ኢሳት፡ የጠባብ ቡድን፣ የዘመድ አዝማድና የቤተሰብ መገልገያ!

ኢሳት: ስለ አንድ ግለሰብ ሆነ ስለ አንድ የፖለቲካ ተቋም ኃጢአትና ግድፈት እየተንቀለቀለ ለማውራትና ለማንበልበል ሲፈልግ፤ በተጨማሪም “ግድ የለም! በእኔ ይሁንባችሁ … እመኑኝ!” ሲል ዕብድ እያለ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳና የሚዘራው መጥፎ የአመጽ ዘር በአጠቃላይ የሚሰራው ሥራ ሁሉ በምንጭ ደረጃ ከሦስት አቅጣጫ የመጣ/የተገኘ እንደሆነ ነው።

  • አንደኛ፡ የራሱ የፈጠራ ድርሳን ሲሆን፤ [ይህ ማለት ውስጥ አዋቂዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሪፖርተራችን ከስፍራው እንደ ገለጸው፣ ከደህንነት ምንጮቻችን የተገኘ መረጃ እንደሚያስረዳው  የሚሉ የሞኝ ፈሊጦች ያጠቃላል] 
  • ሁለት፡ በፈረንጅ አንደበት የተነገረ እንደሆነ፤ [“ሰብአዊ መብት” በሚል ሽፋን የሚታወቁ የዘመኑ የቅኝ ግዥ አቀንቃኞች ይጨምራል]
  • ሦስት፡ በጠላትነት ከሚፈርጀው አካል ያፈነገጠ ግለሰብ የተናገረው ቃል እንደሆነ፤ [ለምሳሌ፡ የህዝባዊ ወያኔ ባርነት ትግራይ የቀድሞ አባላት ሁነኛ የኢሳት መጠቀሚያ መሳሪያዎች ናቸው] –  ኢሳት ለጣቢያው የጥፋትና የሁከት አጀንዳ በሚያመች መልኩ እየቀመመ፣ እየቆራረጠ፣ እየሸቃቀጠ፣ እየሰረዘና እየደለዘ “ይኸው …” ሲል ንጹሐንን ማደናገርና ማታለል ልዩ መታወቂያው ነው። 

ታድያ ሐቅ የሌለው ክፉና አመጽኛ ሰው ሁልጊዜ እንዳታለለና እንዳጭበረበረ አይኖርምና በዛሬው ዕለት ኢሳት በተራው በሰፈረው መስፈሪያ የእጁን ማግኘቱ እርግጥ ይሆናል ማለት ነው። በመቀጠል አብረን የምናነበው እጅን በአፍ የሚያስጭን ማስታወሻ በኢሳት ውስጥ የተሰገሰጉ በሙስና ጋን ውስጥ የተነከሩ ወረበሎችና የኢሳት ውስጠ ምሥጢር እንዲሁም አቅጣጫ ለኢሳት የቦርድ አባላት በያሉበት የተጻፈ የስምታ ደብዳቤ ሲሆን የማስታወሻው ጸሐፊ የቀድሞ የኢሳት ባልደራባ ነበር አቶ ክፍለ ማሞ አለሜ ናቸው። መልካም ንባብ!

Screen Shot 2013-10-24 at 3.47.42 PM

ሙሉ የማስታወሻው  ይዘት ለማንበብ ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ ይጫኑ፥  ኢሳት፡ የጠባብ ቡድን፣ የዘመድ አዝማድና የቤተሰብ መገልገያ! ESAT-G7

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 25, 2013

Advertisements