ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልሰው አለ እንጂ ጣለው አላለም!

የጽሑፉ ዓላማ፥

ግልጽና አጭር በሆነ አነጋገር በኢትዮጵያ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን እምነት ተከታዮች ምእመናን አንዲሁም በሌሎች የክርስትንና እምነት ተከታዮች በሙሉ በአጠቃላይ ከማናቸውም መሰል ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጥቃቶች እንዲሁም ወረራዎች ራሱንና ቤተ ክርስቲያኑን ሜንጫ በእጁ ይዞ በዙሪው ከሚያገሳና ከተሰለፈው ነፈሰ ገዳይ ሃይማኖተኛ እንዴትና በምን ዓይነት መልኩ አንገቱን መጠበቅ እንደሚገባው ክርስቲያንዊ፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ስነ መሎከታዊ ትምህርት ለመስጠት ተጻፈ።

“ለኦሮሞዎች የምለው ምንድ ነው እኔ ስለ እስልምና ብዙ መናገር የጀምርኩ አንድ ከጎንደር የመጣ ጛደኛዬ ስለ አገኘሁ ነው። እኔ ባለሁበት ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ሙስሊም ነው። ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው። ጎንደር ውስጥ ግን ያለና የነበረ ችግር ሲነግረኝ ይሄ መለወጥ አለበት ነው … ።” የጎሳ ዜማ አቀንቃኝ (racial activist) ጃዋር መሐመድ

በእውነቱ ነገር እንደኔው ያለ ዘግይቶ የሰማ ካልሆነ በስተቀር ይህን ንግግር ሰምቶ እንቅልፍ የሚወስደው የክርስትና እምነት ተከታይ ካለ የማይቀርለት ሞት ሳይወስደው የሚያምነውን አምላክ ይመረምር ዘንድ ብቻ ነው የሚመከረው። ይህን አባባሌ ስመ ሊቃነ ጳጳሳትና መነኩሴን አይመለከትም። ምንነው ቢሉ ሰዎቹ ከሞቱ ስለክራረሙ ብንቀሰቅሳቸው ሀገር የሚያስለቅቅ ግመት እንጂ የሕይወት መዓዛ አይገኝባቸውምና። ደግሞም ሊቀ ጳጳና መኖክሴ ድግስ ደግሰህ በደገስከው ድግስ እራሳቸውን እስኪስቱ ድረስ ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ጥራቸው እንጂ ቤተ ክርስቲያን ይጠብቁልኛል ተብሎ ልብ አትጣልባቸው። ምክር አንድ!

ወደ ተናግሮ አናጋሪው የጎሳ ዜማ አቀንቃኝ ግለሰብ የደም አጀንዳ ልመለስ። በነገራችን ላይ ተናጋሪው ግለሰብ ምን ያላደረገ ብለው ነው? ለከት በሌለበት ያልጠራ አማርኛና ተብታባ አንደበቱ የፊዳላት ባለቤት በሆነችው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አፉን መልቶ የመዘባበቱ ምስጢር ሌላ ምንም ሳይሆን ዘወትር አጠገቡ የማይጠፉ ደህና አድርጎ የሚያውቃቸው የከተማ ቡችሎች፥ ሞራለ ቢሶችና እምነት አልባዎች ስመ ሊቀ ጳጳስና መኖክሴ እሱንና መሰሎቹን “አላህ ወአክበር!” በማለት እምነታቸውን ሲገልጹ የድንቁርናቸው ልክ ዳር ድንበር የለውና የተባለውን ሲያስተጋቡ፤ አንዲሁም አንዳንድ የፍየል ዓይን ቀቅለው የበሉ የደፋር አዋቂዎች “ክርስቲያን ነኝ!” ብለው ሲያበቁ “በንግግራቸው” መግቢያ የሚጮሁትን ጩኸት በዓይኑ እያየ በጆሮውም እየሰማ ዛሬ ይህ ሰው ምን ያላደረገ ብለው ነው? ስህተቱ ወዳጆቹን “እናንተን ብሎ ደሞ ክርስቲያን!” ማለት ትቶ በውስጠ ዘ “ክርስትና ብሎ ደግሞ እምነት!” በማለት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሜንጫ ይዞ በመውጣት የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አንገት ለመቅላት ይነሳ ዘንድ ለዘመቻ አፉን ቢከፍት ምን ይደንቃል? ለነገሩ’ማኮ ሰውየው አባቶቹ ያላደረጉት: የሚከተለው ሃይማኖት መመሪያ የሆነውን መጽሐፍ የማያስተምረውን አላደረገ። እንደው በአንጻሩ የሚደንቀኝ ይህ ግለሰብ አለኝ የሚለው የሰፈሩ ታሪክ (በአፈ ታሪክ የተተበተበ ለአደባባይ የማይበቃ አሳፋሪ እውቀት) ይዞና ኖሮት ሳለ ሰላም፤ ፍቅር መጠባበቅንና መከባበርን የሚያሰፍን/የሚያወርድ ንግግር ቢደርግ ነበር የሚደንቀኝ።

እዚህ ላይ አጽንዖት ሰጥቼ ለማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት ቢኖር ግን የሀገር ጉዳይ ግድ ብሎን በአንድነት ለመሰለፍ ሁኔታዎች ሲያስገድዱን መሰለፋችን እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን አጋጣሚ ተሳቦ “አንድ ነን!” ተብሎ የሚነገረው ፕሮፖጋንዳ ግን ጊዜው ያለፈበት ፉገራ ከመሆኑም በላይ “አንድ ነን!” እየተባለ ሲነገረው የመጣ የክርስትና እምነት በየዋህነት ሲመነጠር: ራሱንና ቤተ ክርስቲያንም ለስለታም ሰይፍና ለሚባላ እሳት ሰለባ ሲሆን ሌላው ደግሞ በንጹሐን ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች ደም ሰክሮ ጣመኝ ድገመኝ እየተባለ የሚደልብበትና አትራፊ የሚሆንበት የለበጣ ጨወታ አሁኑኑ አክትሞለታል።

ስማ ያገሬ ሰው! ከእንግዲህ ወዲህ አንድ መድረክ የመቆም አጋጣሚ ተፈጥሮ በአንድነት ለመቆም የተገደድን እንደሆነ እንካ እንዳለፉት የየዋህነት ዘመናት አንዱ በአጀንዳ ሌላውን ደግሞ በሞኝነት ሳይሆን አብረን ስንቆምና ስንጨባባጥ በደንብ በሚገባ ተዋውቀን ብቻ ሳይሆን እንደምንተዋወቅም ጭምር ታውቆ ነው የምንቆመው የምንጨባበጠውም። በማን ላይ ቁመሽ እግዜርን ታሚለሽ! ለነገሩ ይህ ግልሰብም ሆነ ሌሎች አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በሚቆሙበት መድረክ የሚታዩ ቀሚስ ለበስ ሰመ ሊቀ ጳጳስና መኖክሴ ሁሉ አንዳቸውም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አይወክሎም። ምክር ሁለት!

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ፦ “ለኦሮሞዎች የምለው ምንድ ነው … ” – ከምንም በላይ ግለሰቡ በአንዲት ሉዓላዊት በሆነች ኢትዮጵያ በምትባል ሀገርም ሆነች በኢትዮጵያዊነት ጨርሶ ስለማያምን ይልቁንስ የተባበሩት መንግስታትም ሆኑ የዓለም ማህበረሰብ (ኤርትራን አይጨምርም) በማያውቋት መሬት የሰከረ፥ ናላው የዞረበት፥ የታወከና ቅኔ በጉንጩ ትምክህተኛ ግለሰብ በመሆኑ ለጊዜው ይህችን ጠባብ አእምሮ የወለዳት እምነቱን በሌላ ፖለቲካዊ መድረክና አንድምታ መልስ ስለምሰጥበት ለጊዜው ብዙ

ላለማለት ግድ ብሎኛል። ቢሆንም ግን ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ መልክና ገጽታ ተስተካካይ የሌለው አስተዋጽዖ በማበርከት ረገድ ከፍተኛ ሚና የተጫወተች ባለውለታም የሆነችው ትውልድና ቅርስ ጠባቂትዋ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንና የእምነትዋ ተከታዮች ምእመናን እንዲሁም በአጠቃላይ የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የጦርነት፥ የጥላቻ፥ የአመጽ፥ የክተትና የወረራ ጥሪዎቹና አጀንዳዎች ግን ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በስፋትና በጥልቀት በተከታታይ እንማማራለን።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ፦ “እኔ ባለሁበት ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ሙስሊም ነው።” ልብ ይበሉ ኢ- ፍትሐዊ ኢ- ዲሞክራሲያዊ የሀገርና የትውልድ ጸር የሆኑ አንባገነናዊ አመለካከት የነገሰባቸውና የተጸናወተባቸው ግለሰቦች ምንጊዜም 99 በሚልዋት ቁጥር ልክፍት የተለከፉና የተጠመቁባት አፍ መፍቻ ቃንቃቸውም ናት። ዓይናቸው በስብ፥ ልቦናቸውም በትዕቢትና በእብሪት ተዳፍኖዋል/ተወጥሮዋልና ለምን? በማለት ራሳቸው የሚጠይቁበት መንፈስም የላቸውም። የሚገርመው ግን ይህ ግለሰብ መልስ አለው።

ተናጋሪው ግለሰቡ ከየትኛው የኦሮሞ ክልል ክፍል አንደበቀለ ባላውቅም በራሱ አንደበት እንደገለጸው የኖረበት አከባቢ 99 በመቶ በእስልምና እምነት ተከታዮች የተንበሸበሸበት ምክንያት ሲያብራራና ለብዙሐን ምስጢር ሆኖ ተሰውሮ የኖረውን ጉድ በአደባባይ ሰሚ ጆሮ ላለው ፍትረት ሁሉ ግልጽ አድርጎታል።

ተናጋሪው በኖረበት አከባቢ ከእስልምና እምነት ውጭ ሌላ እምነት ብሎ ነገር እንደሌለ አለመኖሩም ብቻ ሳይሆን እንደማይፈቀድ፥

• እስልምና የአከባቢው ብሔራዊ ሃይማኖት አንደሆነ:: በሌላ አነጋገር በተናጋሪው አከባቢው የሃይማኖት ነጻነት እንደሌለ፥

• በአካባቢው የሚኖር ማንኛውም ዜጋም በአከባቢው በሰላም ለመኖር እስከፈለገና ምርጫው እስካደረገ ድረስም በእስልምና ማመን የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ፥

• ህገ መንግስታዊ መብቴ ተጠቅሜ የወደድኩት አደርጋለሁ/እሆናለሁ የምትል አንገትዋ የከበደባት ነስፍ የተነኘች አንደሆነ ወይንም አንገቱን ቀና ያደረገ፥ የእስልምና እምነት በግዴታም ሆነ በውዴታ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ሁሉ ህጻን ሽማግሌ አንስት አቅመ ደካማ የሚል በሌለበት አንገቱ በሜንጫ ተመቶ እንደሚጋደም ግልጽ አድርጎታል።

መቼም ሰው የሰውን አንገት አንደ ጎመን ለመቀንጠስ ያልራራና በሜንጫም አጋድሞት ሲያበቃ መለከት ነፍቶ፥ አፈርህ ያቅልልህ፥ ነፍሰ በጻድቃን ማረፍያ ያሳርፋት እያለ በክብር ይቀብረዋል ብሎ ማሰብ ሲበዛ የዋህነት ነው። እንግዲህ በእንዲህ ዓይነት አሰቃቂ በሆነ የግድያ እልቂትና ሞት ሰለባ የሆኑ ዜጎች ቤት ይቁጠረው። የሚያሳዝነው ግን ኢትዮጵያውያን የክርስትንና እምነት ተከታዮች በሀገራቸው/በምድራቸው ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ ወንድሞችና እህቶች የሆኑ ወገኖቻቸው በእስልምና አላመናችሁም እስልምናን አልተቀበላችሁምና ዋጋችሁ ይህ ነው! እየተባለ የሜንጫ/ሰይፍ ሰለባ መሆናቸውንና እየሆኑ እንዳሉም አንዲህ ያለም ለሰሚ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ሰይጣናዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው እንዳለ አለማወቁ ነው።

ጥጉ: ሰውየው (ተናጋሪው) የሰው አንገት በሜንጫ እየቀላ ቢያድግ ነው እንጂ “እኔ ባለሁበት ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ሙስሊም ነው። ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው።” ብሎ ባልተናገረ ነበር። የለመደውን ሲያጣ ግን አሜሪካ ጠቀምጦ ወገኖቹን (ኢትዮጵያ የሚገኙ የእልምና እምነት ተከታዮች) ያደገበትን ተመክሮ በማውሳትና በማካፈል እንዲሁም የእምነታችሁ ግዴታ ነው ሲል እልቂትን በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ለማድረስ አፉን ከፈተ። ቀጣይ አዋጁ ግን በሜንጫ አገታቸውን መቶ የጣላቸው የጹሐን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ስም ዝርዝር መናገር ይጠበቅበታል።

ይህ ግለሰብ (ተናጋሪው ግለሰብ ማለት ነው) በሃይማኖት ነጻነትና በዜጎች እኩልነት የማያምን ነፈዝ ብቻ ሳይሆን “ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው” እንዲል ያለምንም ውጣ ውረድና የችሎት ውሎ የሰው አንገት ለመቅላት መፍጠኑ ሌላ ማንም ሆኖ ሳይሆን፥ የሕግ የበላይነት ብሎም ነገር ለዚህ ሰው ከቀልድ ያለፈ ምንም ዓይነት ትርጉም የማይሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ ሰብዓዊነት ብሎ ያልዘራበት አረመኔ ቅጥረኛ ነፈሰ ገዳይም ነው።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ፦ “ጎንደር ውስጥ ግን ያለና የነበረ ችግር ሲነግረኝ ይሄ መለወጥ አለበት ነው”። ሃሳቡ ማን እንዳነሳውና ስለ ምን ርእሰ ጉዳይ በሚነጋገሩበት ወቅትም የጎንደር ጉዳይ አንስተው እንደተወያዩ እርግጠኛ ባልሆነም አንድ ግልጽ ስለሆነ ጉዳይ ማለትም የተናጋሪው ግለሰብም ሆነ በዙሪያው ያሉ/የሚገኙ ጽንፈኛ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጥማትና ጩኸት መጫረሻና ግብ ግን ምን እንደሆነ በጥንቃቄ አብረን እንድንመለከት እወዳለሁ። የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ ያደገበት አከባቢ በሜንጫ አማካኝነት አከባቢው በእስልምና እምነት የበላይነት የተጥለቀለቀ እንደሆነና የአከባቢው ነዋሪዎችም ሌላ እምነት የመከተልም ሆነ የማመን ምንም ዓይነት ነጻነት እንደሌላቸው ከተናጋሪው አንደበት ሰምተናል። እንግዲህ ይህ ሰው ስለ ጎንደር ሲሰማም ሆነ ሲጠይቅ (ከሁለቱ አንዱ) ያልተዋጠለት ነገር እንዳለ ከአነጋገሩ ለመረዳት ይቻላል። ይኸውም ለምን? አንደ ትውልድ መንደሬ ጎንደርም በእስልምና እምነት መጥለቅለቅ አለባት የሚለውን ቁጭት ማለት ነው።

በነገራችን ላይ ቀደም ሲል ግልሰቡ በሰጠው ምስክርነት መሰረት ተናጋሪው ግለሰብ እስልምናን በመላ ኢትዮጵያ በሜንጫ/ በሰይፍ የማስፋፋት ካለው ዕቅድና ዓላማ የተነሳ ስለ ትውልድ መንደሩ የእስልማና እምነት ተከታዮች የበላይነትና ከፍተኛ ቁጥር እንዲሁም “እንቢ ለኢስላም!” ያለ ደግሞ በሜንጫ አንገታቸው አየመቱ የጣልዋቸውን ዜጎች ቁጥር ብዛት የልብ ልብ እየተሰማው በጀብድነት ሲናገርና ሲዘረዝር ይሆናል ጋደኛውን በጎንደርና አከባቢዋ ስላለ የእስልምና እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል እንዲነግረው የነዘነዘው። የሙስሊሞች ቁጥርም ከክርስትና እምነት ተከታዮች ቁጥር አንሶ ሲያገኘው ይህ ሰው የሜንጫ ያለህ! በማለት ጉባኤ ጠርቶ መሬት አትሁኒኝ ሲል የሚታየው።

ከዓውደ ንግግሩ ሳይወጡ “ያለና የነበረ ችግር” የምትለዋን አነጋገር ለመፍታት/ለመረዳት “ይሄ መለወጥ አለበት ነው” የሚለውን የሃሳቡ ማሳሪያ በአግባቡ መረዳት ይጠበቅብናል። የዚህ ሰው ቁጭት በጎንደር የእስልምና ተከታዮች የሆኑ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ለምን እንደ ትውልድ መንደሬ ሜንጫ ይዘው አይወጡም? እንዴት ክርስቲያኑ ማህበረሰብ ማንበርከክ ማሰገድ ያቅታቸዋል? በሀገሩ ሜንጫ የለም ወይ? ወይስ ሙስሊሙ በአላህ ማመን አቁመዋል? ነው። አንደ ችግር የሚያነሳውም የሙስሊሞች ቁጥር ከክርስትና እምነት ተከታዮች ቁጥር አንሶ ስላገኘው ነው። ይህን ሪፖርት ከሰማበት ዕለት ጀምሮም የእስልምና ጉዳይ አጀንዳው አድርጎ የተነሳበት ዋና ምክንያትም ዜጎችን በሜንጫ አንገት አንጋታቸውን እየመታ ሳይወዱ በግድ ያለ ፈቃዳቸው ለማሰለምና ለማሰገድ ነው። ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮኸለች!

በእርግጠኝነት ለመናገር ያክል ይህ ሰው ስለ ጎንደር የእስልምና እንቅስቃሴ ሪፖርት ሲሰማ (ከትውልድ መንደሩ የእስልማና እምነት የበላይነት በማነጻጸር ማለት ነው) የሰማውን ሪፖርት እንዴት እርር ድብን እንዳደረገውና እንዳበሸቀው ቀደም ሲል “ስለ እስልምና ብዙ መናገር የጀምርኩ አንድ ከጎንደር የመጣ ጛደኛዬ ስለ አገኘሁ ነው።” ሲል አንደገለጸው ቀድሞውኑ የሚያስብ አእምሮ ካልፈጠሮቦትና የአልቃይዳ ባለማልም ካልሆኑ በስተቀር ይህ ግልሰብ ማን መሆኑና የማን አጀንዳ እንዳጎበጠው ለማወቅ ይቸገራሉ የሚል እምነት የለኝም።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ፦ “ይሄ መለወጥ አለበት ነው”። ከዚህ ሁሉ በሃላ “ምኑ ነው የሚለወጠው?” እንደማይሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ከፈለጉ ደግሞ ይሄውሎት። ተናጋሪው “ይህ መለወጥ አለበት ነው” የሚለው ጎንደር አንደ ተናጋሪው ትውልድ መንደሩ በእስልምና እምነት የበላይነት ብቻ ተጥለቅልቃ ማየት ነው ለውጡ። ይልቁንስ እንዴት? ለምትለዋን ጥያቄ ግን የህይወትዎ ምንጭ በሆነው በልብዎ ላይ መብራት ላበራሎት እወዳለሁ። ተናጋሪው “እኔ ባለሁበት ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ሙስሊም ነው። ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው።” እኔ ባለሁበት? በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው? ለዛውም በአሜሪካ? “እኔ በነበርኩበት … / እኔ በወቅቱ … ” ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ አምናለሁ። መቼም ሰው አይሳሳትም አይባልም እኔም በባዖድ ቃንቃ ስጽፍ አልፎ አልፎ አንዲህ ያለ መጠነኛ ችግር አይታጣብኝም ዳሩ ግን የተናጋሪው ግድፈት ለአማርኛ ቃንቃ ካለው ጥላቻና ጠይቆም ላለማወቅ ከሆነ ግን በእውነቱ ነገር አሳፋሪ ነው። የሀገሬ ሰው “ቢራቢሮ ምንዋን ያልከደነች ምድርን ከደነች!” እንደሚለው ነው ነገሩ።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ ያደገበትና የኖረበት አከባቢ የእስልምና ሃይምኖት ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ያለ ተከታይ ብቸኛ የአካባቢው ሃይምኖት የመሆኑ ምስጢር ሜንጫ ናት! ብሎ በአደባባይ ሹክ ካለን ታድያ ተናጋሪው ጎንደር ላይ ደርሶ ሃሳቡን ይቀይራል ብለው ያምናሉ? እንደው አጋንንት አንደተገለጡለት አህያ የምያናፋው ምን ቢሆን ነው ብለው ነው? በአገሩ (በጎንደር) ሜንጫ የለም ወይ! ሲል አይደለንም? ጥጉን እነግሮት ዘንድ የወተውቱኝ እንደሆነም አይደለም ይህ ግለሰብ አባቶችም በአመጽ በሰይፍና በዝርፍያ ሲበዙና ሲስፋፉ መጡ እንጂ በሰላምና በትምህርት አያምኑም ብቻ ሳይሆን ሰላምና ትምህርት እንደሚያስቃዣቸው ሁላ ቅጭዋን ስነግሮት በአክብሮት ነው።

ያልጠረጠረ ተመነጠረ!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s