ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልሰው አለ እንጂ ጣለው አላለም! ክፍል ሁለት

ባለው ንባባችን በተመሳሳይ ርዕስ “እስላማዊት ሀገረ ኦሮሚያ” የመመስረት ህልም ካላቸው ግለሰቦችና ቡዱኖች መካከል አንድ የሆነ የጎሳ ዜማ አቀንቃኝ (racial activist) ጀዋር መሐመድ የተባለ ግለሰብ በሚኒሶታ በሚኒያአፕለስ ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆኑ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ሰብስቦ ባደረገው እጅግ አሳዛኝና አእምሮ ላለው ሰው የማይመጥን ጽንፈኛ ንግግር ተንተርሰን ለመግቢያ ያክል አንደተመልከትን በይደር መለያይታችን የሚታወስ ሆኖ በዛሬው ዕለት ደግሞ የጽሑፉን ዓላማ በሚገባ ለአንባቢያን ለማስያዝና ለማስጨበጥ ያክል በተዛባ መነጽር እየታየና እየተገመገመ በብዙዎች ዘንድ የተሳሳተ ምስልና ገጽታ እየተሰጠው ያለ የክርስትና እምነት እንዲሁም የቤተ እምነቱ ተከታዮች ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በአጭሩ መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦችን አንስተን እንመለከታለን። በመንደርደሪ ሃሳቤ እንደገለጽኩት ክርስትና ብዙሐኑ ከውጭ ያሉት እንደሚስቡትና እንደሚገምቱት ሳይሆን ክርስትናም ሆነ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ማንም እንደመሰለው እንደሚገልጸው ሳይሆን መጽሐፉ እንደሚያስተምረው እንደሚገልጸውና እንደሚተረጉመው እንዲሁ ነው።

ክርስቲያን፦

• የራሱ ያልሆነ፥
• ለሱ ያልተገባ፥
• ያልተሰጠው፥
• ያልተፈቀደለት፥
• መምህሩ ያላስተማረው፥
• ቅድሳት መጻህፍቶቹን የማይመሰክሩለትን ገንዘቡን አያደርግም፤ እግዚአብሔር በማይከብርበት ህይወት ውስጥም አይገባም አይገኝም ተባለ እንጂ:

ክርስትናያን ማለት፥

• ሞኝ፥
• ስትዘርፈው፥
• እንደ ችቦ ስታነደው፥
• እንደ ሽንኩርት ስተከትፈው፥
• እንደ ስንዴ ስታበጥረው፥
• እንደ እንጨትም ስትሰነጥቀው፥
• እንደ ምናምንቴ እየተቆጠረም ሰላሙን ስትነሳው፥
• በዚህ ምድር ያለውና ከጌታውም የተቀበለው እምነቱን ስትወድበት፤
• ለባአል ስታሰግደው፥
• እንደ አሳማ የሆነ ያለሆነውን ቅጠል ብላ እያልክ ሜንጫ/ሰይፍ ከአንገቱ ላይ አኑረህ እንደ ፍየል ቅጠላ ቅጠል ስታግጠውና አፉ ውስጥ ስትወትፍለት “ለጌታ ክብር ይሁን!” እያለ ሁን የተባለውን የሚሆን የራሱ የሆነ ነገር የሌለው፥ ወፍ ዘራሽ፥ አሳዛኝ፥ ምስኪንና ጌታ የሌለው ባሪያ ማለት ነው ያለ ማን ነው? ስለ እምነት ዋጋ መክፈልን በሚጠየቅበት ዘመን አማኞች ዋጋ ከፍለው አልፈዋል ገና አሁንም ዋጋ መክፈል ይቀጥላል ይህ ማለት ግን ቀደምት የክርስትና እምነት ተከታዮችና የእምነት አባቶች ከላይ ከፍ ሲል የተጠቀሱና ሌሎች መራራ የእምነት ዋጋ ከፍለው ያለፉ ሰዎቹ ሞኞች ስለ ነበሩ ነው ብለው ያምኑ ይሆን እንዴ? እንግዲያውስ ሞኙ ሌላ ማንም ሳይሆን እንዲህ ብሎ የሚያስብ አእምሮ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።

እንግዲህ ጥጉ ይህን ይመስላል፦ ማንኛውም የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ አሳዳጆቹን እንዲሁም ክፉ አሳቢዎች ከልብ መውደድና መመረቅ እጆቻቸውንም የልባቸውን ምክር እንዳትፈጽም በትጋት መጸለይ የአንድ አማኝ ግዴታ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ አንደ ዜጋ ደግሞ ራሱን ከማናቸውም ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ወረራ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ራሱን የመከላከልና ጠላቹን የማሳጣት ባለ ሙሉ መብት ነው። መጽሐፍ “ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ” እንዲልም ከመነሻው ነገር እየሸተተህ፥ ጸብን ፍለጋ፥ በተጨማሪም “ጎረቤቴ እኔ የማመልከውን አምላክ የማያመልክበት ምክንያት ምንድ ነው?” በማለት በሃይልና በጉልበት ጎረቤትህ ለማንበርከክ ሰይፍ ታጥቀህ የሰው ደጅ አታንኳኳ እንጅ ሜንጫ: ሰይፍና ፓንጋ (ገዠራ) ይዞ “የምልህን ካላደረግክ፥ የምለውንም ደግመህ ጮክ ብለህ ካላወጅክ፥ የማምነውን ካላመንክ ቀንዋ ያንተ አይደለችም!” በማለት አንገትህን ለመቅላትና ለመቀንጠስ ደጅህን ለሚያንኳኳ ግን እቅፍ አበባ ይዘህ ጠብቀው የሚል መጽሐፍ የለም። ጥበብ በዚህ አለ!

ኢየሱስ እንደተወለደ በሄሮድስ ሰይፍ መሞት ነበረበት! ብለው የሚሞግቱ/የሚያምኑ ከሆነም በእውነቱ ነገር መቀላቀል ጀምረዋል! በተረፈ ግን አንድ ግለሰብ/ዜጋ/ሕዝብ ምንም ይመን ምን ለሚያምነው እምነት ራሱን የማይሰጥና የማይከላከል: በምድር በአጸደ ስጋ እስካለ ድረስም ሀገሬ የማይልና ለሀገሩ የማይሞት አማኝ ካለ እሱ አይደለም ከውሃና ከመንፈስ ሊወለድ ከስጋና ከደምም አልተወለደም።

እዚህ ላይ አንድ ግልጽ እንዲሆን የምፈልገው ነጥብ አለኝ። ይኸውም: ጸሐፊው ማንኛውም ዓይነት ጦርነት: ደም መፋሰስም ሆነ አመጽ አጥብቀው እንደሚቃወሙና ጦርነትና መዘዙ በተመለከተም ከዚህ ቀደም በበርካታ ስራዎቻቸው ጸረ ጦርነት ያላቸውን አቃም በግልጽ መታወቁን እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ጦርነት በምንም አይነት መልኩ ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ አማራጭ መፍሔት ሊሆን አይችልም የሚል እምነታቸው እንደጸና መሆኑን ይታወቅ ዘንድ ሲጠይቁ በአክብሮት ነው። ክርስትናም እንደሆነ በምንም ዓይነት መልኩ ከጦርነትም ሆነ ማናቸውም የአመጽ ተግባራት ምንም ዓይነት ክፍል ወይንም ደግሞ ዕድል ፈንታ የለውምና። ይህ ደግሞ አይደም በአማኖቹ ዘንድ በውጭ ባሉትም ዘንድ የማይካድ ሐቅ ለመሆኑ አያጠያይቀንም። ጦርነት የታውጀበት የክርስትና እምነት ተከታይ ሕዝብ ግን እንደ ግለሰብ ቅድሳት መጻሕፍት መሰረት የሌለው: ምክንያታዊ ያለሆነ: ዋጋ የሌለውና ከንቱ የሆነ ሞት ለመሞት ምርጫው ካላደረገ በስተቀር እንደ አማኝም እንደ ዜጋም አሻፈረኝ በሚል መናፍስትም ሆነ በአካል የሚገለጥ የጠላት ኃይል ሁሉ ጫንቃ ላይ ወጥቶ ድልን ማወጅ የግሉ ነው።

የዛሬ ጽሑፌን የምዘጋው ያለፈውን በደልና አበሳ በይቅርታ መታለፉን ከማውሳቴ በተጨማሪ ከእንግዲህ ወዲህ ግን የሀገር ባለ ውለታ የሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በተከታዮችዋ ምእመናን እንዲሁም በአጠቃላይ የክርስትና እምነት ተከታይ ዜጎች ላይ የሚደረገው ማንኛውም ዓይነት ሃይማኖታው ትንኮሳዋጋ እንደሚያስከፍል በማሳሰብ ጭምር ነው። ከዚህ ቀደም የሆነውንና ፖለቲካዊ ሽፋን ተሰጥቶት ተድበስብሶ የለፈውን ኢስላማዊ ጥቃት የክርስቲያኖች የግፍ እልቂትና የበርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ መልሶ እንደማይሆንም ይህን ጽሑፍ ለሚያነቡ ወንዶችም ሴቶችም ኢትዮጵያውያን መልዕክቴን በእርግጠኝነት ለማስተላለፍ እወዳለሁ።

ከእንግዲህ ወዲህ፦

 • “አንድ ነን!” እየተባለ ሕዝበ ክርስትያን በአፈ ጮሌዎችና ለሆዳቸው ባደሩ ስመ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ልብ አውልቅ መነኮሳት የሚደለልበት፣ የሚታለልበት፣ የሚጭበረበርበትና የሚደናገርበት፤
 • ባልጠበቀውና ባላሰበው መልኩ የሚያልቅበት: የሚጨፈጨፍበትና በሜንጫ/በሰይፍ የሚመነጠርበት፤
 • ካህን በእጁ መስቀል አንደ ያዘ እንደ ዕንጨት የሚጨስበት፤
 • አማኞች አምላካቸውን ለማምለክ በተሰበሰቡበት በርና መስኮቶቹ ከውጭ ተቆልፈውበት ነዳጅ በላይ ላያቸው ተርከፍክፎባቸው እንደ ችቦ የሚነዱበትና በደቂቃዎች ውስጥ ስጋ አጥንታቸው አመድ የሚሆኑበት፣ ከዚህ ሁሉ የተረፈም የተረፈችውን ነፍሱ በሰይፍ የምትጠናቀቅበትን ሁኔታ አይኖርም።

እናማ ጸሐፊው ይህን ይታወቅልን ይላሉ፦

 • ሁለት ጊዜ ስሕተት፥
 • ሁለት ጊዜ ለቅሶና ዋይታ፥
 • ሁለት ጊዜ አባሽ አልባ እንባ፥
 • ሁለት ጊዜ ሰሚ አልባ ጭኸት፥
 • ሁለት ጊዜ መዘረፍ፥
 • ሁለት ጊዜ በገዛ አገርህ መሰደድ፥
 • ሁለት ጊዜ በእሳት መበላት: መጠበስና መቀቀል፥
 • ሁለት ጊዜ በሰላ ሰይፍ መቀላት፥
 • ሁለት ጊዜ ሞት የለም! አይኖርምምና ቀድሞ በተሳሳተ መረጃና ሸውራራ ዕይታ “ማተማቲክሱ” (ሒሳቡ) ሲያሰሉት የቀለላቸው ሊሂቃን ነገሩ የሒሳብ ሳይሆን የነፍስ ጉዳይ መሆኑን ተረድተው ድጋሜ አቃማቸውን እንዲመረምሩና አካሄዳቸውን መለስ ብለው እንዲሰልሉም ጸሐፊው ምክራቸውን ይለግሳሉ።

ይቀጥላል

ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልሰው አለ እንጂ ጣልለው አላለም!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s