ማን ይሁን እውነተኛ፡ ኢሳት ወይስ አሰና?

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ጸበል ጻዲቅ በአምስት አምት አንድ ጊዜ (በምርጫ ሰሞን  መሆኑ ነው) እንደሚጋጋልና እንደሚንጫጫ ሁሉ የኢሳት ደስታ፣ ትርፍ፣ ዕድገትና ገበያ የሚደራና የሚሞቀው የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውን ለቅሶና ዋይታ፣ ኪሳራ፣ ስብራት፣ ሽንፈት፣ ድክመት፣ ውድቀት፣ ድቀት፣ ሰላም ማጣትና መታወክ ተከትሎ ለመሆኑ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው እውነታ ነው።

ታድያ ሰሙኑ ኢሳት የሚያውቅለት አጥቶ ነው እንጅ ግማሽ አካሉ ከድቶታል። ምን ነው? ምን ተገኘ? ይሉኝ ይሆናል። ኢሳትን ትልቅ ኪሳራ ውስጥ የዘፈቀ፣ ወሽመጡን የቆረጠ፣ ቆሌ መንፈሱ የገፈፈ፣ ደም ያስቀመጠና እርር ኩምትር ያደረገ “16 ህጻናት የሚገኙበት፤ 1 ቱኒዝያዊ፤ 6 – 8 ኢትዮጵያውያን፤ 509 – 511 የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኤርትራውያን በአጠቃላይ 518 ተሳፋሪዎች ጭና ከሊብያ ወደ ጣሊያን ያመራች ከ26 ሰዓታት ጉዞ በኋላ “ጀልቧ ውስጥ በተፈጥረው የእሳት አደጋ” 153 ኤርትራውያን 1 ቱኒዝያዊ ጨምሮ በአጠቃላይ 154 ነፍሳት በህይወት ሲገኙ እንደ ቢቢሲ ዘገባ እስከ አሁን ድረስ 311 የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኤርትራውያን ሬሳ ለማግኘት ተችለዋል።

ይህ አስደንጋጭ ክስተት መላ የዓለማችን ሕዝብ የሐዘን ድባብ ሲያለብስ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን መልካም ማየት የማይሆንለት ኢሳት ግን በተቃራኒው ክፉኛ አበሳጭተዋል አስቆጥተዋልም። ያለቁት ኢትዮጵያውን ቢሆኑ ኑሮ ኢሳት አጋጣሚው እንዴት ለፖለቲካ ፍጆታ ያውለው ይችል እንደነበር እያሰላሰለም “ያልቀረ ምን ነው ኢትዮጵያውያን ባደረገው!” ዓይነቱ ምዋርት እያሟረተ ከፈጣሪ ጋርም  ጸብ ውስጥ ገብተዋል።

ኢሳትም አለ፥ 

ESAT - mouthpiece of Shaibia

“ሰሙኑ በጣሊያንዋ የወደብ ከተማ ላምፔዱዛ ካለቁት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጋር በተያያዘ ዓለም እየተነጋገረ ይገኛል። በርካታ የመገናኛ ብዙሐንም ትልቁ አጀንዳቸው አድርገው ትኩረት ሰጥተዉታል። በርካታ ኢትዮጵያውን በመሰደድ በመንገድ ላይ እየቀሩ ይገኛሉ” ይላል።

የኤርትራ የሬድዮ ጣቢያ አሰና ደግሞ ከሞት የተረፉ ትውልደ ኤርትራውያን በማግኘት እንደሚከተለው ዘግቦታል፥

Assena Vs. Esat

http://www.youtube.com/watch?v=mmgNyQusfoI ሊንኩን በመጫን ከሞት የተረፉ ኤርትራውያን የሰጡት ምስክርነት ያድምጡ!

ማን ይናገር የነበረ ፤ ማን ያርዳ የቀበረ!

በነገራችን ላይ  ውሎ አድሮ እውነቱ መገለጡ አይቀር የተፈጠረው አሳዛኝ እልቂትና ሞት ለመካድና ሌላ መልክ ለመስጠት የሞከረ ኢሳት ብቻ አይደለም። የኢሳት የንስሃ አባት የኤርትራ መንግሥት በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ በኩል ይህን አሳዛኝ ሁኔታ የገለጸው “ሕገ ወጥ አፍሪካውያን ስደተኞች” ሲል ነበር የገለጸው። ወደ አሰና የሬድዮ ጣቢያ ልመልሳችሁ።

ይህ የሬድዮ ጣቢያ (አሰና) በህይወት ከተረፉ ኤርትራውያን ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ለመረዳት እንደተቻለ ኢሳት ነገር እለጠጠና እየወጠረ ያለ አንዳች ጭብጥና ደረቅ መርጃ እንዳወራውና እያወራው እንዳለም ሳይሆን በሞት ጥላ ያለፉና ከሙት የተረፉ ኤርትራውያን እንደገለጹት የኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ6ና ከ8 እንደማይበልጥ አስረግጠው ይናገራሉ። “ነበሩ” ወይም “አሉ” የሚባሉ ኢትዮያውያን (በቁጥር ከ 6-8 ተብለው የተጠቀሱ) የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ለመኖራቸው ግን በተጨባጭ የተረጋገጠ ነገር የለም። እስከ አሁን ድረስ  በህይወት ከተርፉ 154 ሰዎች የሉም ሬሳቸው ከየተገኘ 311 ሰዎችም የኢትዮጵያ ሆነ የሶማሊያ ዜግነት ያላቸው ተሳፋሪዎች አልተገኙም።

ኢትዮጵያውያን ከተሳፋሪዎቹ መካከል ለመኖራቸው በተጨባጭ የተረጋገጠ ነገር እስከሌለ ድረስ “ሰሙኑ በጣሊያንዋ የወደብ ከተማ ላምፔዱዛ ካለቁት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጋር በተያያዘ ዓለም እየተነጋገረ ይገኛል። በርካታ የመገናኛ ብዙሐንም ትልቁ አጀንዳቸው አድርገው ትኩረት ሰጥተዉታል። በርካታ ኢትዮጵያውን በመሰደድ በመንገድ ላይ እየቀሩ ይገኛሉ።” የሚል የኢሳት ዘገባ ደግሞ ዜና ሳይሆን ፕሮፖጋንዳ ነው።  ለዛውም መልክና ለዛ የሌለው በህዝብና በሀገር ላይ የሚነገር እርግማንና ምዋርት ነው።

በበኩሌ አይደልም የስድስትና የስምንት አንድ ሰውም ቢሆን አለ አግባብ መሞት የለበትም ባይ ነኝ። የኢሳት ቁጭትና ምኞት ግን ወዲህ ነው። የኢሳት ፍላጎት የነበረው “በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የዓሳ ነባሪ ቀለብ ሆኑ!” ተብሎ በሰበር ዜና ሲነበብና ሐተታ ሲሰራበት ጆሮ የሚሞላና ስሜት የሚቀሰቅስ ዓይነት ሲሆን “በማኸከላችን ከ6-8 ኢትዮጵያውያን ነበሩ” ተብሎ የተነገረው የኢትዮጵያውያን ቁጥር ለኢሳት እጅግ አነስተኛ ቁጥር ነው። የኢሳት ከፍ ዝቅ ማለትም ሌላ ምንም ሳይሆን አሁንም “በማኸከላችን ከ6-8 ኢትዮጵያውያን ነበሩ” ተብሎ የተነገረው የኢትዮጵያውያን ቁጥር ለክስ፣ ለሰልፍና ለጭኸት የሚበቃ ሆኖ ስላላገኘው ነው። ጎበዝ! ኢሳትን ሐዘን ውስጥ የጨመረ ይኑሩም አይኑሩም “ነበሩ” ተብሎ የተነገረ “የኢትዮጵያውያን” ቁጥር ማነስ ነው። አወይ ኢሳት!

እግዚአብሔር የምዋርተኛ አፍ ይዝጋልን!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E mail: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 12, 2013

Advertisements