አገር ስትዘነጠል አርቲስት አሉባይ በየነ ምን አለ?

የሰው ዳህጸ ልሳን እየጠበቀ እንደ አውራ ዶሮ ከአገር አገር ከመንደር መንደር እየዞረ ያለ እውቀት በመጮህ የሚታወቀው በዚህ አሳፋሪ ድርጊት ተክኖበትም  ከፍተኛ ስምና ዝናም ያተረፈ አርቲስት አሉባይ በየነ ወዴት አለ? የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ባሳለፍነው ሳምንት ከሀገር ውስጥ (ከኤርትራ) የዜና አውታሮችና የመገናኛ ብዙሐን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በማስመልከት የሀገራችን የኢትዮጵያ ታሪካዊ አመጣጥና አመሰራረት አስመልክተው “ኢትዮጵያ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረች ሀገር ናት። ያም ሆነ ይህ ሌላ ሰው የፈልገው ሊል ይችላል ይህች ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀው ሀገር ግን ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የመጣ የዓለም ሥርዓት ሥርዓቱ ራሱ በሚመርጣቸው ገዢዎች ይጠቀምባት ዘንድ የፈጠራት ኃይል ናት።” በማለት ሉዓላዊት ሀገር በሌላ አገር መንግሥት አንደበት ስትዘነጠል፣ ስትደፈርና ስትሰደብ ሕዝቦችዋም ሲገሸለጥ፣ ሲሸለትና ሲዋረድ አርቲስት ታማኝ በየነ ምን አለ?

በተለያዩ ጊዜያት አርቲስት ታማኝ በየነ ዓብዪ ርዕስ አድርጌ ስጽፍ አንድ ሊታወቅልኝ የምፈልገው ነጥብ አለ። ይኸውም፥ አርቲስት ታማኝ በየነ ቁምነገር ያለው፥ አዋቂ፥ የመፍትሔ ሰው ሆኖ ሳይሆን ግልሰቡ ከሚያለማው ይልቅ የሚያጠፋው፣ ከሚተክለው ይልቅ የሚነቅለው፣ ከሚበጀው ይልቅ የሚፈጀው ስለሚያመዝና ራሱን በስራዎቹ ቆም ብሎ ያይ ዘንድ ለመሆኑ ይታወቅልኝ ዘንድ እወዳለሁ። እንደው እኔ የምለው ግን በዙሪያው የከበቡት ሰዎች ምን እየሰሩ እንዳሉ አሳስቦት ቆም ብሎ የሚጠይቅ አንድ ሰው የለም ወይ? የተማረ ያልተማረ ይጋልብብን? አሁንስ “በራሳችን” ማፈር ይገባናል!

የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሉዓላዊት አገር ሀገረ ኢትዮጵያ የገሸለጡበትና ምድሪትዋ የሸለቱበት ቃል ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ (11. 16 ጀመሮ) በመጫን ያዳምጡ ዘንድ ተጋብዘዋል። http://www.youtube.com/watch?v=MoU7vG3bCBQ 

Advertisements