“ማኅበረ ቅዱሳን”፡ ማሰብ ያቆመ ዜጋ የተከማቸበት የመቃብር ስፍራ!

የዘንድሮ ጋዜጠኛ የሞያው ሥነ ምግባር ጠብቆ ሕዝባዊና ሀገራዊ ግዴታውን በመወጣት ፈንታ የምዕራባውያን ሀገራት መሳሪያ የሆኑና የማያሳስብ የሚያሳስባቸው CPJ, HRW, Amnesty International … የመሳሰሉ ጸረ አህጉራችን ጸረ አፍሪካ የተሰለፉ፤ በአጠቃላይ የቀኝ ግዛት ደጋፊ አቀንቃኞችና ናፋቂ ድርጅቶች ተማምኖ ህዝብ በሚያውክ ሥራ መጠመድና ከእኔ ወዲያ ላሳር ማለት ልዩ መታወቂያ ከሆነ ውሎ አድረዋል። (ኃላፍነቱ በአግባቡ የሚወጣ አንድም ንጹህ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ የለም አላልኩም። የአገሬ ሰው ሲተርት “የጊዮርጊስን ግብር የበላ ጩህ ጩህ ይለዋል” እንዲል ኩታራው በራሱ ጊዜ ሲጮኽ ያገኙታል።)

በነገራችን ላይ የእነዚህ ድርጅቶች መቋቋም (CPJ, HRW, Amnesty International) ዋና ዓላማ የሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳስቧቸው ከሆነ አፍሪካ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ በምዕራባውያን አገሮች ከሚፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ፤ የዘር ማጥፋት ወንጀልና እልቂት፤ ሉዓላዊ መንግሥታትና ሀገራት የማውደውና የማተረማመስ ሰይጣዊ ድርጊት ሲነጻጸር በአፍሪካ ግፍ አለ ብሎ መናገር አሳፋሪ ነው። አንድም የሚነገር ሁሉ አምነው የሚቀበሉ ከሆነ ከራዳር ውጭ ኖት ማለት ነው። (በአፍሪካ ግፍ የለም አላልኩም። አለ!)

የሆነ ሆኖ አቶ ተመስገኝ ደሳለኝ የተባሉ ግለሰብ ባሳለፍነው ሳምንት “ፍክት” በሚል የፕሮፖጋንዳ መጽሔታቸው “ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ “ማህበረ ቅዱሳን” ይሆን? በማለት ባልዋሉበትና ባላለፈባቸው እውቀት ለንባብ ያበቁት ጽሑፍ (አንብቤ ኢህአዴግን በተመለከተ እኔን አይመለከትም ኢህአዴግ መልስ መስጠት ካለበት መልስ ይስጥበት) “ማህበረ ቅዱሳን” በማስመልከት የጻፉት ጽሑፍ ግን ሰውየው የት አገር ስላለ “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው የሚያወሩት? ብዬ በአግራሞት አንድም ለአቶ ተመስገኝ ደሳለኝ ለትምህርት ይሆን ዘንድ በተከታታይ “ማኅበረ ቅዱሳን”፡ አገር በታኝ ትውልድ ገዳይ የጽንፈኞች መናገሻ ነው!” እንዲሁም “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚያራግባቸው ቁንጽል መፈክሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ፥ ” በሚሉ ርዕሶች ከትቤ በራሴ ድረ ገጽ [https://salsaywoyane.wordpress.com/] ማስነበቤ የሚታወስ ሆኖ “ነጻ ሚድያ” ሲባል ሰምቼም እንደ አንድ ለሀገሩና ለህዝቡ ጥቅም የቆመ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በነጻነት የጻፍኩት ጽሑፍ የአቶ ተመስገኝ ደሳለኝ “ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ “ማህበረ ቅዱሳን” ይሆን? ላስነበቡን ድረ ገጾች በሙሉ ልኬው ነበር።

ታድያ “ነጻ ሚድያዎቹ” በነጻነት እንድትዋሽና እንድትቀጥፍ የሚያበረታቱ እንጅ በነጻነት የተጻፈ እውነት የማስተናገድ ባህሪ የላቸውምና የተላከላቸው ጽሑፍ ለንባብ እንዲበቃ አልፈቀዱም። አንድም ትጋታቸው ሕዝብ የሚያስፈልገውን በማቅረብ  ሕዝብን ማገልገል ሳይሆን የጢቂቶች አጀንዳ ማራገብ ሆኖ ስላገኘሁት በበኩሌ ብዙም አልደነቀኝም።

የጽሑፉ ውሱንነት

በጽንፈኝነት ዙሪያ የሚያትተው ክፍል ብዙሐንን ያማከለ መሰረታዊና መጠነኛ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ጽሑፍ እንጅ ከርዕሰ ጉዳዩ ተያይዘው ለሚነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች አይዳስ ስም።

ጽንፈኝነት ምንድ ነው?

ኃይማኖታዊ ጽንፈኝነት/አክራሪነት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ በዚህ መልክ ላስቀምጠው። ጽንፈኛ/አክራሪ ወይም ኃይማኖተኛ ሰው “እኔ የምከተለው/የማምነው/የእኔ ሃይማኖት ብቻ ነው ትክክል!” በማለት ብቻ አያቆምም። የኃይማኖተኛ ሰው (አክራሪ/ጽንፈኝኛ ሰው) አደገኛነቱ እሱ ከሚምነው/ከሚከተለው ወይም “የእኔ” ከሚለው ኃይማኖት ውጭ ያሉ የሌላ ቤተ እምነት ተከታዮች በጠላትነት መፈረጁና ጸር መሆኑ ነው። ማንኛውም ዕለታዊ እንቅስቃሴው የሚመዝነው “በሃይማኖት” መነጽር ነው። ፍትሐዊነት፣ ሚዛናዊነት፣ እኩልነት ብሎ ነገር አያውቃቸውም። በአጭሩ ጽንፈኛ/አክራሪ ማለት ማሰብ ያቆመ ፍጥረት ማለት ነው። ሰው ማሰብ አቆመ ማለት ደግሞ ለመልካም ነገር (ለቁምነገር) ነው የማይበቃ እንጅ ለጥፋት የሚስተካከለው የለም። ሰው ማሰብ ያቆመ ዕለት ከበላተኛ አውሬ ይልቅ አደገኛ ፍጥረት ነው። እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ “ማኅበረ ቅዱሳን” ማለት ይህን ይመስላል።

ከዚህ ቀደም ክርስትና “ከሃይማኖተኝነት” መንፈስ እንዴት እንደሚለይና ክርስትና “ሃይማኖት” ሳይሆን ህይወት እንደሆነ በሚገባ ገልጫለሁ። ስለዚህ ወደኋላ ተመልሼ “ኃይማኖተኛ ሰው” ምን ማለት ነው? ወደሚለው ርዕስ አልመለስም። በግርድፉ ግን ክርስትና ማለት ምን ማለት እንደሆነ፤ የክርስትና ህይወት የቀመሰሰ፤ በጽድቅና በእውነት ለሚመላለስ ሰው “ሃይማኖተኝነት” ምን ማለት እንደሆነ ተርጓሚ አያስፈለገውም። አንድም እውነትን አበጥሮ የሚያውቅ ሰው ውሸትን ለይቶ ለማራቆት አንዳች የሚቸግረው ነገር የለምና።

ወደ “የማኅበረ ቅዱሳን” እና ጭፍሮቹ የጽንፈኝነት “ባህሪይ”/ተግባር የተመለስን እንደሆነ – “የማኅበረ ቅዱሳን” ጽንፈኝነት ለየት የሚደርገው የተጠለለባት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንኳ በቅጡ አጥርቶ የማያውቅ፣ ጫፍ ይዞ ቡራከረዬ ማለት የሚቀናው፣ ጥሬ/ያልበሰለ፣ የደንቆሮ “የመሃይምና” የአቡጊዳ ሽፍታ ስብስብ መሆኑ ነው። በአጠቃላይ “የማኅበረ ቅዱሳንና” አባላቶቹ ጽንፈኝነት ከእወቀት ማነስ የመጣ ነው።

ጽንፈኝነት በሐዲስ ኪዳን

ንጹሑ፤ በአንደበቱ በደል የማይገኝበት፤ በመልካምነቱ፣ በፈዋሽነቱ፣ በደግነቱ፣ በእውነተኛነቱ የተመሰከረለት፤ በቃሉና በስራው የሚስተካከከለው የሌለ ጻዲቅ፤ ሁለመናው ብርሃን፤ በአስተማሪነቱ አቻ የሌለው መለኮታዊ፤ ከሁለት ሺህ ዘመናት እስከ ምጽአት ድረስም ለሚያምኑት ለተከተሉትም ፈውስ፣ መድሃኒት፣ ህይወትና መንገድ የሆነው ኢየሱስ መስቀል ላይ ያንጠለጠለ ማን ቢሆን ነው ጎበዝ? ሴተኛ አዳሪ፣ ቀራጭ፣ ማጅራ መች፣ መቀስ እጁ (ሌባ) እኮ አልነበረም ኢየሱስን የገረፉ ያንገላቱ ያቆሰሰሉና መስቀል ላይ ያንጠለጠሉ የሃይማኖት አዋቂዎች፣ የመጻህፍት መምህራን፣ ሊቃውንት ነን የሚሉ ጽንፈኝነትን የተጠናወታቸው የአይሁድ እምነት አክራሪዎች ካህናት ነበሩ። ምን እያልኩ እንደሆነ ይገባዎት ዘንድ በዚህ መልክ ላስቀምተው። ኢየሱስ ነው ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ወይስ ኢየሱስን የሰቀሉ የአይሁድ ረበናት? ኢየሱስ ነው እንጅ! ብለው ከመለሱልኝ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ምን ማለት እንደሆነ ሳስረዳ በሚገባ  ይዘውኛል ማለት ነው።

አሁን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በአንደኛው ክፍለ ዘመን ከዛም በፊት ስለ ነበሩ ፈሪሳውያን በመባል ስለሚታወቁ ሃይማኖተኞች በዘመናችን ስመ አጠራር እክራሪዎች/ጽንፈኝች የሚለውን አብረን እንመልከት።

ፈሪሳውያን፥

 • የሙሴን ሕግ ጠንቅቀው የሚያውቁ: – [“ማኅበረ ቅዱሳን” አይደለም የቤተ ክርስቲያን ሕግ ጠንቅቆ ሊያውቅ ቀርቶ ጸሎተ ሃይማኖት በቃሉ የማይዘልቅ፤ የቄስ ጥምጣም ስለ ጠመጠመ ቄስ የሆነ የሚመስለው፤ ማየት የተሳነው የአራት ኪሎ አውደልዳይ ነው።]
 • ሰማይ የተዘገባቸው: [የሰው አገር የድንጋይ ክምር/ተራራ በመሳለም መንግሥተ ሰማያት መግባት ይቻላል! ብለው የሚያምኑ ከሆነ ብቻ “ማኅበረ ቅዱሳንን” ይጎብኙ። “ማኅበረ ቅዱሳንን” ሲገቡ ሰማይ የተዘጋበት ማኅበረሰብ ምን እደሚመስል ያዩታል።]
 • መንፈሳዊ መገለጥ የሌላቸው: – [እንደ “ማኅበረ ቅዱሳን” ዓይነቱ ደረቅ]
 • ጽድቅን በራሳቸው ሚዛን የሚለኩ: – [የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ነጭ አልባሳት ለብሰው ሲያሸበሽቡ ያለ ሰው በመላዕክት የምስጋና አገልግሎት አይደነቅም።]
 • ህይወት በሚሰጠው በሀዲስ ኪዳን ትምህርት የማይመሩ: – [ለማኅበረ ቅዱሳን አዳኝ ከሆነው ከኢየሱስ ይልቅ መኖክሴ ይሁን ወታደር ማንነቱ በውል የማይታወቅ ማለትም ሲኖዶስ የማያውቀው “ሙሴ ጸሊም” የተባለ ታቦት ነው የሚቀርበው።]
 • ወግ አጥባቂዎች፤
 • ሰው ለመግደል ጾም ጸሎት የሚይዙ ነፍሰ ገዳዮች: – [መጽሐፍ “እግዚአብሔር ያዳናቸው፥ ከጠላቶች እጅ ያዳናቸው ይናገሩ” እንዲል “ማኅበረ ቅዱሳን” ነፍሰ ገዳይ ለመሆኑ እኔ ምስክር ነኝ።]
 • አፈ ወርቆች ልበ ደንዳኖች:
 • ኃይማኖተኞች: ዳሩ ግን ፍቅር ርህራሄ የሌላቸው አውሬዎች:
 • ለማወቅም ሆነ ለመማር ፍቃድም ሆነ ፍላጎት የሌላቸው ትምክህተኞች:
 • የመልካም ነገር ጸበኞች ነበሩ። አሁን በዘመናችን ራሱን በቁልምጫ የሚጠራ “ማኅበረ ቅዱሳንም” ይህን ይመስላል።

እንግዲህ ይህን ማንነታቸው በሚገባ ያየና የተገነዘበ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር ጌታ ደግሞ ምንም እንኳ በነሱ ቤት ለእግዚአብሔር የቆሙ ቢመስላቸው፣ ሰው ከሩቅ ሲመለከታቸውም የሚያስቀኑ ቅዱሳን ቢመስሉም ኢየሱስ ግን እውነተኛ ማንነታቸን ገልጾ ድርጊታቸው የሚያስከትልባቸውን ቅጣት አክሎ በማያሻማ ቋንቋ እንዲህ ነበር ያላቸው (በማቴዎስ 23፡ 1 – 36)፥

 • መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፤
 • በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፤
 • አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፤
 • ፍርድንና ምሕረትን፥ ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፤
 • በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፤
 • በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጥ ግን የሙታን አጥንት ርኲሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፤
 • የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፥ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና ወዮላችሁ! ሲል ካማረና ከተቀባ መቃብር [መቃብር፥ ምንም ውጩ ቢቀባ ቢያምርም በውስጡ የያዘው ግማቱ አገር የሚያስተው ብስባሽ አጥንት ነው!] ጋር ዛሬ ክርስትናን ከጨለምተኝነት አስተሳሰብ መለየት ያቃታቸው የማኅበሩ አባላት “ሰው ሀይማኖቱን ሲጠብቅ እንዴት አክራሪ ይባላል?” በማለት ሲጠይቁ  ስንሰማ ሊደንቀን አይገባም። ምን ነው? ቢሉ “ማኅበረ ቅዱሳን” እንደሆነ ማሰብ ያቆመ ዜጋ የተከማቸበት መካነ መቃብር ለመሆኑ አንስተውምና።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 15, 2013

Advertisements