ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልሰው አለ እንጂ ጣለው አላለም! ክፍል ሦስት

“እናንተ ኦሮሞዎች የራሳችሁን መብት ስታስከብሩ የራሳችሁን ማንነት ስታስከብሩ የፖለቲካ ስልጣንን በእጃችሁ ስታስገቡና የአከባቢውን ደህንነት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሂደት ተጽእኖ ማድረግ ስትጀምሩ ጎንደር ያለው የሃይማኖት ወንድማችሁ ይከበራል ትግራይ ያለው የሃይማኖት ወንድማችሁ ይከበራል።” የጎሳ ዜማ አቀንቃኝ (racial activist) ጀዋር መሐመድ

“እናንተ ኦሮሞዎች …” የገረመኝ ነገር ከ ፳ ዓመት በፊት ነፍሳቸው ይማር መዋቹ የኢ.ፈ.ዲ.ሪ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተር የትግሉ መራራነት: ሕዝቡ የከፈለውን ዋጋና ያስመዘገበው ድል በማስመልከት በመቀሌ ከተማ ተገኝተው  ያደረጉት ንግግር ከአውዱ ውጭ እየተተረጎመ “ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዘረኛ ናቸው/ነበሩ” እየተባለ ዛሬም ድረስ ዜና ይሰራበታል። ይህ ሰው ግን እንዲህ ያለ አሳፋሪ ንግግር ሲያደርግ የተገላቢጦሽ ሕዝብ “የለም!” እያለ ቁጣውን ሲገልጽና ድምጹን ሲያሰማ “ሚድያዎች” ደግሞ በአንጻሩ ዝምታን የመምረጣቸው ጉዳይ ባይደንቀኝም ገርሞኛል። በመሰረቱ ከዚህ በላይ ዘረኝነት: የአንዲት ሀገር አንድነትና የሕዝቦችዋን ህልውና የሚፈታተን ጎጠኛ አነጋገርና ከፋፋይ መልእክት ከወዴት አለ? አንድ የኢህአዴግ ባለስልጣን ያላለውን አለ፥ ቢልም ነገሩን በማጣመምና በቆርጠህ ቀጥል በፈጠራ ዜና ዜጎችን ከማወክ የተባለውን በማስረጃ ምላሽ መስጠት ሕዝብን ማንቃት አይቀልም ነበር ወይ? ለመሆኑ በኢትዮጵያውያን ስም ነገርን የሚያራግቡ “መገናኛ ብዙሐን” ዓላማ ምንድ ነው? ኢትዮጵያንን ማልማት ወይስ ማውደው? በውኑ የኢትዮጵያ መልካምነትና የሕዝቦችዋ ሰላማዊ መቀባበል የማይዋጥላቸው ምስጢሩ ምን ይሆን? የሁከት ያለህ! እየተባለ ነገርን ብቻ ማመላለስስ አያስተዛዝብም ወይ?

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ “የራሳችሁን መብት ስታስከብሩ የራሳችሁን ማንነት ስታስከብሩ …” መብትህንና ማንነትህን ማስከበር ማለት ለዚህ ሰው የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ብሔር ተጠናክሮ ኦሮሚያ የምትባለው ክልል ሲገነጥልና ሲስገነጥል በዚህም አያበቃም በምኒሊክ ዘመን የበደለህን የአማራ ገዢ መደብ አሁን ደግሞ በዘመነ ኢህዴግ “እየመዘረበረህ ያለው” የህውሐት ቡድን ድባቅ ስትመታና በቀልህን ስትወጣ ብቻ ነው። እያለ ለመሆኑ የሚጠራጠር ሰው ካለ ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አጋጣሚዎች በአጀንዳው የሚስማሙ (ሰዎቹ) ሰብስቦ ያደረጋቸው ንግግሮችና በቅርቡ ደግሞ ከአልጀዚራ ስትሪም ያደረገውን ሙሉውን ቃለ ምልልስ እንዲመልከት ነው የሚጠየቀው።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ “የፖለቲካ ስልጣንን በእጃችሁ ስታስገቡና የአከባቢውን ደህንነት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሂደት ተጽእኖ ማድረግ ስትጀምሩ” በግሌ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የኢህአዴግ መንግስት እንጂ ሌላ አለ/ነው ብዬ አላምንም። ይህን በልዩነት እንለፈውና አንዳንዶች እንደሚያስተጋቡትና ሕወሐትም በሆነ ባልሆነ ከሚወገዝበት፥ ከሚኮነንበትና ከሚነቀፍበት አንዱ ኢኮኖሚውን ፖለቲካውን ተቆጣጠረ ነው። ይሄውሎታ! አንዱ የሚወቀስበትን ለዚህ ሰው ደግሞ ወመጣጫ ሲሆንለት። ውድ አናባቢ! ተናጋሪው በሌለ ነገር መቃዠት መብቴ ነው ካለ እስቲ እርስዎ ደግሞ ለአፍታ በምናብዎ ተደራሲው ሕዝብ የፖለቲካ ስልጣን በእጁ ሲያስገባ፥ ደህንነቱና ኢኮኖሚውን ሲቆጣጠር ይታይዎት። ምን ይታይዎታል? ሜንጫ በእጁ ይዞ የተሰለፈ ሰራዊት! ትክክል አይተዋል።

የስልጣን ባለቤት ስንሆን: ኢኮኖሚውን ፖለቲካውንና ድህንነቱት ስንቆጣጠር የተሻለችና የበለጸገች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን! ፍትህ፥ ዲሞክራሲ፥ ነጻነት፥ እኩልነትና የሕግ የበላይነት እናነግሳለን! እኮ አይደለም መልእክቱ። ሰውዬው እያለ እያለ ያለ’ኮ በአንድም በሌላም የምኞታችን ያገኘን ዕለት ማለትም ፖለቲካዊ ስልጣኑ፥ ኢኮኖሚውና ደህንነቱ የተቆጣጠርን ዕለት ዎዮልሽ ኢትዮጵያ! ውዮ በል አማራ! ወዮ በል ህወሐት! እኮ ነው ነገሩ። በሌላ አነጋገር ስልጣን እጃችን የገባ ዕለት  የልባችን እናደርሳለን ነው!! ያን ዕለት የዓይኑ ቅንድብ ያላማረህን ሁሉ ማረድና መጉመድ ያንተ ይሆናል። ያን ዕለት ዜጋ እንዲሰልም ተጠይቆ እሺ ያለ እንደሆነ መልካም እንቢ በማለት አንገቴ አቀናለሁ የምትል ነፍስ የተገኘች እንደሆነ ግን በሜንጫ እየመታህ ትነግሳለህ! ነው ትንቢቱ።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ “ጎንደር ያለው የሃይማኖት ወንድማችሁ ይከበራል ትግራይ ያለው የሃይማኖት ወንድማችሁ ይከበራል።” በመሰረቱ ትግራይና ጎንደር የሚኖረውን የእስልማና ሃይማኖት ተከታይ ማህበረሰብ ከሃይማኖታቸው የተነሳ አድልዎና መገለል የደረሰባቸው መቼ ነው? ግፍ ፈጻሚው በዳዩስ ቢሆን ማን ነው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ወይስ በአንተ ዓይነቱና መሰል ያልተጻፈ የሚያነቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች ክርስቲያናዊ መንግስት ተብሎ የተፈረጀውን የኢህአዴግ መንግስት? በደፈናው እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ ከማለትስ ችግሩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ደረሱ የሚባሉ ችግሮችን መዘርዘር አይቀልም ነበር ወይ? ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደ ኢትዮጵያዊ ከሌላው እምነት ተከታይ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ የጎደለው ነገር ምን ቢኖር ነው? ከሚከተለው ሃይማኖት የተነሳ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዚህ ነገር ተጎድተዋል ማለት ይቻላልን? ባይጎድለው ነው እንጂ ቢጎድለው ኖሮማ የደረሰበትን በደልና ግፍ ማቅረብ ነበር ሰሚ ጆሮ ሊማርክ ይችል የነበረው።

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ “… የአከባቢው ፖለቲካ በብሔር የተከፋፈለ ነው” አንባቢ ሆይ! ተናጋሪው ይህን ሲል ውስጠ ነገሩ አግኝተውታል? ምን እያለ እንደሆነስ ልብ ብለዋል? ኢህአዴግ ከፋፍሎ ለመግዛት ያመቸው ዘንድ አከባቢውን በብሔር እንደከፋፈለው ሁሉ እኛ ደግሞ አሁን ኢህአዴግን ለመጣልና የምናልማት ኢስላማዊት ሀገር ታላቂትዋ ኦሮሞ ለመመስረት ሕዝብ በሃይማኖት ከፋፍለን ብናተረማምሰውና እሳት በማኸከሉ ብናነድበት ምን ይለናል? ምን አለበት? ነው እኮ ነው እየተባለ ያለው። ቀደም ብሎ ግን “ይሄንን ሕዝብ ለመከፋፈል አይደለም” ሲል የተናገራትን ነገር – በሃይማኖት ሕዝብን መከፋፈል ሕዝብ መከፋፈል አይባልም/አይደለም እያለ ነው? ስል ራሴን ለመጠየቅ ዳድቶች ነበር ስቆይ ግን ዋዛው ገባኝና አይ! ምናልባት ሰውዬ ሃሳቡን በአማርኛ በሙላት የመግለጽ ችግር ስለሚስተዋልበት “በኦሮምኛ” ቋንቋ መናገሩ ይሆን ብያለሁ። እርስዎስ ምን ይላሉ?

የጎሳ ዜማ አቀንቃኙ ግለሰብ እንዲህ አለ “የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ለእስልማና መጠናከር ወሳኝ መሆኑ በተለይ ሌሎች መገንዘብ አለባችሁ። በጣም ወሳኝ ነው።” እዚህ ቦታ ላይ “ሌሎች” ተብለው የተመላከቱ ማንን አንደሚያመላክት ግልጽ አይደለም። ኦሮሞ ያልሆኑ የእስልምንና እምነት ተከታዮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግን እገምታለሁ። ወጣም ወረደ ይህ ስብሰባ ክእንግዲህ ወዲህ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭ የሚደረጉ ማናቸውንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ስብሰባዎችና እንቅስቃሴዎች በንቃት እንድንመለከት ይህ ስብሰባ በቂ ማስጠንቀቂያ/ማንቅያ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

እንደ ተናጋሪው አነጋገር ኦሮሞና እስልምና የማይነጣጠሉ የአንዲት ሳንቲም ሁለት ገጽታ ከሆኑ፤ የኦሮሞ መጠናከር የእስልምና መጠናከር ከሆነ የእስልምና መጠናከር ማለት ደግሞ የኦሮሞን መንግስትነት የሚያበስር ከሆነ “ከድምጻችን ይሰማ!” ባዮች ሰልፈኞች ጀርባ ያለውም የኦሮምያ መንግስት ለመምስረት ኦሮሞን ገንጥሎ ለማስገንጠል የሚተጋ ኃይል ነው ማለት ነዋ? ቢሆን ነው እንጅ። የኦሮሞ ትግል እስልምናን እዚህ ካደረሰ የእስልምና ተጠናክሮ መውጣት ማለት ደግሞ የኦሮሞ ትግል የመጠናከሩ ምልክት ከሆነ ከድምጻችን ይሰማ ጀርባ ሃይማኖታዊ ሽፋን ጭሆት የኦሮሞ ሊሂቃን ጥምና ሕልም እውን ለማድረግ የወጣ ገንጥሎ አስገንጣይ ኃይል ለመሆኑ ታድያ ስንቱ ለሀገሬ ሰው ልብ ብለዋል? ነው የእኔ ጥያቄ።

አቤት! የእስልምና እምነት ተከታዮች ጩኸት ደግፎ እንዲወጣ ጥሪ እየቀረበለት ያለውና የወጣ ዜጋ በየዋህነት የገዛ አገሩን ለመበጣጠስና ኦሮሚያን ለመገንጠል መሆኑ ነው? አሁን አሁናማ ጩኸቱ በድል የተጠናቀቀ ዕለት እስላም- ኦሮሞ ስልጣን ላይ ሲወጣና ዜጎች ሳይወዱ በግዳቸው እንዲሰልሙ ሲጠየቁ በኃይልም “አላህ ወአክበር በሉ!” እየተባሉ ሲንገላቱ እንቢ ያለ (አንገቱ ቀና ያደረገ ) ደግሞ በስለታም ሰይፍና በሜንጫ እየተመታ ሲወድቅ ታየኝ። እስላም- ኦሮሞ ስልጣን ላይ ሲወጣ “ታየኝ” እኮ ነው የምሎት። ታድያ ስልጣን ላይ የሚወጣው የተሻለ ስርዓት ለመመስረት ሳይሆን ከዘመናት በፊት ምኒሊክ (አማራ) አድርሶብኛል የሚለውን ግፍና በድል ሂሳብ ሲወራረድ፤ አክሱም ጽዮን ተደርም/ፈራርሶ በምትኩ መስጊድ ሲቆም “ታየኝ። “ታየኝ” የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው መስጊዶች ስብቡ።

ሃሳቤን ለማጠቃለል ያህል የዚህ ግለሰብና የግብረ አበሮቹ ዓላማና ግብ በተመለከተ ሁለት ነጥቦችን በማስቀመጥ ጽሑፌን ልቋጭ።

  • አንደኛ፡ የዚህ ግለሰብ ጥረትና ሕልምም ሆነ “የድምጻችን ይሰማ!” ጩኸት ኢትዮጵያ እንደ አገር የመለወጥ የማበልጸግና ገጽታዋን የመቀየር ዓላማና ራዕይ ያነገበ ሳይሆን በአንጻሩ ስምዋ ሲጠራ የሚከነክናቸው ሀገረ ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀውን ሀገር በማፈራርረስና ሕዝቦችዋንም በማተረማመስ ኦሮሚያ የምትባል ኢስላማዊት ሀገር የመፍጠር ሕልም፤
  • ሁለተኛ፡ ኦሮሞ በቀድሞ ዘመን (በምኒሊክ/አማራ) የዘር ማጥፋት እንደተካሄደበት: እንደተረገጠና እንደተጨቆነ አሁን ደግሞ በዘመነ ኢህአዴግ ዘመነ ስልጣን እየተመዘበረ እንደሚገኝ: ገናም ከጭቆና ያልወጣ ማህበረሰብ እንደመሆነ አዲስ ታሪክ በመፍጠርና አስመስሎ በማቅረብ “ኦሮሞ ነኝ!” ለሚል ሁሉ ኢትዮጵያ ከምትባል ሀገር ምንም ዓይነት እድል ፈንታ የለህም! የሚል ድምጽ በማስተጋባት ከዚህ የተነሳም አጋጣሚዎችን የሚፈጥሩት ቀዳዳዎች በመጠቀም ምድሪቱ የደም መሬት ማድረግ ሕዝቦችዋንም ደም መቃባት ነው።

ጥብቅ ማሳሰብያ፦ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ “ኦሮሞ” ተብሎ የተቀመጠውን ቃል ተናጋሪው “አድረስ” ያደረገውን ክፍል እንዲሁም ሰሚም በተናጋሪው ግለሰብ ቃልና ሃሳብ ተስማምቶ መስማማቱ “አላህ ወ አክበር!” ሲል ድምጹን ሲያሰማ የነበረውንና መልእክቱን በተለያዩ መንገዶች የማዳመድ እድሉ ገጥማቸው የግለሰቡን አቋም ለተጋሩና ለሚጋሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ብቻ ይመለከታል።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s