራል ብለው የሚያምን ሰው ካለ በእውነቱ ነገር ከኢሳት የባሰ ደንቆሮ መሆን አለበት። መች ይሄ ብቻ ተካሄዱ የተባሉ ውይይቶች በምን ያህል ቀናት ልዩነት የተደረጉ/የሚደረጉ ውይይቶች እንደነበሩም መልስ እንሻለን።
  • ሌላ የሚገርም ነጭ ሐሰት የተጠቀሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለ ሥልጣናት በኤርትራ በርሃ ካደፈጠ መልዕክተኛ ጋር በምን መንገድ ነበር የሚገናኙ? ቀይ መስቀል ይሆን እንዴ ያገናኘቸው የነበረ? ከሆነስ ኢሳት ለምን ይህን “እውነት” ደበቀን?
  • የኢሳት ሰለባ የሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የደህንነት ባለ ሥልጣን ሁለተኛው ሰው ድምጻቸው ቀርቶ ማንነታቸውን አላውቅም። የአለቃ ጸጋይ በርሐ ድምጽ ግን በሚገባ አውቃለሁ። የአለቃ ጸጋይ በርሐ ድምጽ ነው ተብሎ የቀረበ ድምጽ (ማንነቱ ኢሳት ብቻ የሚያውቀው ግለሰብ) ደግሞ ጨርሶ የተጠቃሹ ባለ ሥልጣን ድምጽ እንዳይደለና ሊሆንም እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ። ኢሳት ጦሩ የወረወረባቸው አለቃ ጸጋይ በርሐ የሚባሉ ሌላ ግለሰብ ካልሆኑ በስተቀር። ታድያ ኢሳት በትግራይ ሕዝብና በትግራይ ጠቅላይ ግዛት ተወላጆች ባለ ሥልጣናት ብቻ ያነጣጠረ ዘመቻና ተልዕኮ ምክንያቱ ምን ቢሆን ነው ብለው ያምናሉ?
  • እንደው እኔ የምለው ግን ኢሳት ያቀረበው ድምጽ የተከሳሹ ከፍተኛ የመንግሥት ሹም ድምጽ ለመሆኑ ለአድማጮቹ የሚያቀበው ማስረጃ ምንድ ነው? አድማጭ የኢሳት ፕሮፖጋንዳ “አዎ እውነት!” ነው ብሎ ለመቀበል ስለ ተከሳሾቹ ድምጽ የሚያውቀው ነገር አለ? ከሌለስ ዋስትናው ምንድ ነው? ለነገሩ ኢሳት፡ ይህን ሁሉ የሚደርገው ወያኔ ካልሆነ በቀር እኔን ወጥሮ የሚጠይቅ ማን አባቱ ያበደ ነው! ብሎ በማመን የሚሰራው ስራ እንደሆነማ ማናችንም አንስተውም።
  • አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቢሆኑም እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ከሚገቡ ይልቅ ሰርተው መብላት ይሻላቸው ነበር ብለው አያምኑም? የሕዝብ ገንዘብ በልተህ ስታበቃ ተመልሰህ ደግሞ በድራማ የሕዝብን ልብ ማዋለልና የሕዝብ አንጀት መብላት እንኳ የሐሰት አባት “ሰይጣን” ራሱ የሚያውቃት መላ አይመስለኝም።

ጥጉ፥ እንደዚህ በረቀቀ የቴክኖሎጂ ውጤት የሰለጠናና መነጋጋር የቻለ ሰላይ አንድ አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለ ደደብ ግለሰብ “መግደል” ያቅተዋል አቅቶትም በቁጥጥር ስር ዋለ ቢሉኝ ቆዳዬን በጥፍርዎ የገፈፉት ያህል ነው የሚያመኝ። ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮኸለች!

 ክፍል ሁለት – ይቀጥላል

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

Nov 16, 2013

Advertisements