የኢሳት የንስሃ አባት – “Amnesty International” ማን ነኝ አለ

ሰው የቄስ ንስሃ አባት ሲጠራ እንጂ “የተሻለ ዓለም እንፈጥራለን” በሚል ፈሊጥ የተቋቋሙ እንዴትና በማን እንደተቋቋሙም በውል የማይታወቅ ዳሩ ግን ከተመሰረቱበትና ከተቋቋሙበት ዓላማ እጅግ ሩቅ መንገድ ተጉዘው ዓለምን እያወኩና እያተረማመሱ ያሉና የሚገኙ የባዕዳን ድርጅቶች በአናቱ ላይ ሰይሞ ያሉትን ሳይጨምርና ሳይቀንስ እንደ የገደል ማሚቶ የሚያስተጋባ፤ “Amnesty International” ስለ ኢትዮጵያ እንዲህ አለ (በአጠቃላይ የነጭ ዘር ያለበት እንዲህ አለ) በማለት ኢሳቶች ነውር ለማውራት እንዲህ የሚያጣድፋቸውስ ምን ይሆን? ባንዳነት! የሀገር ጥላቻ! ያሉ እንደሆነ አልተሳሳቱም።

የኢሳት ነገር እየሆነ ባለው ነገር መፍትሔ በመጠቆም ፈንታ ዛሬም “Amnesty International” “Ethiopian repression of Muslim protests must stop” በማለት ስጋቱን ገለጸ ሲሉ ሳይውል ሳያድር በዕለቱ http://www.youtube.com/watch?list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn&v=NPWQYggRBac ብለው ለማስተጋባት የቀደማቸው የለም። እኔምለው በአንድም በሌላም እየታመሰች ያለችው ሀገር እኮ የጠላት ሀገር አይደለችም። ምድሪቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት። ውይ! ላካ ኢትዮጵያ ማለት ለኢሳቶች የእንጀራ እናት ናት። የጭዋ ነገር ደግሞስ “ሰበር” ብሎ ለመጻፍ ሰራዊቱ “ሰ” መሆኑ ቀርቶ ንጉሡ “ሠ” የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው? ወይስ ሰበር ዜናው የእስልምና በመሆኑ የፊደላት ባለ ቤት ከሆነችው ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ላለመስማማት ነው? የሼክ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሐፍ አጠበች ይሉት ይሄውሎታ። በሚቀጥለው ተስተካክሎ እንደሚጻፍ ተስፋ አደርጋለሁ።

ወደ ርዕሳችን ስንመለስ “በእስር የሚማቅቁ እስረኞች ከእስር ይፈቱ!” በማለት ድምጽ የሚሆን ግለሰብም ሆነ ድርጅት መኖሩ በራሱ መታደል ነው። በእውነቱ ነገር እንዲህ ያለ ስራም የሚያስመሰግንና የሚደገፍ መልካም ተግባር እንጂ የሚተች/የሚነቀፍም አይደለም። ዳሩ ግን “የህሊና እስረኞች” ይፈቱ በማለት መንግስታት ማፈጠጥና ማስፈራራት ለአፍሪካ መንግስታት ብቻ ነውን? የሚለው ጥያቄ ግን መመለስ የሚገባው ጥያቄ ነው። በእርግጥ የእኛ (የአፍሪካውያን) ነገር ትንሽዋ ነገርም ብትሆን ጎልቶ የሚታይበት ምስጢሩ ድህነት ስለተጨመረበት ነው። ይህ ማለት ግን ሌላው የዓለማችን ክፍል በአፍሪካ አለ የሚባለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣም ሆነ ሌሎች ሰብዓዊ በደሎች በተቀረው ዓለም አይፈጸሙም ማለት ግን አይደለም። ወደ አፍሪካ ስንመጣ ግን በነገር ሁሉ ጣት የተቀሰረች እንደሆነ ጣቶች ሁሉ ወደ አፍሪካ ብቻ የሚቀሰርበት ምክንያት ግን አይገባኝም። ወይስ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል መሆኑ ነው?

በኢትዮጵያ እስር፣ ግፍ፣ ኢ ፍትሐዊነት አለ ወይ የለም? “አዎ አለ” በማለት ቀጥተኛና የማያሻማ መልስ የምሰጠው “አዎ! ስኖውደን በራሽያ/ሩስያ የሚገኘው ሊሞሸር ሳይሆን “ከስቅላት” ለመትረፍ ነው፤ ብራድለይ በውህኒ ዓለሙን እየተቀጨ ሳይሆን እየቀጨ ነው፤ ጥቁር አሜሪካዊ ትራይቮን በጥቁነቱ ሞት አይገባውም ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሰው ደም እኩል እንደሌላው ሰው ታይቶ ገዳይ በነፍስ ማጥፋት በወንጀል መጠየቅ አለበት/ነበረበት” ብለው የሚያምኑ ከሆነ ብቻ ይሆናል ከላይ ከፍ ሲል ለተነሳ ጥያቄ መልሱ “አዎ! አለ” የሚል ቀጥተኛ መልስ ሊያገኙ የሚችሉ። በእነዚህ ከብዙ በጥቂቱ የምዕራቡ ዓለም የሰብዓዊ መብት አያያዝ እውነታዎች የሚስማሙ ከሆነ ደግሞ በኢትዮጵያም ሆነ  በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያለው/የሚታየው  የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚክዱበት ሁኔታ የለም። ታድያ “Amnesty International” ሆነ ሌሎች መሰል “የሰብዓዊ መብት ተሟጓች” ድርጅቶች ክንዳቸው አፍሪካ ብቻ ሲዘረጋና ሲበረታ ሲያዩ ድርጅቶቹን የማይጠይቁ ከሆነ እርስዎ ራስዎም ችግር አለቦት ማለት ነው። ከነምሳሌው “ባለቤቱ ያቀለለው አሞሌ…” እንደሚባለው ነገ ኢትዮጵያ ለኑሮ የምትመች አገር ሆና ካገኝዋት ዜጎችዋ እርስ በርስ አጨራርሰውም ሆነ ወደ ባህር ጥለው ምድሪቱ የማይሰፍሩባት ምክንያትም  የላቸውም። ማን ያውቃል? እዚህ ሁሉ ሰጣ ገባ ውስጥ ሳይገቡም አንድ ቀን በሕግ በገዛ አገራችን አስለቅቀው ተደላድለው የሚኖሩበት ምክንያትም ሊፈጥሩ ይችላሉ።

እንግዲያውስ የኢሳት የንስሃ አባት “Amnesty International” ጨምሮ የተቋቋሙበት ዋና ዓላማ ድሃን ለመበደል፣ አፍሪካ ሀገሮችን አለ አግባብ ለመርገጥና ሕዝብን ለመከፋፈል፣ በሕዝቦችና በመንግስት መካከል ሰላማዊ የሆነ ቅብብል እንዳይኖር እሳት መለኮስ በአጠቃላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ለመሆን ካልሆነ በስተቀር “Amnesty International” ሆነ መሰል “የሰብዓዊ መብት” ተሟጋቾች ነን ባዮች ቀልደኞች ምዕራባውያን ድርጅቶች እውነት፦

  • ስለ ሰብአዊ መብት መረገጥ፥
  • ስለ ፍትህ መጓደል፥
  • ሃሳብህን በነጻነት የመግለጽ መብት ስለ መነፈግና መታፈን፥
  • ስለ ስለ ዜጎች እኩልነትና ዲሞክራሲ፥ ግድ የሚላቸውና የሚቆረቁራቸው ከሆነ የሀገሪቱ ህገ መንግስት በመጣስ ጸረ ዜጎቹና የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ታጥቆ የተነሳ የአሜሪካ መንግስት በዜጎቹ የሚፈጽማቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶች በአስቸኳይ ማቆም ይገበባዋል በማለት ለአሜሪካ መንግስት አፍ አውጥቶ ይናገር። አይመስልዎትም? “የሰብዓዊ መብት” ተሟጓቾቹ 1.5 ሚልዮን ንጹሐን ኢራቃውያን ነፍስ መቀሰፍ በተመለከተ ምን አሉ? ባዶ! እኔ እስከሚገባኝ ድረስም ዝምታ የመምረጣቸው ጉዳይ ሌላ ምንም ማለታቸው ሳይሆን “ያለቀው ሕዝብ መሳሪያ ታጥቆ ግንባር ወርዶ ሲታኮስ የሞተ ሕዝብ ነው” ብለው የሚያምኑ ለመሆናቸው ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም። ለተጨቆኑ፣ ድምጽ ለሌላቸው፣ ለደካሞችና ለግፉዓን ድምጽ መሆን ያልቀረ፣ ተው ማለትና ልቀቅ ብሎ ማስለቀቅ ኃያሉ ጭምር ተው ማለት ነው እንጅ።

መቼም አእምሮው ያጣ ግለሰብ ካልሆነ በስተቀር “ብራድለይ ወደ ውህኒ የወረደው ከብቶቹን ውሃ ለማጠጣት ነው” የሚል አይኖርም። ሩስያ የሚገኘው ስኖውደንም እንዲሁ “ለሽርሽር ነው የሄደው” ባይ ሰው አይኖርም። ጥቁር በመሆኑ ብቻ በአመጸኝነትና በሁከት ፈጣሪነት ተፈርጆ ልቡ በጥይት ተበስቶ የወደቀና ደሙ ደመ ከልብ ሆኖ የቀረው 17 ዓመት ትራይቮንም እንዲሁ “ሞት አጓጉቶትና የማያቀው ዓለም ናፍቆት ነው” ብለው ያምኑ ይሆን? በእውነቱ ነገር ዓለም አቀፍ ድርጅቶቹ እንዲህ ብለው ቢያምኑ ነው እንዲህ ከፍ ዝቅ የሚያደርጋቸውና የሚያንገሸግሻቸው እንጂ የሰው ክብር መገፈፍና መገፋት ቢሆን ኖሮማ ለድሃ አገሮች ድምጻቸው ከፍ አድርገው የሚያሰሙት ያህል ለኃያላኖቹም ሲናገሩ በሰማናቸው ነበር። ለዚህ ግን አልታደልንም። እንደው የቦስተን ፍንዳታ ተከትሎ ተጠርጣሪው (መዋቹ) ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቀ መሆኑን እየታወቀ በሰባት ጥይት ተደብድቦ ስለ ሞተው ግለ ሰብስ የሰብአዊ ተሟጓች ድርጅቶች ምን አሉ? ባዶ!

“Amnesty International” እውነትነት ካለው “Free Bradley Manning!” በማለት መፎክር ማሰማትም ሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ለምን አይሞክራዋትም? ICC እንደሆነም ትላልቆቹ ትቶ በጦር ወንጀለኝነትና በዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ቢመሰርት የሚመሰርተው በማን ላይ ሆነ ነውና። ICC ክስ መሰረተ ተብሎ ዜና የተሰማ እንደሆነ ክስ የሚመሰርተውና የሚያናፋው በአፍሪካ መሪዎችና በሌሎች ደካማ አገሮች ነው። CPJስ ቢሆን የማይክል ሃስቲንግስ (የሮሊንግ ስቶነ ጋዜጠኛ) ድንገተኛ ሞት በማስመልከት ምን አለ? ይህ ሰው በዋዜማው ማን ሲያሯሩጠው እንደነበረና ማንን ለማጋለጥ ጥድፍያ ላይ እንደነበረም የታወቀ ነው። ከዚህም በመነሳት ለመዋቹ ድንገተኛ የሆነበት የሞት ዓይነት ጀርባ ማን እንዳለ ለማጣራት ያደረገው ነገር አለ? ባዶ!

ነገሬን ለማሳጠር ያክል የሀገሬ ሰው “የማትሰማው ስድብ ዘፈን፣ የማታነበውም ጽሑፍ ስዕል ነው!” እንዲል ኢትዮጵያዊ ሆይ! የራስህ ባልሆነ ቋንቋ ከሚሰራጩ ከፋፋይ ዜናዎችና ሪፖርቶች እንደ ዘፈንና እንደ ስዕል ሆኖውልህ ከብዙ አሰቃቂ ክስተቶች ለማምለጥ እንደተቻለ ምንም ጥርጥር የለውም። ተርፈናል!! ተርፈናል ተበሎ ሕዝብ በሙሉ ልቡ እንዳይተኛ ግን የሌሊት እንቅልፍ የሚነሳ መራራ ዘር ከጓዳህ በቅለዋል። በበሉበት ሳህን የሚጮሁ፣ ስለ ጌቶቻቸው ክብር ያጠባች ወላጅ እናታቸውን በቁምዋ ከመቅበር/አፈር ከማልበስ የማይመልሱ፣ እምነታቸውንና ማንነታቸውን የሸጡ፣ ከጠላትም በላይ ጠላቶች፣ ሆድ አደሮችና መሆዶዎች እንደ ኢሳት ያለ የባንዳዎች ስብስብና የጥፋት መልዕክተኞች ጥቃቅን ቀበሮዎች ግን አይተኝሉህምና አጥብቀህ ያዛቸው፣ እወቃቸው፣ አጥምዳቸውም ለማለት እወዳለሁ።

ኢሳት ሀገር የሚከፋፍል: ሕዝብ የሚበትን: የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርስ የሚያባላና በገዠራም የሚያጨፋችፍ: በዚህ መሃልም እንጀራቸውን የሚጋግሩበት ምክንያት አስከተፈጠረ ድረስ ያለውንና የሌለውን አቅማቸው ተጠቅመው በሰበርም ሆነ በመደበኛ “ዜና” የኢትዮጵያውያን ነፍስ የማያውኩበት ምንም ምክንያት የላቸውም። ስራቸው እንጀራቸውም ነውና። የዋኖቹ ዓላማና ግብም ሁከትና ትርምስ መፍጠር እስከ ሆነ ድረስ ኢሳት ሞያው የሚጠይቀው ስነ ምግባር ተሟላ አልተሟላም ትርጉም አይሰጣቸውም። ኢሳት እንደ አሳማ ያገኘውን ከማግበስበስና እንደ ውሻም የበላውን ሁሉ ከመትፋት አልፎ ይህ ነገር ወደ ህዝብ ጆሮ ቢደርስ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው በማለት ለትውልድ የሚቆረቆር ልብም የላቸውም። እንደውም በአንጻሩ “በዋናነት የምንፈልገው ነውጥና ሁከት አይደለም ወይ!” በሚል መንፈስ ኢሳት የነጭ አንደበት እየጠበቀ ፕሮፖጋንዳውን ለመንዛት ሲጣደፍ ነው የምናየው። ለዚህም ነው እንዲህ ያሉ ሪፖርቶች በሕዝብ ጆሮ ቢደርሱ ሀገርን ይጠቅማሉ ወይስ ያውካሉ? ያንጻሉ ወይስ ያበጣብጣሉ? ብሎ ጥያቄ በኢሳት ሰፈር ዘንድ ቦታ የሌለው። ይህን ዓይነቱ ጠማማ የኢሳት አካሄድ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕጣ ፈንታ የሚያጨልምና የሚያኮላሽ እንጅ የሚያቀናም እንዳይደለ ለሁላችን ግልጽ ሊሆን ይገባል።

ኢሳት የሀገር ጠላት ነው! ምን ነው ቢሉ

  • ሀገሩ የሚወድ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የማንንም ድምጽ ሳያላምጥ አያስተጋባም! 
  • ሀገሩ የሚወድ “ዜናው/ሪፖርቱ” ብቻ በሕዝቡ ዘንድ ውዥንብር ይፍጠርልኝ እንጂ ሀገር/ሕዝብ የራሱ ጉዳይ! በማለት በግብር ይውጣ ስራ ራሱን አያሰማራም።
  • ሀገሩ የሚወድ ሰው የግሉ ጥቅምም ቢሆን ይጎድልበታል እንጂ በሀገሩ ሉዓላዊነት ላይ ቆሞ ከበሮ አይደልቅም።
  • ሀገሩ የሚወድ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የሀገሩ ሉዓላዊነትና ጥቅም ከማስቀደም ይልቅ ሌላ የሚቀድም ነገር የለውም።
  • ሕዝቡንና ሀገሩን የሚወድ ዜጋ በእናት አገሩ ህልውና ላይ ቁማር የሚቆምር ህሊናም አእምሮም የለውም። 

ህሊና ቢሶች የኢሳት ቅጥረኞች ግን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት በተደጋጋሚ ከመግለጽ አልተቆጠቡም። ወጣም ወረደ በባዖድ ያልተገዛ ህዝብ ምስጉን ነው! ይህ ሕዝብ እንኳንም እንግሊዝኛ ተናጋሪ ባዕድ አልገዛው! እንኳንም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ባዕዳን አልተገዛን። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! አለመገዛትህ ከምንም በላይ በህልውናህ የሌሊት እንቅልፍ የራቀባቸው ጥቅማቸው እንጅ ማንነትህ ትርጉም ከማይሰጣቸው ወጥመድ ጠብቆሃል። በባዕድ አለመገዛትህም አንዳች ነገር አልቀረብህም። የቀረብህ ነገር ቢኖር እርስ በርስ መጨራረስ፥ ጥላቻ፥ ጸብ፥ ደም መፋሰስ፥ በፓንጋ መቆራረጥና መተራረድ፥ መለያየት፥ የማያባራ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መግባት በአጠቃላይ የቀረብህ ነገር ቢኖር ሞት ነው። ጠላቶችህ ተቆርቋሪዎችና መልካም አሳቢዎች መስለው የሚረጩትን መርዝ እየሰማህ እርስ በርስ ተራርደህና ተጨፋጭፈህ መተላለቅ ነው የቀረብህ።

ይህ ስል ግን በምንም ዓይነት መልኩ “ድንቁርናን” እያበረታታሁ አይደለሁም (እንግሊዝኛ ቋንቋ አለማወቅ በድንቁርና የሚያስፈርጅ ከሆነ ማለቴ ነው)። እንግሊዝኛ ቋንቋ ማወቅ ይጎዳል እያልኩም እንዳይደለ አንባቢ እንዲገነዘብልኝ እፈልጋለሁ (አስተዋጽዖ አለው የለውም? ተመክሮ ለመቅመስ በተወሰነ መልኩ ሊኖረው ይችላል)። አሁንም አባባሌ ከትምህርት ጋር አንዳች የሚያገናኝ ነገር የለውም። የትምህርት ሰው ነኝ የዕድሜ እኩያዎቼ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ሁሉ ደግሞ እኔ “የገጠመኝ ዕድል” (የመማር) ቢገጥማቸው ደስታዬ የላቀ ነው። መማር ራስህን ለመልካም ነገር ማዘጋጀት ነውና።

በተረፈ የትልቅዋ ካፒታሊስ አገር ሀገረ አሜሪካ አበዳሪ ትልቅዋ ኮሚኒስት ሀገረ ቻይና 46 በመቶ የሚሆነው የከፍተኛ ተቋሞችዋ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገሩን ይቅርና አሜሪካ የምትባል ሀገር ካርታ ላይ ጠቁመ ማሳየት እንደማይችሉ ስገልጽ በዚህ አጋጣሚም የዕድገት ምንጭ የዜጎች የእርስ በርስ መቀባበል: ልዩነቶችን በማጥበብ አንድነትን በማጠንከር: ከምንም በላይ ደግሞ በዜጎች መካከል ሰላምና ፍቅር መሰረት ያደረገ ግኑኝነት የመኖሩን ተከትሎ የሚመጣ/የሚገኝ ውጤት እንጅ የባዕድ ቋንቋ ከማወቅና ካለማወቅ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት እንደሌለው በመግለጽ ጽሑፌን እዚህ አቋጫለሁ። ኢሳት የሀገር ዕዳ ነው!

ሀገሬ ህዝቤ የሚል ሁሉ ደግሞ ወያኔ ከተባለ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ወያኔ ነው!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገርብኤል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s