ሦስቱ ጣምራ ጠላቶች! (ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ፣ ግንቦት 7ና ኢሳት)

እንደው ለነገሩ ነው እንጅ ኢሳት ቃለ ኢሳይያስ አፈወርቂ ማለትም ባሳለፍነው ሳምንት የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ከሀገር ውስጥ (ከኤርትራ) የዜና አውታሮች የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በማስመልከት የሀገራችን የኢትዮጵያ ታሪካዊ አመጣጥና አመሰራረት አስመልክተው “ኢትዮጵያ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረች ሀገር ናት። ያም ሆነ ይህ ሌላ ሰው የፈልገው ሊል ይችላል ይህች ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀው ሀገር ግን ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የመጣ የዓለም ሥርዓት ሥርዓቱ ራሱ በሚመርጣቸው ገዢዎች ይጠቀምባት ዘንድ የፈጠራት ኃይል ናት።” በማለት ሉዓላዊት ሀገር ሲዘነጥሉና በማንነቱ ክቡር የሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲዋርዱ በነጋ በጠባ ቁጥር “ኢትዮጵያዊ አማራጭ ድምጽ ነኝ” ሲል የሚለፍፈው ኢሳት ቃለ ኢሳይያስ አፈወርቂ በመቃወም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር ቆሞ ይሞግታል፤ የጣቢያው የጀርባ አጥንት፣ ደጀን፣ አለኝታና ባለውለታ የሆኑ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ መያዣ መጨበጫ የሌለው የዕብደት ቃላቸው በማውገዝ ዜና ይሰራል ሐተታ ያትታል ብየ አልጠብቅም። ኢሳት የግንቦት ፯ ልሳን እንደመሆኑ መጠን ይህን ያደርጋል ብዬም አይደለም በውኔ በሕልሜም አላስበውም። 

ኢሳቶች ይህን ያደረጉ ዕለት ደግሞ ይሄ አውሮፓና አሜሪካ ተቀምጦ ወሬ መሰልቀጥ የለመደ ቅጥረኛ ሁሉ ወደ ድስት አጠባና አልጋ የማንጠፍ ሥራ እንደሚሰማራ  አልጠራጠርም። እስቲ አሁን እኔን ለማሳፈር እንኳ አንድ ቢሉን ምን አለበት? (አንባቢ ሆይ! ጸሐፊው በስራ ክቡርነት አጥብቀው ያምናሉ። በየትኛውም የስራ መስክ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ቤተ ሰቦቻቸውን ለሚረዱና ለሚደጉሙ ወንዶችና ሴቶች ኢትዮጵያውያን ከልብ የሆነ የላቀ ክብር አላቸው። ለመድረስ የተፈለገው ዘራፊዎችን እንጅ የሥራ ክቡርነትን ለማቃለልም አይደለም።)

በግርድፉ ኢሳት ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ ግን ጸሐፊው ሲመልሱ ኢሳት ማለት የኢትዮጵያ መልካምነት መየት የማይሻ፣ መልካም በጎ የሆነም ነገር የማይገኝበት ይልቁንስ ነውርን በማውራት የተካነ፣ ከምድሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ግንባር በመፍጠር የጠላቶችዋ ዓይን ጆሮና አፍ በመሆን ኢትዮጵያን ለመበታተንና ሕዝቦችዋም እርስ በርስ ለማባላት፣ ለማጨራረስና ደም ለማቃባት ምድሪቱም የደም መሬት ለማድረግ ታጥቆ የተነሳ የጠላት መሳሪያ ነው። 

የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሉዓላዊት አገር ሀገረ ኢትዮጵያ የገሸለጡበትና ምድሪትዋ የሸለቱበት ቃል ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ (11. 16 ጀመሮ) በመጫን ያደምጡ ዘንድ ተጋብዘዋል። http://www.youtube.com/watch?v=MoU7vG3bCBQ

 ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

Sep. 15, 2013

Advertisements