አንዳርጋቸው ጽጌ ነፈሰ ገዳይ ነው!

የአገሬ ሰው ሲተርት “ከአህያ የዋለች ጊደር … ” እንዲል “የአውሮፓ ኑሮአቸው ትተው ወደ ኤርትራ ያቀኑ” እየተባለ መለከት የሚነፋላቸው ነጻ ያልወጡ “ነጻ አውጪ” አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዛቸው ልብ ብሎ ያስተዋለ ሰው እርር ጥብስ ብለው ሳሉ የምያስይዋት የውሸት ፈገግታ፣ ጥራዝ ነጠቅ የቃላት አጠቃቀም፣ ሽምጠጣ፣ አቀማመጣቸው ሳይቀር ደህና አድርገው መምህራቸው የሲዖል ፍላስፋው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ወደ መምሰል እየተጠጉ ለመሆናቸው ማስተዋሉ አይቀርም።

Lampedusa_coffin_kids-500x297

“በጣም ቀላል እኮ ነው! የትም አገር ላይ እኮ ድሃ የመጨረሻው ድሃ የሚበላ የሚጠጣ በሌለበት አገር ላይም ቢሆን ሁሌም የሚዘረፍ ነገር አለ። ከዛ ላይ የበለጠ መዝረፍ ስትጀምር የበለጠ ሕዝቡን የምታሰቃይበት ሁኔታ ይመጣል እንጅ የሚዘረፍ ነገርማ መቶ ሺህም ትሁን አንድ ሚሊዮንም ዶላር የሚዘረፍበት ሁኔታ ሁሌም አለ በአንድ አገር ላይ። ከፈለግክ ግን በደንብ መዝረፍ ከአንድ ቤት ውስጥ ይዘረፋል እንኳን ከአንድ አገር።” አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ይህን ቃል የተናገሩት ሙስናን አስመልክተው በኤርትራ ምድር ይቅር በሙስና የሚጠረጠር ባለ ሥልጣን ሊኖር “ሙስና” የሚል ቃል በራሱ በኤርትራ መዝገበ ቃላት እንደሌለና እንደማይታወቅ፤ የህግደፍ ባለ ሥልጣናት ለአገራቸውና ለሕዝባቸው የተሰጡ ብጹአን መሪዎች መሆናቸው፤ የሻዕቢያ “እንከን የለሽ ማንነት”፣ “ጽድቅና” “ቅድስና” ለመግለጽ አስበው በተቃራኒው እውነተኛ የህገደፍ አረመንያዊ፣ ፋሽሽታዊና ሰው በላ ማንነት እንዲሁም የኤርትራ ሕዝብ በአሁን ሰዓት የሚገኝበት ለጠላት የማትመኝለት አሰቃቂ ሁኔታ ምንጭ ለዓለም ሕዝብ ምስክርነታቸው የሰጡበት አጋጣሚ ነበር።

በነገራችን ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መንፈሳቸው ተነሳስቶና ነቃ ብለው ስለ መዝረፍ በሚገርም አገላለጽ ሰፊ ማብራሪያ ሲሰጡና ሲናገሩ የሰማ ሰው ባይሆን ሰውየው “በአሥር ሺህ” የሚቆጠር የማስተምረውና የማሰለጥነው ወታደር አለኝ ሲሉ የገለጹት አለኝ የሚሉት ወታደር ድል የቀናው ዕለት እንዴት መዝረፍ እንዳለበት የሚያሰለጥኑ ማጅራት መች መሆን አለባቸው ብሎ ሳይጠረጥር አይቀርም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ አንድ ሁላችንን የሚያስማማ ደረቅ እውነት ተናግሯል። “የበለጠ መዝረፍ ስትጀምር የበለጠ ሕዝቡን የምታሰቃይበት ሁኔታ ይመጣል ሲሉ እንደ ተናገሩት። በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ባለ ሥልጣናት ለዓለም መሪዎች ምሳሌ መሆን የሚችሉ በመልካም ሥነ ምግባር የታነጹ ብጹአን ናቸው! ሲሉም ቀድተውናል፤ ጥያቄው፥

  • የኤርትራ ወጣት ቢደላው ይሆን እንዴ ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት አገሩን ጥሎ እየኮበለለ ያለው?
  • ሴቶችና ወንዶች ኤርትራውያን የህግደፍ አስተዳደር ቢመቸው ይሆን ወይ በሲና በርሃ ልባቸውና ኩላሊታቸው እያስረከቡ የሚገኙ?
  • የኤርትራ ህዝብ ቢደላው ነዋ በኢጣልያ ላምፔዱዛ (ደሴት) በባህር ዳርቻ እንደ ተንሳፎ ሲያበቃ እንደ ባህር ዓሣ እየተለቀመ ያለው? 
  • የኤርትራ ህዝብ ጥጋብ ቢያንቀው ነዋ እንደ ፈርዖን ሠራዊት ሬሳው በባህር ዳርቻ እየተዘፈዘፈ ያለው?
  • የኤርትራ ህዝብ ቢመቸው ነዋ ድፍን ዓለም እያነጋገረ የሚገኘው?
  • በኤርትራ ምድር የመቃብር ቦታ ቢታጣ ነዋ ኤርትራውያን አገር አርቀው እየተቀበሩ ያሉ? በማለት አንዳርጋቸው ጽጌ በጥያቄ ማጣደፋችን አይቀርም።

መጽሐፍም ሲናገር  “ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል”  እንዲል በሲና፣ በሱዳን፣ በግብጽ፣ በሊብያ … የተበተነና እየሞተ ያለ የኤርትራ ሕዝብ “ደስታው መግለጹ ይሆን ወይ?” በማለት በድጋሜ አንዳርጋቸው ጽጌ በፍርድ ወንበር ፊት አቁመን ማናዘዛችን አንተውም። ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ግን የአቶ አንዳርጋቸው ምላሽ “የበረራ ሰዓቴ ስለ ደረሰ መሄድ አለብኝ!”  በማለት ረግጠውን እንደሚሄዱ እርግጠኛ ነኝ።

አንባቢ ሆይ! አቶ አንዳርጋቸው “የበለጠ መዝረፍ ስትጀምር የበለጠ ሕዝቡን የምታሰቃይበት ሁኔታ ይመጣል” ሲሉ እንደ ተናገሩት የኤርትራ ሕዝብ ስቃይና መከራ አይተው የህግደፍ ባለሥልጣናት ማንነት በማስመልከት የሚሰማዎት ይናገሩ ዘንድ ቢጠየቁ ግለጽ የሆነ ምስል ይኖሮታል የሚል እምነት አለኝ። ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ግን በሰው ሐዘንና ህመም መሳለቅ፡ መቀለድና መቆመር የሚያምርባቸው እንደ እነ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያለ ከእውነት ጋር ትውውቅ የሌለው መንዳቢ፣ በሰው መቃብር ላይ ቤቱ የሚገነባ አረመኔ፣ በንጹሐን ደም የተጨማለቀና ያበጠ ነፈሰ በላ፣ ሰብአዊነት ያልፈጠራቸው ግለስቦች ናቸው እንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመምራት እየተውተረተሩ ያሉ። በህግደፍ አመራር ደስታውን የገለጸ አንዳርጋቸው ጽጌ ነፍሰ ገዳይ ነው! ታድያ ሀገርዎንና ህይወትዎን ከቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች የመጠበቅ ግዴታ እንዳለቦት አውቀው በንቃት ይቆሙ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሬን ሳስተላልፍ በአክብሮት ነው።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

Oct 09, 2013

Advertisements