ኢሳት፡ ቀባሪ ያጣ በድን!

“ኢሳት በሚገባው መንገድ ወዶ ሳይሆን ተገዶ እየተማረ ለመምጣቱ ምንም አያጠያይቅም። ከፍ ሲል ከላይ የምንመለከታቸው ሁለት የተለያዩ የኢሳት የዝርፍያ ዝግጅት ማስታወቂያዎች ኢሳት ለጉድ ሲያደነቁረን ከርሞ ሲያበቃ እንደ ወትሮው ግን የዝግጅቶቹ ውሎዎች ምን ይመስል እንደነበር ልያሳየን ያልደፈረበት ምክንያትም ኢሳትና ጭፍሮቹ ለኃያልም ኃያል እንዳለው በማያዳግም መልኩ የመማራቸው ውጤት ነው። የዋህ ካልሆነ በስተቀር ለምን? ሲል የሚጠይቅ ሰው ካለ ኢሳት ከማስታወቂያ ያለፈ ሙሉ የዝግጅቶቹ ይዘት ለማሳየት ያልደፈረበት ምክንያት “ከመቀመጫው ላይ ቁስል ያለበት ውሻ እንደልቡ አይጮህም” ከሚለው የአበው ተረት ለጥያቄው በቂ መልስ ያገኛል።” [ቀደም ሲል “የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው!” በሚል ርዕስ ለንባብ ከበቃ ጽሑፍ የተወሰደ] 

ከላይ ከፍ ሲል የምናነበው ዓረፍተ ነገር ለንባብ የበቃ ትናንት አሁድ ኦክተበር 27/2013 ከምሽቱ 7pm ነበር። ጽሑፌን የምለጥፍበት ገጽ ከ 5pm በኋላ ከሰባት ሰዓታት በፊት ቀደም ብሎ መሆኑ ነው የሚቀጥለውን ቀን ይቀበላል። ታድያ ጽሑፌን የማያመልጠው የኢሳት የፕሮፖጋንዳ ክፍል ጽሑፌን ተከትሎ ኦክተበር 6, 2013 በኮሎራዶ ያካሄደውን የዝርፍያ ዝግጅቱን ትቶ ኦክተበር 13, 2013 በቶሮንቶ ካናዳ ያደረገውን የዝርፍያ ዝግጅቱ በዛሬው ዕለት ሰኞ ከሰዓት አከባቢ ለጥፎልናል። [የኢሳት የዝርፍያና የልመና ምሽት በቶሮንቶ ለመመለከት ሊንኩን ይጫኑ http://ethsat.com/video/esat-special-toronto-esat-fundraising-28-october-2013/]

ቀድሞም ቢሆን የጽሑፌ ዓላማ ኢሳትን እንቅርቱን ይዤ የዋጠውን ማስተፋት ነበርና የቶሮንቶ ውሎውን አስተፍቸዋለሁ። በዋናነት የሚፈለገውም ይህ ነበር። ሕዝብ ጠላቱን እንዲያውቅ። ጊዜ ቢያልፍበትም እንደ ቶሮንቶው ቆራርጦም ቢሆን የኮሎራዶም በቅርቡ እንደሚተፋ በተስፋ እንጠብቃለን። 

የቶሮንቶ ምሽት በርካታ አስደናቂ ክስተቶች ታይቶውበታል። በጥቂቱ የጠቀስን እንደሆነም በዚህ ምሽት አቶ አበበ ገላው አምልኮ ቀረሽ ውዳሴ የተንበሸበሹበት ምሽት ነበር። በሞቅታው ሚዛናቸው የሳቱ (የተንሸራተቱ) አቶ አበበ ገላው ለአፍታም ቢሆን “ነጻ አውጪ” ሆነው አምሽተዋል። ምሽቱ ለአቶ አበበ ገላው ብዙ የተዋጣ ምሽት አልነበረም። እንደው አቶ አበበ ገላው ሳያስቡት ጠማማነታቸው አምነው የተቀብሉበትና የተናዘዙበት (በአንድ በኩል የሚደገፍ ድርጊት ነው)፣ እኛ ኢትዮጵያውያንን የሸነገሉበት፣ ዱላ ቢያቀብሉት እርስ በርሱ የሚከሻከሽ ሃሳብ የሰነዘሩበት ምሽት ነበር። አቶ አበበ ገላው “ሀገራችን!” “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!” ማለት ሲያበዙም “ኢትዮጵያ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረች አገር ናት” የሚለውን የአቶ ኢሳይያስ ሃሳብ በመቃወም ኢትዮጵያዊነታቸውን ያስመሰክራሉ ብየ ጠብቄ ነበር። ዱሩዬው ዶ/ር ብርሃኑ ሳያስጠነቅቃቸው አልቀረም መሰለኝ አላየሁም አልሰማሁም ብለው አለፉን።

በአቶ አበባ ገላው ገና ተስፋ አልቆረጥኩም። ከሌሎች አዳማቂዎችና ከበሮ መቺዎች ጋር እኩል የማያቸው ዓይነት ሰው አልነበሩምና ያለ አንዳች ጥርጥርም በኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ ይዘምታሉ የሚል እምነት ነበረኝ። ለምሳሌ ያክል፥ እንጀራችንን እየበላ የወይን ጠጃችንም እየጠጣ ለአስር ዓመታት ያክል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ሲሰልል የኖረ ጠላት በማስመልከት ኢትዮያዊነታቸው ይገልጻሉ ብዬ ስጠብቅ ባዶ። “አቶ ኢሳይያስ እውነት ነው … ተስፋይ ገብረአብም ደግ አደረገ!” የማለት ያህል አቶ አበባ ገላው የባጡ ቁጡ ቀበጣጥረውና ዘበራርቀው ሲወርዱ ከምር ማመን አቅቶኛል።  

ማንን እንደሚያዙበት ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም አቶ አበባ ገላው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ነፍስ በማጥፋታቸው/በመግደላቸውም [የተባለውን ነው ያስቀመጥኩት] ሙሉ የጀነራል ማዕረግ የተሾሙበት ምሽትም ነበር። አጤው በተውሶ ታሪክ (የዳንኤል ታሪክ) ለጨረታ የቀረቡበት ስዕልም የምሽቱ ትንግርታዊ ገጽታው አንዱ ነው። በአጭሩ የቶሮንቶ የኢሳት የዝርፍያና የልመና ምሽት ግማቱ ሰው ያስጠጋም ነበር።  ከብዙ በጥቂቱም እንደሚከተለው ይመስል ነበር፥

  • “ወያኔ ሲመጣ በነጣላ ጫማና በቁምጣ ሱሪ ራቁቱን አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትና መከላከያ ሚኒስተር ቅማሉን ያራገፈበት ልብሱን ያጠበበት ነበር። ሽንት ቤቱ ሁሉ ተዘግቶ ለመጸዳጃ እንኳን ችግር እንደፈጠረ አዲስ አበባ የነበርን ሁሉ እናውቃለን።” መቼም ወያኔ ሲባል ኦሮሞ፣ አማራ፣ ደቡብ ወይም ሲዳማ ነው ብሎ የሚያምን ሰው ካለ ውሸታም ነው። ታድያ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ እማን ትክሻ ላይ የሚያርፈው ያሉኝ እንደሆነ መልሱ ስለሚያውቁት ወደሚቀጥለው ተናጋሪ አልፋለሁ።
  • “በተወሰነ ክልል ብቻ (የትግራይ ክልል መሆኑ ነው) በከፍተኛ የትምህርት ብልጫ አድርጎ ገዢና ተገዢ መፍጠር” 
  • “ኢትዮጵያዊውን ዜጋ በሀገሩ ሁለተኛ ሦስተኛ አራተኛ (አንደኛ ዜጋ የትግራይ ሕዝብ መሆኑ ነው) ዜጋ ሆኖ እንዲኖር እያደረጉ በኢኮኖሚና በመብት ጥቅም መለያየት ማቃቃር።”
  • “ምንም እንኳ እኛ ብዙዎች ብንሆንም (22 ሚልዮን > 6 ሚልዮን) ግን ደግሞ ጥንካሬ ያንሰናል ይህ ማመን አለብን።” [አቶ አበበ ገላው 1:05:02]

“የአብነት ተማሪ “ስለእመብርሃን ስለ ወላዲተ አምላክ” ብሎ የዕለት እንጀራውን እንደሚያገኝ ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው። ኢሳት የትግራይ ሕዝብ ስም ሳያጎድፍ፣ የጥላሸት ሳይቀባ፣ ሳይቦጭቅ፣ ሳይዘባበት፣ ሳያቃልል፣ ሳይሳደብ፣ ሳይዘረጥጥ፣ ሳይኮንን፣ ሳይራገም፣ ሳያጣጥል፣ ሳያማ፣ ሳይዘልፍ፣ ሳያሽሟጥጥና ሳያዋርድ የሚሰበስባት ዜሮ አምስት ሳንቲም የለችም።” [ቀደም ሲል “የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው!” በሚል ርዕስ ለንባብ ከበቃ ጽሑፍ የተወሰደ] አወይ ኢሳት!

ገንዘብ! ገንዘብ! ገንዘብ! ብሎ ሲሸበለል ያየነው ዶ/ር ብርሃኑ ሰዎች የሚያንጨበጭቡለት ያክል በልቤ ቦታ ከሌላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው። ብርሃኑ ተራ ዱሩዬ ነው። እሱን ፊት ለፊት በሚደረግ ውይይት በሚገባው ፍልስፍና ማስበርገግ ነው እንጅ በጽሑፍ የሚሰማ ዓይነት ሰው ስላይደለም ጊዜዬ የማጠፋበት ምክንያት የለኝም።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 28, 2013 

Advertisements