አበበ ገላው ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሰጡት መልስ

ዕድሜና ጤና የሰጠው ሰው የማያየውና የማይሰማው ነገር የለም። ጠቢቡም “ጕድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል ድንጋይንም የሚያንከባልል ይገለበጥበታል።” እንዲል (ምሳሌ 26: 27) በሽብር፣ በሁከት፣ በነውጥ፣ በጦርነትና በደም መፋሰስ ለውጥ ማምጣትና አገር ማልማት ይቻላል ብሎ የሚያምን እንዲሁም የትግራይ ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ይህን ሕዝብ ፈጅቶ በማስፈጀትም ወደ ሥልጣን ለመውጣት የሚያስችለው ድብቅ የፖለቲካ ፕሮግራም ቀርጾና ዘርግቶ የሚንቀሳቀስ ቀቢጸ ተስፋ ኃይል ልሳኑ በሆነው በፈጠራ ወሬ፣ በበሬ ወልደ ድርሰትና በአሉባልታ ሰፊውን ሕዝብ ማወናበድ ማደናገርና በማጭበርበርም የተጠመደ መቀመጫው አሜሪካና አውሮፓ ያደረገ የፕሮፖጋንዳ ማዕከል ኢሳት ትናንት የመዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ ዘመድ ተጨባጭ የኑሮ ሁኔታ ለማሳጣት የተቋሙ ቅጥረኖች የለፈፉበትን ምራቅ ሳይደርቅ ዛሬ ደግሞ የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂን ለማወደስ ለመቀደስና ከፍ ከፍ ለማድረግ ብቅ ያሉ የጣቢያው ባለቤት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቀደም ሲል መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለማሳጣት ታስቦ በአቶ አበበና በአቶ ሲሳይ አጌና የተገነባ ግንብ በጠራራ ጸሐይ ሲንዱት ሲያፈራርሱትና ሲያፋልሱት ለማየት ተችሏል። በነገራችን ላይ ግለሰቦቹ አንድ ቋንቋ መናገርና መደማመጥ ተስኗቸው እንደ ባቢሎን ሰዎች ነገር ሲቀላቅሉ የምናገኛውቸውና የምናያቸው ነገሩ እንዲሁ በድንገትና በአጋጣሚ የሆነ/የተከሰተ ጉዳይ ሳይሆን ጠቢቡ በተመሳሳይ የጥበብ መዝገቡ “ጠላትነቱን በተንኰል የሚሸሽግ ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል” ሲል እንደገለጸው እንዲሁ ነው።

የጽሑፉ ዓላማ: 

የግንቦት 7 የፕሮፖጋንዳ ማዕከል የሆነው ኢሳት የሳይበር ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ሠራተኛ አቶ አበበ ገላው የተባሉ ግለሰብ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “ያልተጠኑ ገጾች” በሚል ርዕስ ለለቀቀው የመዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ወንድምና እህት የኑሮ ሁኔታ የሚስያቃኝ ይዘት ያለው በምስል የተደገፈ የህይወት ምስክርነት በመቃወም የሰጡትን ቃል እንዲሁም የፕሮፖጋንዳ ማዕከሉ በበላይነት ከሚዘውሩ ልሂቃን መካከል አንዱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተባሉ ግለሰብ በቅርቡ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር በመወከል የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቅ ተክለ ስብእና ለማስተዋወቅ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን  “ከአስመራ” አሜሪካ ድረስ በመምጣት በተለይ የፕሬዝዳንቱ የደረሱ ሦስት ልጆች “ተጨባጭ ሁኔታ” በማስመልከት የሰጡትን ምስክርነት በሚደንቅ ሁኔታ አቶ አበበ ገላው መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በመቃወም ካደረጉት ቃል ጎን ለጎን በማስቀመጥ የዜጎች ዓይን ለመክፈት፤ በተጨማሪም መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በወንድም እህታቸው ያሳዩት አቋም “ሳዳምም እንዲህ ነበረ” ካስባለ እንደው በከፋ መልኩ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ሴትና ወንዶች ልጆቹ ማስተማር አቅቶት ልጆቹ በአስር ዶላር መሬት ለመሬት ሲርመሰመሱ ከመስማት የከፋ ነገር የለምና አቶ ኢሳይያስ እንዴት ከሳዳም በከፋ መልኩ ሳይገለጹ ቀርተው በአንጻሩ ግን አምልኮ ቀረሽ ውዳሴና ክብር ሊቸርላቸው ቻለ? በማለት መልስ ፍለጋ ለመጠየቅ ተጻፈ። አይመስሎትም?

የጽሑፉ ውሱንነት፥ 

የጽሑፉ አዘጋጅ አቋምም ሆነ ጽሑፉ በይዘቱ መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሴትና ወንዶች ልጆቹ እንዲሁም በወንድምና እህታቸው ያሳዩት አቋም በተመለከተ ምንም ዓይነት የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ሃሳብ አያንጸባርቅም። መጽሐፍ “ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን?” እንዲል መንታ የሆነው የኢሳት ምላስ ዓይኑን ከፍቶ የማየት ፍላጎችት ላለው ኢትዮጵያዊ በንጽጽር ለማሳየት ያለመ ብቻ ነው።

 ሐተታ: 

የመዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ወንድምና እህት

“Vs.”

የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ወንዶችና ሴት ልጃቸው ነባራዊ ሁኔታ፥

የመዋቹ ጠቅላይ ሚኒስተር ወንድምና እህት የሆኑ ሁለት ግልሰቦች ግለ ህይወትና የኑሮ ሁኔታ የሚያስቃኝ (የሚዳስስ) በምስል የተደገፈ ማስረጃ የተለቀቀ ሰሞን ከሞላ ጎደል የብዙሐኑ ዜጎች ቀልብ ሲስብና ሲገዛ በአንጻሩ ደግሞ በኢሳት ሰፈር ያስከተለው ፖለቲካዊ ኪሳራና የፈጠረው ራስምታት ለመገመት በሰው መቀመጫ ቃሪያ የመቀባት ያክል የተለቀቀው ቅኝት የፕሮፖጋዳ ማዕከሉ ቅጥረኞችና ባለቤቶች ቁጭ ብድግ ሲያደርግ መታየቱ በራሱ በቂ ከመቂም በላይ ነው ብዬ አምናለሁ።

እንግዲህ በማስቀደም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለማወደስና ለማድነቅ ሦስት የፕሬዝዳንቱ ልጆች የሚገኙበት ሁኔታ በማስመልከት የተናገሩትን እንዳነበብን በመቀጠል ደግሞ እንዲህ ያለ ቀልድ “የማይጥማቸውና የማይደላቸው” እንደው “ሳዳማዊነት ነው” ሲሉ የሚገልጹት የመልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል መልእክተኛ የሆኑት ማለትም በህልማቸው በአብሳሬ ምስራች ቅዱስ ገብርኤል በኩል “ሰማያዊ አጀንዳ” የተቀበሉ የአቶ አበበ ገላው ቃል ደግሞ በተከታይ እናነባለን።

የግንቦት ፯ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጽድቅ፣ መልካምነት፣ ፍትሐዊነት፣ ምሉኡነት፣ ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ያላቸው ታማኝነትና ቆራጥነት በዚህ መልኩ ነበር የገለጹት “በሌላ በሌላ ነገር የኤርትራ መንግሥት መሰንጠቅ መተቸት ትችላለህ ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ልጆቹ አስመራ ዩኒቨርሲቲ መግባት መቻል አቅቷቸው ፈተና ውጤት በቂ ስላላገኙ በአስር ዶላር በወር አገልግሎት እንደማንኛው ኤርትራዊ ነው የሚሰሩ። [አቶ ሲሳይ አጌና ውጭ አገር ሄደው አልተማሩም?] አንድም ልጁ ሱዳንም እንኳ አያውቅም። እንኳን ፈረንጅ አገር ሄዶ ለመማር ነው የምልህ ያለኸው። በሙሉ ልጆቻቸውን ሳዋ ልከው [የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ልጆች እዛው ኤርትራ ነው ያሉት] … ኤርትራ ትምህርት የተማሩት ኤርትራ ነው። ሳዋ እንደማንኛውም ሰው ተልከው ስልጠናቸውን ጨርሰው እዛ ሳዋ የሚባለው ቦታ ላይ ነው ፈተና የሚሰጠው ወደ አስመራ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ በጣም ጥቂት ቦታ ነው ዩኒቨርሲቲ ያለው ከፍተኛ ፉክክር ነው ያለው የፕሬዝዳንት ልጅ ስለሆኑ ግን ልዩ ተደርጎላቸው ልዩ አስተያዬትና መግቢያ ፈተና ዝቅ ብሎላቸው ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የሚደረግበት ሁኔታ ስለሌለ ሦስቱም ዩኒቨርስቲ የማይገቡ ልጆች ያልገቡ ልጆች ነው ያሉት።

ቀደም ብዬ እንደ ጠቀስኩት እንዲህ ያለ የሽፍጥ የስላቅና አደናጋሪ መንታ ምላስ “የማይደላቸው” አቶ አበበ ደግሞ አለቃቸውን አቶ አንዳርጋቸው እንዲህ ሲሉ ያሳጣሉ፥ ለምሳሌ “የወንድማቸው ሳንቡሳ መሸጥ የእህታቸው ጠላ መሸጥ” የሚለውን የአቶ አበበ ገላው ቃል “የፕሬዝዳንቱ ልጆች ስንፍና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች አለመብቃት” በሚል ቃል ብንተካው “ይሄ የሚያሳየው የአቶ ኢሳይያስ ጥንካሬ አይደለም። አቶ ኢሳይያስ ልጆቻቸውን በሚገባ ማስተማር የሚችሉ አቅም ያላቸው ሰው ናቸው። የገንዘብ አቅም አላቸው  ስልጣኑም ያላቸው ሰው ናቸው። ሊረዱ ይችሉ ነበረ ያንን አለማድረጋቸው እንደ ታላቅ ሰው የሚያስቆጥር አይደለም።” አቶ አበበ ንግግራቸው በምሳሌ ስያስደግፉም “ሳዳም ሁሴንም በተመሳሳይ ሁኔታ የቅርብ የሆኑ ዘመዶችን በድህነት እንዲኖሩ ያደረገበት ሁኔታ ነበር ይሄን ማድረጉ ሳዳም ሁሴን ታላቅ ሰው ሊያደርገው አይችልም። እንደዚሁ ሁሉ አቶ መልስ እህትና ወንድም በድህነት እንዲኖሩ ችላ ብለው መኖራቸው ታላቅነታቸው የሚያሳይ ነገር አይደለም ወደ ራሳቸው ማተኮራቸው ነው የሚያሳየው። ለሥልጣናቸው ሲባክኑ የቤተሰባቸውን ጉዳይ እንኳን በአግባቡ ለማየት የፈቀዱ ሰው እንዳልሆኑ ነው።” እንዲሉ አቶ አበበ አሁን አዚህ ቦታ ላይ በሳዳም ፈንታ ማንን እንደሚተኩልን ባላውቅም በነገራችን ላይ የሳዳም ቤተ ዘመድ ድሆች ነበሩ የሚለውን ነጭ ውሸት አቶ አበበ ገላው ከየት እንዳገኙት ባይታወቅም የሳዳም ሁሴን ወንድምና “እህት” ግን የጨረሱ ባለ ሃብቶችና ያለ ተቃናቃኝ የሀገሪቱ ቁልፍ ቁልፍ የስልጣን ቦታዎች የተቆናጠጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ማስረጃ ማስረዳት/ማቅረብ እችላለሁ። አንደኛ: ሳዳም ሁሴን ሴት እህት አልነበረውም ሁለተኛ: በአባትና እናታቸው የሚወለድ ወንድማቸው ገና በልጅነቱ በካንሰር በሽታ የሞተ ሲሆን በአባታቸው የሚወለዱ ሦስት ወንድ ልጆች የኑሮ ደረጃ እናንሳ ከተባለ ደግሞ  በቴሌቪዥን መስኮት እንዳየነው እንደ ጸጋዬ ዜናዊ በየመንገዱና በዬ ጠላ ቤቱ ሳንዱች እያዞሮ ሽጠው ቤተሰቦቻቸው የምያስተዳድሩና ኑሮአቸው የሚገፉ ዓይነት ጎስቋላ ሰዎች ሳይሆኑ ባርዛን ኢብራሂም አል ቲኽሪቲ የኢራቅ የደህንነትና የጸጥታ ቢሮ ዋና ዳይሬክተርና የወንድማቸው የሳዳም ሁሴን የቅርብ አማካሪ፤ ዋታባን ኢብራሂም አል ቲኽሪቲ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር፤ ሳባዊ ኢብራሂም አል ቲኽሪቲ ደግሞ ቀደም ሲሉ የጸጥታ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር መሪ ቀጥሎም የወንድማቸው የሳዳም ልዩ አማካሪ በመሆን ያገለገሉ ሰዎች ነበሩ።

ወረደም ወጣ አቶ አበበ ገላው ይህን ማለታቸውን ግን አይተዉም “ሳዳም ሁሴንም በተመሳሳይ ሁኔታ ልጆቹን ለከፍተኛ ተቋም ማብቃት ተስኖት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እንዲኖሩ ያደረገበት ሁኔታ ነበር ይሄን ማድረጉ ሳዳም ሁሴን ታላቅ ሰው ሊያደርገው አይችልም። እንደዚሁ ሁሉ አቶ ኢሳይያስ ልጆቻቸው በሚገባ ማስተማር አቅቷቸው ችላ ብለው መኖራቸው ታላቅነታቸው የሚያሳይ ነገር አይደለም። ወደ ራሳቸው ማተኮራቸው ነው የሚያሳየው። ለሥልጣናቸው ሲባክኑ  ልጆቻቸው ጉዳይ እንኳን በአግባቡ ለማየት የፈቀዱ ሰው እንዳልሆኑ ነው።” በማለት አለቃቸው አቶ እንዳርጋቸው ጽጌን አፍ ማስያዛቸው ነው።

የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቅ ልጆች እጅግ የወረደና ርካሽ የኑሮ ደረጃ ለመግለጽ ቃላት ሲቸገሩና ቋንቋ ሲያጥራቸው የሚስተዋሉ/የተስተዋሉ የተቻላቸው ያክልም ተናግረው እርካታ ያጡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነገሩን በናቅፋ መንዝረው ለማስረድ ሲሞክሩ ያሉት ይህንኑ ነበር “ተቀጥሮ የሚሰሩበት አምስት መቶ ናቅፋ ነው የብሔራዊ አገልግሎት አምስት መቶ ናቅፋ ማለት በአሁን ወቅት “ሪልይ” በልቅ የሆነውን ምንዛሬ ከወሰድከው አስር ዶላር ነው። ማንኛውም ኤርትራዊ ወጣት በዛ ደረጃ ነው እየሰራ ያለው እዛ አገር ላይ በዛ ደረጃ ነው የሚሰሩ ያሉት።” በአቶ አንዳርጋቸው ዋሾ ምላስና ወገበ ነጭነት ክፉኛ የተበሳጩ አቶ አበበ ገላው ደግሞ በፊናቸው ሰፋ ባለ መልኩ እንዲህ ይላሉ። (አቶ አበበ ገለው ለዚህ የሚሰጡት መልስ ሌላው አዳማቂ መሳይ ከበደ “እንዲህ ዓይነቱን ነገር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማስተላለፍ በተለይም ጠላ [ሲሸጡ እህታቸውን መታየታቸው ወንድማቸውም እንደዚሁ ሳንቡሳ ሲሸጡ መታየቱ] የሚለውን “የአንድ የሀገር መሪ ልጆች (የፕሬዝዳንት) ልጆች የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፍ አቅቶአቸው አስር ዶላር በወር እየተከፈላቸው በድህነት ተቆራምደው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ነው እየገፉ የሚገኙ ተብሎ ሲነገር” በሚለው ሲተካ ማለት ለምንድ ነው ያስፈለገው? አቶ መለስ/ኢሳይያስ ቅን እውነተኛ መሪ መሆናቸውን ለማሳየት ነው ወይስ ከዛ ያለፈ ነገር ይኖረዋል ብለህ ታስባለህ?” በሚለው  ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሚሰጡበት ወቅት ነበር።)

“ከዛ በተረፈ ምንድ ነው ለማስተላለፍ የተፈለገው መልዕክት እንግዲህ ሁላችንም እንደምናውቀው በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሚድያ ተቋማት አቶ መለስ/ኢሳይያስ በሚልዮን የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር በውጭ ባንኮች እንዳከማቹ የተቀመጠበት የተዘገበበት ሁኔታ ሁሉ እንዳለ እንውቃለን። እንግዲህ ይሄ የኢትዮጵያ/የኤርትራ ሚድያዎች አይደሉም የዘገቡት አለም ዓቀፍ ሚድያዎች ነው የዘገቡት ከየትም አምጥተው አይደለም ይህን የዘገቡት እና ያንን ለመሸፈን አቶ መለስ/ኢሳይያስ ኮራብት አይደለም በሙስና ሊጠረጠር የሚችል ስብእና ያለው ሰው አይደለም። እንኳን አይደለም ሌላ ይቅርና ቤተሰቦቹን/ልጆቹን እንኳን ረድቶ አያውቅም/በአግባቡ አላስተማረም የሚል ነው ያንን ትልቅ የሆነውን የኢትዮጵያ/የኤርትራ ሀብትና ንብረት እንደመዘበረ የሚነገረውን ዜና ለማስተባበልና ለማዳፈን የተደረገ ጥረት ነው ግን የሚሳካ አይደለም ምክንያቱ ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አንድ ሰው ኮራብት መሆኑንና ቤተሰቦቹን መርዳት አለመርዳቱን/ልጆቹን በአግባቡ ማሳደግና ማስተማርና አለማስተማር ሌላ ጉዳይ ነው። አንዳንዶች በራሳቸው ስልጣንና ሀብት ንብረት ላይ በጣም ስለሚያተኩሩ ልሎችን የማየት ዕድሉና ጊዜም የላቸውም። አቶ መለስም/አቶ ኢሳይያስም የኖርሩት/እየኖሩት ያሉት ህይወት ይሄ ነው። ምክንያቱም አምባገነን ስለሆኑ ሁል ጊዜ ስልጣን ከእጃቸው እንዳያመልጥ ሃያ አራት ሰዓት ሁሉም ነገር ሲቆጣጣሩ ሃያ አራት ሰዓት ሁሉን ነገር ሲከታተሉ የነበሩ/እየተከታሉ ያሉ ሰው ስለሆኑ እና ወደ ራሳቸው ያተኮሩ ሰው በመሆናቸው እንግዲህ በስብእናቸው አቶ መለስ/ኢሳይያስ የምናውቀው ምንድ ነው ከሳቸው በላይ ሰው ያለ የሚመስላቸው ሰው አይደሉም። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተንጸባረቀ አጋጣሚዎች እውነተኛ ስብእናቸው ራሳቸውን አዋቂ ታላቅ ሰው እንደ እሳቸው ያነበበ የለም በዓለም ላይ እንደሳቸው የሚያውቅ የለም ሌላው ሁሉ ከሳቸው በታች ነው። በዚህ ዓይነት ስብእና ነው የኖሩት/እየርኖሩ ያሉት። ምንም ዓይነት ቪድዮ ቢሰራጭ/አቶ እንዳልካቸው ጽጌ የፈለጉትን ቢሉ መሸፈን የማይቻለው ሐቅ አቶ መለስ/ኢሳይያስ አፈወርቂ አንባገነን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ኢትዮጵያውያንን/ኤርትራውያንን ለጭፍጨፋ ያዳረጉ ብዙ ኢትዮጵያውያንን/ኤርትራውያንን ለእስር በሀሰት ክስ እነ እስክንድር ነጋ/ፍስሃዬ ዮሐንስ ሁሉ በሀሰት ተከሰው ያልፈጸሙትን  ሽብር ሽብር ፈጠራችሁ ተብለው የታሰሩ/በ2004 ፕሬዝዳንቱ ከ Australian Broadcasting Corporation ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ ቃል በቃል “አላውቀውም” በማለት የሰጡት ቃል እንደተጠበቀ ሆኖ  በእስር በአሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ  ከዛ በላይ ደግሞ ምንም ዋጋ የሌለው ጦርነት ከኤርትራ/ኢትዮጵያ ጋር የተደረገ ጦርነት ሰማኒያ ሽሕ ሕዝብ ያለቀበት ጦርነት ሁሉ እሳቸው/አቶ ኢሳይያስ ተጠያቂና ኃላፊ የሆኑበት ጦርነት ነው። … እነዚህ እነዚህ እውነቶች በምንም ዓይነት ተረት ተረት/የአቶ አንዳርጋቸው አዳፍኔ ምስክርነት የሚሸፈኑ አይደሉም።”  ይላሉ

በነገራችን ላይ አቶ አበበ ገላው ስለ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቢጠየቁ የአቶ አንዳርጋቸው አቋምና አገላለጽ ይጋራሉ ወይስ አቶ አበበ ገላው የተጠመቁበት በጥቂቱ AI USA, AI London, HRW, CPJ, State Department, Freedom House ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚሉትን በመጋራት አለቃቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በመቃወም “አቶ ኢሳይያስ የመሰለ የለየለት ነፈሰ ገዳይ፣ አረመኔ፣ ፣ ሰው በላ፣ አንባገነን መሪማ በዚህ ምድር የለም ተፈልጎም አይገኝም።“ በማለት ይገልጽዋቸውና ይሞግቱ ይሆን? ለሚለው ጥያቄ በእውነቱ ነገር ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ሚዛናዊ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ፣ ገለልተኛና የሕዝብ ዓይንና ጆሮ የሆነ ሚድያ ማቋቋም ሊጠይቀን ነው።

ይቀጥላል 

በክፍል ሁለት፥

አቶ አበበ ገላው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ በተስተዋሉበት ቪድዮ መሳይ ከበደ እዛው በዛው ላነሳው የቤቱ የፈጠራ ጥያቄ አቶ ሲሳይ አጌና የሰጡት እርስ በርሱ የሚጋጭና የተመታታ መልስ እንዲሁም በድጋሜ አቶ ሲሳይ ባሳለፍነው ሳምንት ከበላይ አዛዣቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በነበራቸው ቆይታ ሻዕቢያን በማወደስና በመቀደስ እንደ ወትሮው ደግሞ ግልጽና በማያሻማ አነጋገር የትግራይ ሕዝብ የዘለፉበት በሕዝቡም ያላቸው ስር የሰደደ ጠላትነትና መሰረተ ቢስ ጥላቻ የገለጹበት ዓረፍተ ነገር ሰሚ ጆሮ ለማንቃት (አንባቢን ለማስታወስ) እወዳለሁ።

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Sep. 10, 2013

Advertisements