“ማኅበረ ቅዱሳን”፡ አገር በታኝ ትውልድ ገዳይ የጽንፈኞች መናገሻ ነው!

ሌላው ይቅር እኔ እስከማውቀው ድረስ፡ ጥርት ያለ ግብና ዓላማ የለውምና (አልነበረውምና) በኢትዮጵያ ውስጥ በፍጥነት ተነስቶ በተነሳበት ፍጥነት ያልከሰመ፣ እንደ ጥላ ታይቶ ላሽ ያላለ፣ ዝናብ እንደሌለው ደመና አንዣቦ ሲያበቃም ብን ብሎ ያልጠፋ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉልበት ያልበላ ጊዜያዊ እንቅስቃሴ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት ለመግፈፍና በአንጻሩ ደግሞ የአንድ ብሔር ፍጹም የሆነ የበላይነት ለማንገስ በሚደረገው መላላጥ ሁሉ ያልተሞከረ ወይም መጠቀሚያ ያልሆነ የማኅበረሰብ ክፍል (እንቅስቃሴ) የለም። አንዳቸውም ውጤት አላስመዘገቡም እንጅ ሁሉም ነገር ተመክሮዋል። በከፈተኛ ተቋማት የሚደረገው ትንኮሳና ግርግር፤ ጎሳን ያማከለ ሊነሳ የሚፈለገው ግጭትና ትርምስ፤ ኃይማኖታዊ ተቋሞች በሽፋንነት መጠቀምና ሌሎች በርካታ መንገዶች ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው።
እስልምና የራሱ አጀንዳ ይዞ ሲነሳ የእኛዎቹ (ሳይዘሩ ማጨድ ሳይቀቡ መንገስ የሚያምርባቸው ፖለቲከኞቻችን) ደግሞ ከየትም ከትም ተጠራርተው “ድምጻችን ይሰማ!” እንደ ጀልባ ሲንጠላጠሉበት ጀልባዋ ሰጠመች። የዋልድባ ጉዳይም  እንደዚሁ “የስኳር ፋብሪካ በትግራይ ክልል መተከል የለበትም!” የሚለውን ስውር አጀንዳ “ቤተ ክርስቲያን ተደፈረች!” የሚል ሽፋን ተሰጥቶት ሲጮኽና እሳት ለማያያዝ ሲሞከር ይህም በሚገርም ሁኔታ ሳይሰምር ቀረ። አሁን ደግሞ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተዋልና የሞተውን እባብ “ጸበል” ረጭተን ለምን ግርግር ፈጥረን ህልማችንን እውን አናደርግም (ምኒሊክ ቤተ መንግሥት አንገባም!)” በሚል ስሌት በነጻ ፕሬስና በጋዜጠኝነት ስም ነገር ፍለጋ “ማኅበረ ቅዱሳን ይቅደም!” የሚል መፎክር ተይዞ ዘመቻ ተጀምሯል።
ለመሆኑ “ማኅበረ ቅዱሳን” ማን ነው? በማንና እንዴትስ ተመሰረተ? ዓላማውና ግቡስ ምንድ ነው? መንፈሳዊ ካባ የተላበሰና በስም ያማረ በቤተ ክርስቲያን ሥር እንደ ማኅበር ለመደራጀትም ሆነ ራሱን ችሎ ለመቆም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት አለው? የዚህ መሰሪ ድርጅት ህቡእ የፖለቲካ ተልዕኮውስ ምን ይመስላል? ለሚሉና ሌሎች በርከት ያሉ “በማኅበረ ቅዱሳን” ዙሪያ ሊያነሱት የሚችሉት ጥያቄ በበቂ ሁኔታ መልስ ያገኙ ዘንድ ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ ይጫኑ [https://salsaywoyane.files.wordpress.com/2013/10/assocaition-of-saints-or-association-of-the-davil.pdf]

ልዩ ማስታወሻ፥

መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኘት በምድሪቱ ሥር እየሰደደ የመጣውን የኃይማኖት ጽንፈኝነት በማስመልከት ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ እኔም መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ ሳይሆን እንደ አንድ ዜጋ ጽንፈኝነትንና ጠባሳውን፤ በተጨማሪም አንድ ራሱን “ክርስቲያን ነኝ!” ብሎ የሚጠራ አማኝ/ግለሰብ ሆነ ድርጅት ሌላ ድብቅ አጀንዳ ከሌለው በስተቀር ከጽንፈኝነት ጋር ምንም ዓይነት ክፍልም ሆነ ሕብረት እንደሌለው ጽንፈኝነት ጸረ ክርስትና እንቅስቃሴ ለመሆኑ ለማመላከት ከሥነ መለኮት ዕይታ “«አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚለው አባባል “ሕገ መንግሥት” ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስትናም ላይ የተቃጣ የጸረ ክርስቶስ ሃሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው!” በሚል ርዕስ እ.አ.አ ሚያዝያ 2012 ያዘጋጀሁት ጽሑፍ  ሆኖ በወቅቱ በዳያስፖራ አከባቢ የኢትዮጵያ ጉዳይ ከማንም በላይ ይመለከተናል ለሚሉ የድረ ገጽ ባለቤቶች ለንባብ ያበቁት ዘንድ ብልከውም አንዳቸውም የተላከላቸው ጽሑፍ ለንባብ ያበቁት ዘንድ አልደፈሩም። ይህ ጽሑፍ “ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ ‘ማህበረ ቅዱሳን’ ይሆን?” በሚል ርዕስ በተመስገኝ ደሳለኝ የተጻፈው ጽሑፍ ላስነበቡን ድረ ገጾች በሙሉ ተልኳል።

ሐተታ፥ 

የምዕራቡ ዓለም የዕድገትና የስልጣኔ ምስጢር በማውሳት ሐተታዬን ልጀምር። ለብዙዎቻችን ግልጽ እንደሆነ የምዕራቡ አለም ፖለቲካ ከተቀረው የዓለማችን ክፍል የሕዝብ አስተዳደር የተለየና የላቀ የሚያደርገው ቢኖር የፖለቲካ መሪዎች የሃሳብ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በሚደርሱት የጋራ ውሳኔ፣ አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ለመሆኑ አያከራክርም። ለምሳሌ ያክል “የዲሞክራሲ” ተምሳሌት መሆንዋን በሰፊው የሚነገርላት ልዕለ ሃያልዋ ሀገረ አሜሪካ የወሰድን እንደሆነ በተለይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በየትኛውም መስክ ያለ ተቃናቃኝ በኢኮኖሚውም ሆነ በፖለቲካው መድረክ የበላይነትዋን እንደያዘች የመዝለቅዋ ምስጢር ስልጣን ላይ የሚወጡትም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉትን የፖለቲካ መሪዎች ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ውጤት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። ይህ ማለት ዲሞክራትም ይሁን የሪፐብሊካን ፓርቲ አቀንቃኝ ሀገራቸው አሜሪካ በዋናነት ልትከተለው በሚገባት ፖሊሲ ላይ የጎላ ልዩነት ቢኖራቸውም የአሜሪካን ሉዓላዊነት እንዲሁም የአሜሪካ ሕዝብ ጥቅም የመጣን እንደሆነ ግን አንዱን ከሌላውን መለየት ፈጽሞ አይቻለንም። ሀገራዊ ጥቅም በተመለከተ ዲሞክራቱም ሪፖብሊካኑም አሜሪካዊ ነው!! እናማ ከየትም አቅጣጫ ቢመጡ ይህ ጽሐፍ ሲያነቡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በሰከነ መንፈስና በተረጋጋ ልብ ያነቡት ዘንድ ስጠይቅ በአክብሮት ነው።
መዋቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በወቅቱ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ካደረግዋቸው ንግግሮችና ከሕዝብ ተወካዮቹም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል ሃይማኖትን በማስመልከት መንግስታዊ ትንታኔአቸውና አቋማቸውን ለፓርላማው ግልጽ አድርገዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ማህበረ ቅዱሳን” ከአልቃይዳ ጋር በማመሳሰልም ገልጸውታል። እንግዲህ ይህን አገላለጽ/ንግግር ያዳመጠ ሰው አልቃይዳ ማለት ደግሞ ማን ነው? ምንስ ማለት ነው? ብሎ የሚጠይቅ አዋቂ ሊኖር እንደማይችል አምናለሁ።
አልቃይዳ በብዙሐን የንጹሐን ዜጎች ደም ተጠያቂ: በደም የተነከረ መታወቂያ ያለው: መሰረተ ልማቶችን በቦንብ የሚያጋይ: በአጠቃላይ በንጹሃን ሰዎች፣ በልማት ተቋማት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ንብረቶች ላይ ያነጣጠረ የሽብር ጥቃቶች የሚፈጽም ጸረ ልማትና በግርግር የሚያምን ሃላፊነት የጎደለው ሃይል ነው በአንጻሩ ደግሞ “የቅዱሳን ማህበር” ሲል ራሱን በቁልምጫ ቋንቋ የሚጠራ:
  • ለነውሩ መንፈሳዊ ካባ ያጠለቀና የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ፥
  • ታቦት ተቀርጾለት አምልኮ ብቻ የቀረው፥ 
  • በኢየሩሳሌም በሶሪያ … የሚገኘን የተቀደሰ ተራራ ነው እያለ ተራራ እያሳለማ ሲዘርፍና የአማኞች ኪስ ሲያራቁት የኖረ፥
  • ላለፉት ሃያ ዓመታት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስም ከእምነትዋ ተከታዮች አልፎ በሀገርና በትውልድ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆና ተቀምጦ ይሄ ነው ተብሎ በቀላሉ የማይገመት የአገር ሀብትና ንብረት በሕገ ወጥ መንገድ ስያግበስብሰና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሲዘርፍ እዚህ የደረሰ፥
  • በብዙዎች የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ልጆች ደም የተጨማልቀ ነፍሰ ገዳይ፥
  • ከቤተ-ክርስቲያን አልፈው ለሀገር የሚተርፍ እውቀት ያላቸውና በጥበብ የተሞሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለስደትና ለግዞት ህይወት የዳረገ፣ ሀገር ወልዳ እንዳልወለደች የወላድ መሃን ያደረገ፥
  • የህልውናው ያክል ጸበኛ፣ አልታዘዝ ባይና አመጸኛ ትውልድ በማፍራት አቻ የማይገኝለት፥
  • በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ታሪክ ምእመናን ከመሪዎች፣ አባቶች ከልጆች ጋር እንደ አንድ አካል መደማመጥ ይሳናቸው ዘንድ የአለመግባባት መንፈስ ያስተጋባ፥
  • የተለያዩ ያማሩ ስሞች ያሏቸው ድረ ገጾች በመክፈት በቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጭምር ሳይቀር ጦርነት የከፈተ፥
  • ለምንም ለማንም በማይበጁ ያልተጠኑና ቤተ ክርስቲያን በሕግ የማታውቃቸው እንግዳ ትምህርት በማሰራጨት ሃይማኖትን የሚበርዝ፣ ትውልድን የሚያደነዝዝ ሰላቢ ነው።
በአጠቃላይ “ማኅበረ ቅዱሳን” ክርስቲያናዊ ድርጅት ሳይሆን ጸረ ክርስቶስ ወንጌል የተደራጀ አጽራረ ጽድቅ፤ መከፋፈልንና ሁከት እንደ አጀንዳ ቀርጾ ነውጥን በመፍጠር ምኞቱን የሚያሳካ ሀገር በቀል የጥፋት ተልእኮ ያነገተ ጽንንፈኛ የማይገልጸው አውዳሚ ነፍሰ ገዳይ ማኅበር ነው።

እንደ “ማኅበረ ቅዱሳን” ያለ በኃይማኖት ሽፋን

ህቡዕ የፖለቲካ አጀንዳ የሚያራምዱ ጽንፈኞች መዋጋት የዜጎች ሁሉ ግዴታ ነው!

ራሱን “ማኅበረ ቅዱሳን” ሲል የሚጠራ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጉያ ላይ ተወሽቆ በመንፈሳዊነት ስም ስለ ተቋቋመው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው መሰሪ ድርጅት በማስመልከት መንግስት የሀገርና የሕዝብን ሰላም የመጠበቅ ግዴታው ነውና በመግቢያዬ ለመግለጽ እንደሞከርኩት መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው ባደረገሩት ንግግር ላይ የሰይጣን ማህበር “ማህበረ ቅዱሳን” ለመግለጽ የተጠቀሙበት አገላለጽ እርምጃው ሀገራችንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ማእከል ያደረገ እስከሆነ ድረስ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የተናጋሪው ሃሳብና አቋም ሙሉ በሙሉ በመጋራት አንኳር አንኳር ነጥቦችን በማተኮር እንደሚከተለው ሐተታዬን ይዜ ቀርቤአለሁ::
መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በተለያዩ ሃይማኖቶች የጽንፈኝነት ምልክቶች መታየታቸውን አውስተው በምሳሌነት ከጠቀሱት መካከል በአዲስ አበባ የተከበረውን የጥምቀት በዓልና  የማኅበረ ቅዱሳን ጸረ ሕገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው የገለጹት በእንዲህ ዓይነት መልኩ ነበር “ጥምቀት ላይ ከነበሩ መፎክሮች አንዱ «አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚል  ነው::” የማኅበሩ አፍራሽና ጸረ ሕገ መንግስታዊ ድርጊት ሲያስረዱም ምክንያታቸው እንደሚከተለው አቅርበዋል «አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚል ሕገ መንግስት የለንም። አንድ ሀገር የፈለገውን ዓይነት ቁጥር ያለው ሃይማኖት ነው ህገ መንግስቱ የሚለው” ሲሉ የመንግሥታቸው አቋም ግልጽ አድርጓል። እዚህ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ብቻ ጠቀሱ እንጂ “ማህበረ ቅዱሳን” የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ሰላምን የሚፈታተን: የሃይማኖት ነጻነትን የሚጻረር: የዜጎች ሰብዓዊ መብትን የሚጋፋ አቋሙን የሚያንጸባርቅባቸው አባባሎችና ትምህርቶች በርካታ ናቸው።

ይቀጥላል

በክፍል ሁለት፥ “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚያራግባቸው ቁንጽል መፈክሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ፥ 

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 11, 2012

Advertisements