ህወሐት የትግራይ ሕዝብ በጠላቶቹ ጫንቃ ላይ ቆሞ በደሙ የጻፈው ታሪክ ነው!

መጽሐፉን አንብቤ ከጨረስኩት ሁለት ወራት አልፎታል። የመጽሐፉ ርዕስ ‘Disinformation’ የሚል ነው። የመጽሐፉ አዘጋጅና ዋና ጸሐፊ Lt. Gen. Ion Mihai Pacepa ይባላሉ፤ እአአ 1978 አገራቸው ጥለው የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ የገቡ በኮሚስትዋ አገረ ሮማንያ የኮሚንስት የሥለላ ተቋም ዋና (ከፍተኛ) ባለ ሥልጣን እንዲሁም የፕሬዝዳንት ኒኮሊ ዋና አማካሪ ሆነው ያገለግሉ ባለ ሁለት ኮከብ ጄኔራልም ናቸው። መጽሐፉ ተጨማሪ ማብራሪዎችን ሳይጨምር 354  በአጠቃላይ 427  ገጽ ያለው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተጽፎ ሰኔ 25/2013 ለንባብ የበቃ መጽሐፍ ሲሆን የመጽሐፉ ይዘት ሙሉ በመሉ ከቀድሞዋ ሶቬት ሕብረት [ራሽያ] የስለላ ድርጅት [KGB] በተያያዘ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች አንስቶ አንባቢያን ያስደምማል። በይዘቱ ሰሚ ጆሮ ጭው የሚያደርጉ፤ ዓይን ከፋች ታሪኮች፣ እውነታዎችና ክስተቶች የያዘ መጽሐፍም ነው። 

እውነት ለመናገር መጽሐፉ በKGB ዙሪያ የሚትተውን “ከአእምሮ በላይ” ድርጊቶቹ እውነት ይሁን አይሁን እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው። ምን ነው? ቢሉ፥ ማንበቤን በገፋሁ ቁጥር KGB የሚሉት የቀድሞዋ ሶቬት ሕብረት የስለላ ተቋም ከእስትንፋሴ ይልቅ ቅርብ ሆኖ እስኪሰማኝ ደርስ ነገር ዓለሙ ለመቀበል የሚከብድ ሆኖ ስላገኘሁት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ራሴን በማላውቀው ዓለም ሳገኝ እጅግ ስለ ደነቀኝም ነው። KGB ለራሱ ዓላማ ሌላው ይቅር የምዕራባውያን የሚድያ ተቋማት ሳይቀር ሰርጎ በመግባት የተጭበረበረ ማለት የተፈበረከ ሰነድ በመስጠት፣ ያልሆነ የፈጠራ መረጃዎችን በማቀበልም እንዴት ይጠቀምባቸውና ይጫወትባቸው እንደ ነበርም ሌላ የመጽሐፉ ውበት ነው።

እንደ ጸሐፊው ማብራሪያ ይህ እጅግ ግዙፍና ምስጢራዊ የስለላ ተቋም [KGB] እውነታዎች ደብዛቸው ማጥፋት፣ መረጃዎች ማዛባት፣ አዳዲስ ታሪኮች መፈብረክና ማሰራጨት ጨምሮ ለዚህ ልዩ ተልዕኮ ያሰማራው የሰው ኃይል ቁጥር ሲገልጹም ፥ በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ለተቋሙ ይሰሩ የነበሩ የሰራተኞች ቁጥር የሶቬት ሠራዊትና መከላከያ በድምር እጅግ የሚበልጥ እንደነበር ይናገራሉ። የደህነንት ቢሮ ብቻውን በመላ ዓለም ከአንድ ሚልዮን በላይ የደህንነት ሃላፊዎችና (መኮንነኖች) እንዲሁም በርካታ ሚልዮን መረጃ ሰብሳቢ ሰራተኞች (Informants) እንደ ነበሩትም አክለው ይገልጻሉ። 

በ112 አገሮች ቅርጫንፍ “ያለው” ዓለም ዓቀፍ የሰላም ጉባኤ (WPC) ጨምሮ the WFTU – the World Federation of Trade Unions (በ90 አገሮች); the Women’s International Democratic Federation (በ129 አገሮች); the International Union of Students (በ152 አገሮች); the World Federation of Democratic Youth (በ210 አገሮች) ቅርጫንፍ ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የKGB ውጤት ናቸው ይሉናል የተቋሙ መሃንዲስ በመጽሐፋቸው። ይህ ማለት ልክ በዘመናችን በሰብአዊ መብትና በፍትህ ስም የተቋቋሙ ዋናውን ትተው ድሃ አደግ አገሮች በማሳደድና በማደን የተካኑ እንደ እነ AI, HRW, ICC, CPJ … የመሳሰሉ የባለ ጊዜዎች (የምዕራባውያን) እጃዙር መሳሪያዎች እንደ ማለት ነው። 

እንግዲህ የመጽሐፉ ጸሐፊ ተራና አላፊ አግዳሚ መንገደኛ ሳይሆኑ ብሩህ አእምሮ የነበራቸው የKGB መሃንዲስ ናቸው። የድርጅቶቹ ስም አሰጣጥ በተመለከተም አለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረውም ሆነ ተብሎ የተደረገ መሆኑንም ያስረዳሉ። 

በመጽሐፉ በግልጽ እንደተቀመጠ የሶቬት ሕብረት ግብ የበላይነትዋ ለማረጋገጠ ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን የKGB መቋቋምና የስራ ድርሻ ምዕራባውያንን በተለይ ተቀናቃኝዋ አሜሪካ ማዳከም ወይም ማንኮታኮትና ከጨወታ ውጭ ማድረግ ነው። በወቅቱ የሶቬት ባለ ሥልጣናት ይህን እውን ለማድረግ የተከተሉት መንገድ ደግሞ ከላይ ከፍ ሲል በዝርዝር የተመለከትነው እጅን “በአፍ የሚያስጭን” አሰራር ነበር።

እዚህ ሁሉ ዝርዝር ውስጥ የገባሁ አንባቢን አንድ ቁምነገር ለማስጨበጥ ነው። ይኸውም፥ አንድን በጠላትነት የምትፈርጀው መንግሥት ወይም ሕዝብ በሌላው ወገን ወይም በሕዝብ ዘንድ ለማሳጣት በእቅድ ስለ መወንጀል፣ በፈጠራ ታሪኮች የተሳሳተ መረጃዎችን ስለ ማሰራጨትና ሕዝብን በውሸት ስለመነጥና ለማታለል ስለሚደረጉ ሽርጉድ ዓይናችን ከፍተን ማየት ስለሚገባን ነው።

“ህወሐትን እናድን!?”

በቀድሞ አረመኔያዊ ወታደራዊ የደርግ መንግሥት ወታደር ነበር ‘ሻለቃ’ ሲሳይ አጌና ኋላም የፕሮፖጋንዳና የቅስቀሳ ክፍል ቀስቃሽ ካድሬ የዛሬ ንብረትነቱ የግንቦት 7 የሆነው ወታደራዊ ልሳን በኢሳት የፕሮፖጋንዳ ክፍል ቅጥረኛ በሳለፍነው ቅዳሜ እ.አ.አ ጥቅምት 26/2013 ዓ/ም ከአንድ የወሬ መንፈስ ክፉኛ የተጸናወተው፣ የሚያንቀለቅለውና የሚያንቀዠቅዠው አዳማቂ ግለሰብ ጋር በመሆን የትግራይ መንግሥት “ህወሐትን እናድን!?” ሲል  በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈ ብዙ ገጽ ያለው ወረቀት እየበተነ መሆኑንና የትግራይ መንግሥት የጥሪ ወረቀትም ኢሳት እጅ እንደደረሰ፤ ሙሉ ዘገባውን ለማቅረብ ደግሞ ኢሳት የትርጉም ሥራ እየሰራ እንደሆነ የተለመደ ፕሮፖጋንዳቸውን ይዘው በመቅረብ ያዙኝ ልቀቁኝ ካልሆነም ራሴን አጠፋለሁ ሲሉ ተስተውሎዋል። [ሙሉ ይዘቱን ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ http://ethsat.com/video/esat-efta-26-october-2013/]

‘ሻለቃ’ ሲሳይ አጌና ሁነኛ የደርግ ሰው እንደመሆናቸው መጠን ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) ካንጀታቸው አምርረው ቢጠሉና የትግራይ ሕዝብ ታሪክና አርማ የሆነው ህወሐት የጥላሸት ለመቀባት ሌተቀን ቢተጉ በተጨማሪም ህወሐት ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በመላ የሰጠውን ነጻነትና ያጎናጸፈውን ድል ቢከነክናቸውና ዕሬት ዕሬት ቢላቸው የሚደንቅ አይደለም። እውነት ነው መንግሥትን መቃወም የዜጎች ሁሉ መብት ነው። አንድ ሕዝብ ለነጻነቱ አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍስሶ በልጆቹ መስዋዕነት የጻፈው ታሪክ መቃወም ግን መብት ማለት ምቀኝነት ማለት ነው የሚል አዲስ ትርጉም (አዲስ ፍቺ) ካልተሰጠው በቀር መብት የሕዝብ ክብርን እንደማይነካ በዚህ አጋጣሚ አጽንዖት ሰጥቼ ለማስገንዘብ እወዳለሁ። በአጭሩ በህዝብ ታሪክ መዝመት መብት አይደለም። በህዝብ ታሪክ መዝመት ጥላቻ ነው።

ህወሐት ‘ሻለቃ’ ሲሳይ አጌናና መሰሎቻቸው አራቁቶ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ክብር ስያለብስና ሞገስ ሲሆን እነ አቶ ሲሳይ በህልማቸው የሚያዩት ቅዠት ሁላ እውነት እየመሰላቸው ያልሆነውን ሆነ ያልተደረውን ተደርገ ከማለት ይመለሳሉ ብሎ ማሰብ በራሱ የዋህነት ነው። ‘ሻለቃ’ ሲሳይ የትግራይ መንግሥት “ህወሐትን እናድን!?” የሚል ወረቀት እየበተ ነው በማለት ጥሩምባ ሲነፉ የሳቱት ቁም ነገር ቢኖር የትግራይ ሕዝብ ችግር ከራሱ ታሪክ (ከህወሐት) ሳይሆን ታሪኩን እየሰረዙና እያደበዘዙ የሚገኙ የህዝባዊ ወያነ ባርነት ትግራይ ዲቃላዎች መሆኑን ዘንግተውታል። ህወሐትማ የትግራይ ሕዝብ በልጆቹ ደም የጻፈው የራሱ ታሪክ፣ ተለይቶ የሚታወቅበት አርማው ነው።

ለመሆኑ ሰው አእምሮውን ካልጣለና ካላበደ በስተቀር እንዴት ነው ሰው ከራሱ ጋር የሚጣላው? ይህ ለትግራይ ሕዝብ ስድብ ነው። የትግራይ ሕዝብ የኢሳት ዓይነቱ የጥርቅሞች ስብስብ፣ የማንነት ቀውስ ያለበት፣ ቀዥቃዣ ሕዝብ አይደለም ከራሱ ጋር የሚጣላው። ከራሱ ጋር የተጣላ ከአስመራ እስከ … እየተንቀዋለለ ያለ ማን እንደሆነ ለሁላችን ግልጽ ነው።

እንግዲህ ስለ ህወሐት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ምንነት ብዙ ተወያይተናል። ህወሐት ማለት ለትግራይ ሕዝብ ደም ሥሩ ስለመሆኑ፤ ህወሐት የትግራይ ሕዝብ የሚኮራበት ታሪኩና ማንነቱ መሆኑ፤ በአጠቃላይ ህወሐት ማለት የትግራይ ሕዝብ በጠላቶቹ ጫንቃ ላይ ቆሞ በደሙ የጻፈው ታሪክ ነው ብለናል።

የትግራይ ሕዝብ ሰላም ወዳድነቱና ትዕግስቱ አልታይ ብሎት መስመር ጥሶ እግሩን ለሚያነሳ በየትኛውም አቅጣጫ ሊሰለፍበት የሚችለው የጠላት ኃይል ዛሬም እንደትናቱ በጠላቶቹ ላይ የሚታጠፍ እጅ እንደሌለውም ቀደም በቀደሙ ጽሑፎቼ በስፋት ስላተትኩት ያለንበት አገር የመድኃኒት አገር ስለሆነ አሁን ለሻለቃ ሲሳይ አጌና ዕብደት መድኃኒት ለቅሌታቸውም ማስታገሻ የሚሆን ህወሐት ለመላ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የዋለውን ውለታና የከፈለውን የደም መስዋዕትነት ከብዙ በጥቂቱ በመዘርዘር ጽሑፌን ልቋጭ። 

ህወሐት ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ይመስላል፥

  • በማንነታቸው ሳይሸማቀቁ ከሌላው ወገን እኩል እንዲኮሩና እንዲቆሙ ዕድል የሰጠ/የፈጠረ፤
  • ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአገራቸው እንደ ባሮች ሳይሆን እንደ ጌቶች የሾመ፤
  • ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከጨቋኝ ሥርዓት/ከባርነት ነጻ ያወጣ፤
  • ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ መሬት አንገታቸውን አቀርቅረውና ተሳቀው ሳይሆን ቀና ብለው ይረግጧት ዘንድ ያደረገ፤
  • በጨለማቸው ላይ ብርሃንን ያበራ፤
  • በሞቱ ህልውናቸው ያረጋገጠ፤
  • በአፋቸው ሳቅ በከንፈሮቻቸው እልልታን ያኖረ ማን ቢሆን ነው? እንዴት እንዴት ነው ነገሩ ጎበዝ? ሻለቃ ሲሳይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነው በፕሮፖጋንዳ ሕዝብን ሲያደነዝዙ፤ እነ አፈ-ወርቅ አግደው በካድሬነት ሕዝብን እያገቱ ጉድጓድ ውስጥ ሲጨመሩና የዜጎች ብልት እየቆራረጡ ወገን ቁም ስቁሉን ሲያሳዩ የነበሩ፤ እነ ታማኝ (አሉባይ) በየነ ከበሮ ይዘው ገዳዮች እያጀቡ ሕዝብ ሲገድሉና ሲያስገድሉ፣ ሲያርዱና ሲያሳርዱ የነበሩ ነፈሰ ገዳዮች ናቸው። የለም! የሚል ሰው ካለ መድረኩ ክፍት ነው። ለነገሩ መድረክ ሲኖር አይደል።

ህወሐት ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከዚህም ሁሉ በላይ ነው። እንደው ውርደትንና ሽንፈትን ከተከናነቡ ወገን (የደርግ ወታደር ነበር) ካልሆነ በስተቀር በህወሐት የጀግንነት ታሪክ ቅር የሚለው ማን ነው? ቢዋጥልንም ባይዋጥልንም፤ ቢስማማንም ባይስማማንም፤ ብንቀበለውም ባንቀበለውም አገር ነጻ የወጣች ህወሐት (የትግራይ ሕዝብ) ባፈሰሰው ደምና በከፈለው የህይወት መስዋዕትነት ነው። አይመስሎትም?

በተረፈ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ከመቆም ጋር በተያያዘ ቀጥተኛ ችግር ያላቸው የደርግ ቅሪቶችና በጥላቻ የተሞሉ ልሒቃን የህወሐት ስም በተነሳ ቁጥር የኢየሱስ ስም እንዳለፈበት ሰይጣን ቢንቀባዥራቸውና በነጋ በጠባ ቁጥር ህወሐትን ቢያወግዙና ቢኮንኑ ምን ይደንቃል? ከአፉ ሥጋ እንደተመነገለ ውሻ ሰዎች ህወሐት ባስመዘገበው ድል አውሮፓና አመሪካ ተሰሳስበው ቢጮኹና ቢንፈራገጡ ምኑ ነው የሚደንቀው? እንደው ይህን የመሰለ ከባድ ኪሳራና ውርደት ደርሶባቸው፤ ተነጥቀው፣ ተራቁተው፣ ህፍረት ተከናንበውና ተቦጫጭቀው ሲያበቁ እጅና እግራቸው ሰብስበው አርፈው ቢቀመጡና ዝም ቢሉ ነበር/ነው የሚገርመው። 

እኔ ግን ለእርስዎ (ለአንባቢ) ጥያቄ አለኝ፥

ኢሳት እየነዛው ያለ ፕሮፖጋንዳ ስምተውታል አይደል? ታድያ ይህ የኢሳት ፕሮፖጋንዳ ሲሰሙ ምን አሉ? 

ለምንድ ነው የትግራይ ሕዝብ የኢሳት ዒላማ የሆነው? ኢሳት ለምንድ ነው የትግራይ ሕዝብ መልካም መልክና ገጽታ ማጥፋት የተያያዘው? ይህ ሕዝብ ሕዝባችን አይደለም ወይ? ቢያንስ ቢያንስ በተባበሩት መንግሥታት ዘንድ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እስካለች ድረስ የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለም ወይ? ነገሩ እንዲህ ከሆነ ለምን የኦሮሞ ፈረስት የፖለቲካ ፕሮግራምና የዕለት ዕለት እንቅስቃሴዎች መወያያ አይሆንም? ኢሳት ለምን የኦሮሞ ፈረስት ሕዝባዊ ስብሰባዎችና በራሪ ጽሑፎች እየተረጎመ አያቀርብም? ኢሳት ትግርኛ የሚያውቅ ከሆነ ሌላው ቢቀር ለምን አንዲት መስመር የማትሞላ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃል ተርጉሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱ አያሳይም?” አሉ ወይስ አሁንም አልነቁም?

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 30, 2013

Advertisements