የሙስሊሞች ጥያቄ የሥልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ ነው!

መሪ ጥቅስ፡

“ሰሎሞንም በአባቱ በዳዊት ዙፋን ተቀመጠ መንግሥቱም እጅግ ጸና። የአጊት ልጅ አዶንያስም ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ እርስዋም ወደ እኔ መምጣትህ በሰላም ነውን? አለች እርሱም በሰላም ነው አለ። ደግሞም ከአንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ አለ እርስዋም ተናገር አለች። እርሱም መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥቱ ከእኔ አልፎ ለወንድሜ ሆኖአል። አሁንም አንዲት ልመና እለምንሻለሁ አታሳፍሪኝ አለ። እርስዋም ተናገር አለችው። እርሱም አያሳፍርሽምና ሱነማይቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ አለ። ቤርሳቤህም መልካም ነው፥ ስለ አንተ ለንጉሡ እነግረዋለሁ አለች። ቤርሳቤህም የአዶንያስን ነገር ትነግረው ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ገባች ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም፥ በዙፋኑም ተቀመጠ ለንጉሡም እናት ወንበር አስመጣላት፥ በቀኙም ተቀመጠች። እርስዋም አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች። ንጉሡም እናቴ ሆይ፥ አላሳፍርሽምና ለምኝ አላት። እርስዋም ሱነማይቱ አቢሳ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት አለች። ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ ሱነማይቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኝለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት ካህኑም አብያታርና የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው አላት።”  (መጽ. ነገሥት ቀዳማዊ  2፥ 12- 22)

የጽሑፉ ዓላማ፡ 

ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በአንድም በሌላም መልኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታጥቆ የተነሳ ኢሳት በመባል የሚታወቀው የሳይበር ሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ እ.አ.አ ነሐሴ 16/2013 ዓም (ርዕስ የለውም) [http://ethsat.com/video/esat-news-analysis-16-august-2013/] የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ላይ ያነጣጠረ ያሰራጨው የማዘናግያ የተሸረበ ተንኮልና ሴራ (ፕሮፓጋንዳ) ቅድሳት መጻህፍት እንደሚያስተምሩት እንዲሁ ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እየተናገሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ አፋቸውን ለመዝጋት፥ ለመመከትና ለማምከን በተጨማሪም አርቲስት ታማኝ በየነ የተባለ በቅድሳት መጻሕፍት እውቀት ያልበሰለና ያላደገ ንኡሰ ክርስቲያን ከተመሳሳይ የጥፋት፥ የሁከትና የሽብር ልሳን ከሆነው ከኢሳት እ.አ.አ ሚያዝያ 2013 ባደረገው ቃለ ምልልስ የሰጠውን እጅግ አሳፋሪ ቃል [http://www.youtube.com/watch?v=Jwe_w6-65ik] ከቻለ ግለሰቡ ከስህተቱ ተምሮ በስህተት ላይ ስህተት ከመስራት ይመለስ ዘንድ ለመምከር፤ አሻፈረኝ ያለ እንደሆነ ደግሞ ስለ ልጆቹ ሲል ክርስትናን በተመለከተ አፉ ይዘጋልን ዘንድ ለትምህርት ተጻፈ።

የጽሑፉ ውሱንነት፡ 

ኢሳት የሳይበር ሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ እ.አ.አ ነሐሴ 16/2013 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን አማኞች ዒላማ ያደረገና ያነጣጠረ ያሰራጨው ፕሮፖጋንዳ በተመለከተ ጽሑፉ ጠቅለል ባለ መልኩ የፕሮፖጋንዳው ጭብጥና ዓላማ በጨረፍታ የሚያመላክት እንጅ እያንዳንድዋን የፕሮፖጋንዳው ይዘት አይተነትንም።

ሐተታ፡ 

ሰሎሞን ማለት የስሙ ትርጓሜ ሰላማዊ ማለት ሲሆን ዳዊት ከቤርሳቤህ የወለደው ባረጀ ጊዜም በፈንታው በዙፋኑ ይቀመጥ/ይነግስ ዘንድ የተቀባ የእስራኤል ሦስተኛና የመጨረሻ በጥበቡም የታወቀ ታላቅና ገናና ንጉስ ነው። ቤርሳቤህ ማለት ደግሞ ቀደም ስል እንደተመለከትነው የዳዊት ሚስት የሰሎሞንም እናት ናት። አዶንያስ ዳዊት ከአጊት የወለደው አራተኛ ልጁ ሲሆን (2ኛ ሳሙ 3፡ 2- 4) በአባቱ ተገስጾም ሆነ አባቱ ከቶ በሕይወቱ ሳለ ተቆጥቶት የማያውቅ በውበቱም እጅግ ያማረ ሰው ነበረ።

በተመሳሳይ መጽሐፍ ምዕ 1፥ 5-10  የአጊትም ልጅ አዶንያስ “ንጉሥ እሆናለሁ!” ብሎ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎች አዘጋጅቶ እንደተነሣና ሴራውም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር እንደመከረ በዝርዝር ያትታል። በተጨማሪም ነቢዩ ናታን የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?” በማለት ሲያረዳትና አዶንያስ ሳይገባው ወደ ንግሥና የወጣ እንደሆነ ለራስዋ ሆነ ለልጅዋ ህይወት ጠንቅ አንደሆነ በማሳሰብ ጭምር ሳይመሽ በጊዜ ማድረግ የሚገባት ታደርግ ዘንድ ምክሩን ሲለግስላትም እንመለከታለን።

ቤርሳቤህም ጨርቄን ማቄ ሳትል ወደ ንጉሡ እልፍኝ እንደገባችና ከቁ 17 ጀምሮ እንደተጻፈም “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ለባሪያህ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ምለህልኛል አሁንም እነሆ አዶንያስ መንገሡ ነው አንተም ጌታዬ ንጉሥ ይህን አታውቅም እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል የንጉሡንም ልጆች ሁሉ ካህኑንም አብያታርን የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል ባሪያህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም። አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዓይን ይመለከትሃል። ይህ ባይሆን ጌታዬ ከአባቶችህ ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ኃጢአተኞች እንቈጠራለን።” በማለት በአጊትም ልጅ አዶንያስ መሪነት በንጉሱ ግዛት እየሆነ ያለው ጋጠ ወጥነት ካስረዳችው በኋላ ንጉሱም “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን በእውነት ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ” በማለት ቃሉን በማህላ አጽንቶ እንደሸኛትና እንደተናገረው እንደ ቃሉ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ንጉስ ሆኖ ይነግስ ዘንድ ሲሾመው ደግሞ በቁጥር 33 እንመለከታለን።

ሰሎሞን በመላ እስራኤል መንገሱንና በአባቱ ዙፋን መቀመጡ የሰሙ የአዶንያስ ደጋፊዎች፣ አጨብጫቢዎችና ከበሮ መቺዎች የሚይዙትና የሚጨብጡት ጠፍቶባቸው በየአቅጣጫው ሲበታተኑ የሰራውን ስራ የሚያውቅ አማጺው የአጊት ልጅ አዶንስ ደግሞ ከለላ ፍለጋ የመሠዊያ ቀንድ ለመያዝ ሮጦ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ። ሰሎሞንም “አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ ንጉሡ ሰሎሞን ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” የሚል መልዕክት በሰማ ጊዜ ሰሎሞን “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል” ሲል በላከው የይቅርታና የምህረት መልዕክት መሰረት አዶንስ ከመሠዊያው እንደወረደና ከዚም በንጉሡ በሰሎሞን ፊት ቀርቦና እጅ ነስቶ ሰሎሞንም ወደ ቤትህ ሂድ በማለት በሰላም ሲያሰናብተው እናገኘዋለን።

የሀገሬ ሰው “ድመት መንኩሳ አመልዋ አትረሳ” እንዲል ከፈጸመውም ወንጀል አንጻር በሞት መቀጣት ሲገባው በምህረትና በይቅርታ የተሰናበተ አዶንያስ በሰላም አርፎ መቀመጥ አላስችል ብሎት አሁን በመላ እስራኤል ንጉስ ሆኖ ለመንገስ ያደረበት ክፉ ምኞትና የተጸናተው በሽታ በድጋሜ በሰሎሞን መንግሥትነት ለማሴር ደግሞ ተነሳ።

መሰሪው የአጊት ልጅ አዶንያስ እንቅልፍ የነሳው የበላይ የመሆን፣ የፖለቲካና የስልጣን ጥያቄው እውን ለማድረግ ማለትም በንጉሡ በሰሎሞን ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሰላማዊ የሚመስል አውዳሚ የጋብቻ ጥያቄ ይዞ ብቅ አለ። ይህ ለብዙሐን በቀላሉ የማይታይ መሰሪ ንድፍና እቅድ ደግሞ በምድር ክበብ ላይ የተቀመጠ፣ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል፣ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ እግዚአብሔር ዓይኑ የገለጠለትና ያበራለት ከንጉሡ ከሰሎሞን በቀር ይህ ሰላማዊ መሰል አውዳሚ አጃንዳ የማየት ዓቅም ያለው ሰው አልነበረም። ይሄ ምስጢር ለተወዣዋዥ አርቲስት ታማኝ በየነ ሆነ ለመላ የኢሳት ቅጥረኞች የሚገባ ዓይነት ምስጢርም አይደለም። የአዶንያስ ሴራ የንጉሡ እናት ከሆነችው ከቤርሳቤህ ጀምሮ ለሰፊው ሕዝብ የሚገባ ዓይነት አጀንዳ ሳይሆን እንደው ከአዶንያስ ጎን የሚያስቆምና ይደልዎ! አየተባለ ድጋፍና ይሁንታ የሚያሰጥ አጀንዳ ነው። ቤርሳቤህ በየዋኅነት ያደረገችውም ይህንኑ ነው።

ሴራው እንደሚከተለው ይመስላል፥ “የአጊት ልጅ አዶንያስም ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ እርስዋም ወደ እኔ መምጣትህ በሰላም ነውን? አለች እርሱም በሰላም ነው አለ (1)። ደግሞም ከአንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ አለ እርስዋም ተናገር አለች። እርሱም መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ (2)፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ (3) ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና (4) መንግሥቱ ከእኔ አልፎ ለወንድሜ ሆኖአል (5)። አሁንም አንዲት ልመና እለምንሻለሁ አታሳፍሪኝ አለ። እርስዋም ተናገር አለችው። እርሱም አያሳፍርሽምና ሱነማይቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ አለ (6)። ቤርሳቤህም መልካም ነው፥ ስለ አንተ ለንጉሡ እነግረዋለሁ አለች (7)።”

ከአንድ እስከ ስድስት ያስቀመጥኳቸው ቁጥሮች ምን ማለት እንደሆነ አጠር አጠር ባለ መልኩ ላስቀምጥ፥ ከዚያ በፊት ግን ደንቆሮው አርቲስት ታማኝ በየነ በኢሳት ቀርቦ የተናገረውን ላስታውሶት “እኛ ሙስሊሞች የምንለው ‘የእስላም መንግስት ይቋቋም አላልንም’ ይሄን ሲል No No No! በልብህ የምታስበው አለ እንድል ነው የሚፈለገው? እኔ ማነ ነኝና ነው በአንድ ኢትዮጵያዊ የውስጥ ስሜት ውስጥ ተጠራጣሪ ሁኜ ልክ አይደለህም ልል የምችለው?”

 1. ቤርሳቤህ “ወደ እኔ መምጣጥ በሰላም ነውን?” በማለት ስትጠይቀው ኤዶንያስ: በአፉ “ሰላም ነው!” ሰይጣን አይስማ ምንም ችግር የለም! በማለት ቢሸነግላትም በልቡ ያለው ግን እውነት ሰላም የሚያወርድ ሳይሆን የሰውን ሰላም የሚነሳ አጀንዳ መሆኑን በቁጥር ስድስት ላይ አስፍተንና አመሳጥረን የምናየው ይሆናል።
 2. “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ” ውሽት! ማን የሰጠው መንግስትነት? “ንጉሡም ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን በእውነት ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ ብሎ ማለ።” (ቁ. 29, 30)
 3. “እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ” ውሸት! የት ቦታ ነው የእስራኤል ሕዝብ አዶንያስን የተከተለ? አዶንያስ የእኔ ናቸው በማለት ያሰባሰባቸው ድግስ ደግሶ አብልቶና አጠጥቶ አፋቸው የዘጋቸው ወንዝ የማያሻግሩ ካህናትና 50 የሚያክሉ ምናምንተዎች “እስራኤልም ሁሉ” የሚያስብለው?
 4. “ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታል” አዶንያስ የሰሎሞን መንግስትነት ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን የምያምን ከሆነ ቤርሳቤት ጋር ምን ሊሆን መጣ? በማለት ይጠይቁኝ ይሆን። ግድ የለም! ለጥቂት ይታገሱኝ እንጅ የአዶንያስ አነጋገር ከሽንገላ  ያለፈ እውነትነት እንደሌለው ቁጥር ስድስት ዓይንዎን ያበራሎታል።
 5.  “መንግሥቱ ከእኔ አልፎ ለወንድሜ ሆኖአል” አሁን አዶንያስ ቤርሳቤህ እየወጋት ያለው ማደንዘዣ መርፌ መጡኑ ጨምረዋል። አዶንያስ በውስጠ ዘ እያለ ያለው “ቤርሳቤህ ሆይ! ግድ የለም እመኚኝ ድሮ የምታውቂው መሰሪ፣ ነውጠኛ፣ ሁከተኛ፣ አሸባሪውና አደጋ ጣዩ አዶንያስ አይደለሁም። ንግሥና እንደሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለወንድሜ ሆኖዋል። እኔም ወጥቶልኛል። ይልቁንስ …
 6.  “እርሱም አያሳፍርሽምና ሱነማይቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ አለ” የፈጣሪ ያለህ! ሱናማዊትዋ አቢሳ ደግሞ ማን ናት? እና አዶንያስ ሰሎሞንን አቢሳን ይድረው ዘንድ ጥያቄ ቢያቀርብ ምን ላይ ነው ጥፋቱ? ምን ችግር አለው? በማለት ማብራራ ፍለጋ ጥያቄ ይጠይቁ ይሆናል። የሚያስብ አእምሮ ሳይሆን የረጅም ምላስ ባለቤት የሆኑ እንደነ አርቲስት ታማኝ በየነ ያለ ደግሞ አዶንያስ “ሰላም ነው! … መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ … ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታል … መንግሥቱ ከእኔ አልፎ ለወንድሜ ሆኖአል” እያለ No No No! በልብህ የምታስበው አለ እንድል ነው የሚፈለገው? አዶንያስ የጋብቻ ጥያቄ ነው እያቀረበ ያለው! ጥያቄው ሰላማዊ ነው! የተፈነከተ ሰው የለውም! እንደው አዶንያስን ልናደንቀው ይገባል! የጋብቻ ጥያቄው በመደገፍም አብረንው ልንቆም፣ ልንድረው፣ ላናጨበጭብለት፣ ልንጮህለትና አጋርነታችንን ልናሳየው ይገባል። በማለት ሽንጡን ገትሮ የሚሟገት ሰውም አለ። ለማንኛውም አቢሳ ማለት ዳዊት በሸነገለ በዕድሜም እየገፋ ሲመጣ ባሪያዎቹ “ለጌታችን ለንጉሡ ድንግል ትፈለጋለች በንጉሡም ፊት ቆማ ታገልግለው፥ በጌታችንም በንጉሡ ብብት ተኝታ ታሙቀው” ሲሉ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት በእስራኤልም አገር ሁሉ የተዋበች ቈንጆ ሱነማይቱን አቢሳን አገኙ አቢሳ ንጉሡ ባይገናኘትም ትረዳውና ታገለግለው የነበረች ሴት ናት። አዶንያስ ቤርሳቤህን አባክሽ አያሳፍርሽምና ልጅሽ ሰሎሞን አቢሳ ይድርልኝ ዘንድ ተማጸኝልኝ በማለት ደጅ ሲጸና የምናየው አዶንያስ በአቢሳ ፍቅር የከነፈ ይመስሎታል? አዶንያስ በአቢሳ ፍቅር አህል ውሃ አልወርድ ያለው ይመስሎታል? አዶንያስ ቀደም ሲል በራሱ መንገድ ሞክሮ ያልተሳካለት የፖለቲካና የስልጣን ጥያቄ በእስራኤል ሕግ መሰረት የንጉስ ሚስት የነበረች ማግባት ማለት ለአዶንያስ የሚያስገኘው ጥቅም ቢኖር ነው እንጅ ብለው አልጠረጠሩም? ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮሃለች! ሁሉን መጠራጠር ከንቱ ቢሆንም ሁሉን አምነህ መቀበል ደግሞ የከንቱ ከንቱ መሆኑን ለአርቲስት ታማኝ በየነ እንደሚያደርሱልኝ ቃል ይግቡልኝ።
 7. “መልካም ነው!” አለች ቤርሳቤህ የተደገሰላት ድግስ አርቃ ለማየት ባትታደልም። የእኛ ታማኝ በየነስ ቢሆን በቀላል አማርኛ “እኔ ማነ ነኝና ነው በአንድ ኢትዮጵያዊ የውስጥ ስሜት ውስጥ ተጠራጣሪ ሁኜ ልክ አይደለህም ልል የምችለው?” ብሎ የለም። በነገራችን ላይ በቤርሳቤህና በአርቲስት ታማኝ በየነ መካከል የጾታ ልዩነት መኖሩን እንደተጠበቀ ሆኖ ትልቁ ነገር ግን ቤርሳቤህ ሕግ አርቲስት ታማኝ በየነ ፖለቲካ አለማወቃቸው ያመሳስላቸዋል። ቤርሳቤህ የአዶንያስ የጋብቻ ጥያቄ “መልካም ነው” በማለት ብቻ አድንቃ እጅዋና እግርዋ አጣጥፋ ብትቀመጥ ባልከፋ ነበር ነገር ግን “ስለ አንተ ለንጉሡ እነግረዋለሁ” በማለት ጭራሽ የአዶንያስ መልዕክተኛ በመሆን ወደ ንጉሡ ለመሄድ መጣደፍዋ ነው የሚገርመው። ታማኝ በየነም እንደዚሁ በግሉ የሙስሊሙች ጥያቄ “የመብት ጥያቄ ነው” ብሎ ሊያም ይችላል። በኃይማኖት ስም ግን ለራሱ ታታሎና ተሳስቶ ዜጎችን የማሳሳት መብት የለውም። አርቲስት ታማኝ በየነ ለማውራት የማይለግምና የማይታጠፍ ምላስ እንጅ ለማሰብ የታደለ አእምሮ እንደሌለው በቃሉ መስክሮልናል። ማሰብም ሆነ ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫ ማየትና መጠየቅም ስላልፈጠረበት “እኔ ማነ ነኝና ነው በአንድ ኢትዮጵያዊ የውስጥ ስሜት ውስጥ ተጠራጣሪ ሁኜ ልክ አይደለህም ልል የምችለው?” አለን። ታድያ ታማኝ የክርስትና እምነት ተከታዩ ማህበረሰብ በተለይ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን እምነት ተከታዮች ምእመናን የእስልምና ኃይማኖት አማኞች የስልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ ደግፈው ይወጡ ዘንድ ጥሪ የምታቀርበው ማን ነኝ ብለህ ስለምታምን ነው አይሉልኝም? አርቲስት ታማኝ በየነ ሆይ! በመጀመሪያ ደርጃ በዚህ ማንነትህ ከራስህ አልፈህ ማንንም እንደማትወክል ልትወክልም እንደማትችል ልታሰምርበት ይገባል። ሌላው ይሄ በማይመለከትህ፣ ባልገባህ በማይገባህና በማያገባህ፣ በማታውቀው፣ ባልፈጠረብህ፣ ባልዋለብህ ባላለፈብህና በሌለህ እውቀት እጅህን ለመጨመር ለምን አፍህ እንደሚፈጥንብህ አይገባኝም። በሞያህ እየቆረጥክም እየቀጠልክም “አይጥ አለፈች ድመት ተደናቀፈች” ዓይነቱ ክሊፕ እየሰራህ የሚስቅልህን ሰብስበህ አስቀህ ጎጆህን ከማሞቅ አልፈህ አእምሮ፣ እውቀትና ትምህርት በሚጠይቅ ሀገዊ ጉዳይ በተመለከተ አፍህን መክፈት የሚገባህ ሰው አይደለህም። አፍህ ስላመጣልህና አማርኛ ማውራት ስለ ቻልክ ብቻ ሳታስበውና ሳታመዛዝን በአደባባይ በምታደርጋቸው ሃይማኖታዊ ነክ ንግግሮችህ በእውነቱ ነገር ልታፍር ይገባሃል። ለመሆኑ መቼ ነው አላውቅም ማለት የምታውቅና አስበህ መናገር የምትጀምረው?  ከነተረቱ “ዶሮ ጭራ ጭራ አወጣች ማረጃዋን ካራ” እንዲል ውሎ አድሮ የሚዋረደው ሌላ ምንም ሳይሆን አንተ ራስህ ነህ እያቀለልህ ያለኸው። ራስህን የመግዛት ችግር ካለብህ ደግሞ እንዲህ ዓይነቱ ተራ አስተሳሰብና አመለካከት የሚወልደው ንግግር ሚስትህንና ልጆችህን ሰብስበህ በቤትህ ተናግረኸው የሚቀር ምስጢር ይሁንልህ ስል ወንድማዊ ምክሬን ልለግስልህ እወዳለሁ። በተረፈ ስለ ልጆችህ ስትል ክርስትናን በተመለከተ አፍህን ያዝልን። ለራስህ ተዋርደህ የመጽሐፉ ባለቤት አታዋርድ የእግዚአብሔር ስምም አታሰድብ። በነገራችን ላይ አርቲስት ታማኝ በየነ ይህ ሁሉ የሚቀባጥረው እስልምናን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ከሳውዲ የሚጎርፈውን ገንዘብ ተካፋይ ስለሆነ ነው፣ ክርስቲያን አይደለም፣ እስላም ነው፣ ከሃዲ ነው ወዘተ ብዬ አላምንም። ይልቁንስ አርቲስት ታማኝ ኃይማኖትም ሆነ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ያልተረዳ፣ በነገሮች እውቀት ያልበሰለ፣ የልምድ አዋላጅ፣ ዕድለኛ ፖለቲከኛ (ራሱን እንደ ፖለቲከኛ የሚቆጥር ከሆነ ማለቴ ነው)፣ ሌጣና ደንቆሮ ግለሰብ ነው ብዬ ግን አስረግጨ አምናለሁ። አይመስሎትም?

የአዶንያስ ጥያቄ በአፉ እንደሚለፍፈው የጋብቻ/የፍቅር ጥያቄ ሳይሆን በልቡ የቀበረው የስልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ መሆኑን ማየታችንን እንቀጥላለን። ታድያ የድምጻችን ይሰማ “የመብት ጥያቄ” በሚል የተደጎሰ የስልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ ሳይዘነጉ ነው።

“ቤርሳቤህም የአዶንያስን ነገር ትነግረው ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ገባች ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም፥ በዙፋኑም ተቀመጠ ለንጉሡም እናት ወንበር አስመጣላት፥ በቀኙም ተቀመጠች። እርስዋም አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች። ንጉሡም እናቴ ሆይ፥ አላሳፍርሽምና ለምኝ አላት። እርስዋም ሱነማይቱ አቢሳ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት አለች (8)። ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ ሱነማይቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኝለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት (9) ካህኑም አብያታርና የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው አላት (10)።”

8 “ሱነማይቱ አቢሳ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት አለች” ሌላ ምን ትበል። ቤርሳቤህ አለማወቋን ነው እንጂ መሰሪው አዶንያስ አስይዞ የላካት የሚፈነዳ ቦንብ እኮ ለእርስዋም ጭምር ነው። ልብ ይበሉ! ቤርሳቤህ “ይህ ባይሆን ጌታዬ ከአባቶችህ ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ኃጢአተኞች እንቈጠራለን።” በማለት በንጉሡ ፊት ያደረገችው ንግግር እኮ አዶንያስ የነገሰ እንደሆነ እርስዋም ልጅዋም የአዶንያስ ሰይፍ ሰለባ እንደሚሆኑና እንደሚጠራርጋቸው ነበር የገለጽችው። እስቲ አሁን እግዚአብሔር ያሳዮት ቤርሳቤህ አዶንያስ አስይዞ የላካት “የጋብቻ ጥያቄ” የስልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ መሆኑን ብታውቅ ኖሮ ቤርሳቤህ የአዶንያስ መልዕክት ለማድረስ ወደ ንጉሡ ስትሄድ። ጥጉ አእምሮው የሳተ አልያም ደግሞ የአርቲስት ታማኝ በየነና ግበረ አበሮቹ የኢሳት ቅጥረኞች ማየት የተሳናቸው የድኩማን ማህበር ማህበርተኛ ካልሆኑ በስተቀር ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ይህን ያደርግ ዘንድ  አይውለውም።

“ሱነማይቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኝለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት” ይህ ማለት በእስራኤል ሕግ የንጉሥ ሚስት ያገባ ወንድ ልጅ (ባል ማለት ነው) የንግሡ ዙፋን ወራሽ ሲሆን የአዶንያስ አጀንዳ ደግሞ “የጥይት” ድምጽ ሳያሰማ፣ ምንንም ሳይፈነክትና ግርግርም ሳይፈጥር የንጉሡ ሚስት የነበረችው አቢሳን በማግባት የስልጣን ጥሙን ላማርካት የነደፈው መሰሪ ስልት ነበር።

10 “ካህኑም አብያታርና የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው” ለመከራ ያለው መኖክሴ ዳዊት ሽጦ አህያ ይገዛል!  እንደሚባለው መነኮሳቱም ሆነ ሊቃነ ጳጳሳቱ በየመድረኩ እየወጡ ቢዘፍኑና ቢያቀነቅኑ፤ እንደነ ታማኝ ያለ ዕድለኛ ፖለቲከኛ ደግሞ “አላህ ወአክበር! ተክቢር! ተክቢር!” እያሉ ቢጮኹ፤ እንደ ኢሳት ዓይነቱ ሀገር በታኝ ትውልድ ገዳይ የሽብር ልሳኖች በፕሮፖጋንዳ ብዛት በክርስቲያኑ ማህበረሰብ ቢዘመቱና ቢረባረቡ ሊደንቀን አይገባም። ይልቁንስ በማናቸውም የመደለያ አጀንዳና አሽቃባጮች ድርጊት ሳንደለል እምነታችና ሀገራችን ቅድሳት መጻህፍት እንደሚያስተምሩን እንዲሁ ከመቼም ጊዜ በበለጠ ከኢስላማዊ ኃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ወረራ ለመጣበቅ፤  ለሚጠይቁንም ሁሉ መልስ መስጠት ያቻለን ዘንድ በአማላካዊ ቃል ራሳችንን ልናስታጥቅ፤ በተጠንቀቅ ልንቆም ይገባል።

እንደው እግዚአብሔር ያሳዮት እስልምና በኢትዮጵያ ምድር ለዛውም በዘመነ ኢአህዴግ ተበደልኩ፣ ተቆረጥኩ፣ ተፈለጥኩ፣ ተገፋሁ በማለት “የመብት ጥያቄ” ሲያነሳ። ለመሆኑ እንደ ኢአህዴግ አባዝቶ ያባዛቸው፣ የሾማቸውና የሸላለማቸው ማን ቢኖር ነው? ጃንሆይ ወይስ ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም? “ሹም ነገር ሲፈልግ የደሮ ሻኛ አምጡልኝ ይላል” ያሉ አባት ስማቸው ማን ነበር? ትናንትም ሆነ ዛሬ

የሙስሊሞች ጥያቄ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ አይደለም።

 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ ያሹትን ለመንቀልና ለማፍረስ የመብት ጥያቄ ካባ የተላበሰ ኢስላማዊ የፖለቲካና የስልጣን ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ ሸሪዓ የምድሪቱ የበላይ መተዳደሪያ ሕግ የማድረግ ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ ምድሪቱን የመቆጣጠር የበላይነት ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ የኢትዮጵያ ኢኮናሚ ደህንነትና አጠቃላይ የፖለቲካ መዋቅር ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ ኢትዮጵያን የዓረብ ሊግ አባል የማድረግ ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ ክርስትናን የማዳከምና የመበቀል ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ እስልምናን የማስፋፋት ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ እስልምናን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት የማድረግ ጥያቄ ነው!
 • የሙስሊሞች ጥያቄ፥ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስመ ዝክሯ፣ ታሪካዊ ይዞታዋና ህልውናዋ የማጥፋት የማውደምና የመደምሰስ ጥያቄ ነው!

ለመሆኑ ይህ ሁሉ ጩኸት፣ ጥሪ፣ ስብሰባ፣ ስምታና ጋጋታ ምን ለመሆን ነው?

 • ክሩን ለመበጠስ?
 • አብያተ ክርስቲያናቱን በእሳት ለማጋየት?
 • ባላምነበት ተገዶ ምላሱ ከትናጋው እስኪጣበቅ ድረስ አላህ ወአክበር በማለት ለመጮህ?
 • ስግደት ለማይገባው ለመስገድ?
 • የካህናቶቹን አንገት በስለታም ሰይፍ ለመቅላት?
 • አገልጋዮቹን እንደ ፍዬል ጫት ለማስቃም?
 • ሀብት ንብረትቱን ሜዳ ላይ ጥሎ ለመንከራተትና ለመሰደድ?
 • የአገሩ ቅርስና ታሪክ ለማፈራረስና ለማውደውም ነው ወይስ ሌላ ከዚህ ቀደም ያልቀመስነው ቢኖር ነው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አማኞች ምእመናን የእስልማና ኃይማኖት ተከታዮች የስልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ ደግፈው እንዲወጡ ጥሪ የሚቀርበው? ጥሪው ምን አድርግ ነው? የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አማኞች ምእመናን ሰይፍ ጋነገቱ ጎን ቆሞው ፎቶ ግራፍ እንዲነሱ ነው? ቀልደኛ። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አማኞች ምእመናን ክራቸውን ለመበጠስ፣ አብያተ ክርስቲያናት በእሳት ለማውደም፣ አገልጋዮች ካህናቶቹን በሰይፍ ስለት ላማጨድና ለመጨረስ ምን እርዳታ ያስፈልጋቸዋዋል? ምእመናን ይህን ለሰሚ ጆሮ እጅግ በጣም የሚሰቀጥጥና የሚዘገንን አረመንያዊ ድርጊት በገዛ ራሳቸው፣ ካህናቶቻቸው፣ ክብራቸው የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ድርጊት ለመፈጸም ከወሰኑ ምንም ዓይነት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እርዳታ አያስፈልጋቸውም።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s