ለአቶ አበበ ገላው:

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል አቶ አበበ ገላው ከተባሉ ግለሰብ (የቀድሞ የኢሳት ሰራተኛ) በኢሜይል አድራሻቸው ለደረሳቸው መልዕክት የሰጡት መልስ። 

ሰላም አቶ አበበ

ስለ እኔ፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ ስለ ሚድያ አጠቃቀምና ስለ ዜጎች ሕጋዊ መብት ያሎት አመለካከት በቀጥታና ደረቅ መረጃ አውቅ ዘንድ ስለ ጻፉልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

በእርግጥ አንድ እርምጃ ወደ ፊት የተራመደ ሰው በቃላት ለማንኳሰስ መሞከርና ዘመቻ መክፈት በእርስዎ አልተጀመረም። ምድር እስካለች ድረስ ነፋስ አለ። ግራ አመለካከት አራማጆችና ኋላቀሮች እዚህ ምድር አስካሉ ድረስም እንዲሁ የሚያውቁት ሆነ የማያውቁትን ግለሰብ ማብጠልጠልና ማቃለል የተፈተነ አስተማማኝ መሳሪያቸው ነውና ብዕር አጣጣሎት ለእኔ እንግዳ አይደለም። አይደንቀኝምም።

በበኩሌ “የቀድሞ ስህተቴን” ላለመድገምና ከስህተቴም ለመማር ካለኝ ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ገንቢ ሂስና ነቀፋ እንዲሁም አስተያየት የምወድና የምቀበል ግለሰብ ነኝ። የተሳሳትኩም እንደሆነ ስህተቴን በአደባባይም ቢሆን መሳሳቴን ለመግለጽና ለመቀበል የሚከብደኝ ሰው አይደለሁም። በአንጻሩ ደግሞ እርስዎን ጨምሮ ከማንም ቢሆን ስራዎቼን ተከትሎ ውዳሴ የምጠብቅ ዓይነት ሰው አለ መሆኔንም ስገልጽሎት በአክብሮት ነው። በነገራችን ላይ መማር ተገቢ መሆኑን ባምንበትም በሌላ መልኩ ግን ወደ ትምህርት ቤት የሄድኩት ምክንያት፥

 1. ከእንደዚህ ዓይነት ተራና ርካሽ ቃላቶች ራሴን ለመጠበቅ፥
 2. ሰዎች አለን በማለት የሚመኩበትን ምንም ቢሆን እንደሚቻል ለማረጋገጥ፥
 3. አደርገዋለሁ ብዬ ከተነሳሁት ዓላማም የተነሳ እንደ አሁኑ ያለ መላላጥ ሲፈጠር ደግሞ ለነገር ፈላጊዎች ክፍተት ላለመፍጠርና፥
 4. ከምንም በላይ ደግሞ የባላንጣዎቼን አፍ ለማዘጋት ነው። ደግሞም አድርጌዋለሁ።

አቶ አበበ ሙልጌታ ለማስተላለፍ ስለፈለግከው መልዕክት የመረጃ እጥረት አለብህ ብለው የሚያምኑ ከሆነ፤ ኢሳት ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅም ስራ እየሰራ ነው ብለው የሚያኑ ከሆነ፤ እርስዎም በግልዎ በዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አምናለሁ፥ በነጻ ፕሬስ አምናለሁ፥ አንጻራዊ አመለካከት ያለው ግለሰብ ሃሳቡን በነጻነት ሲያንሸራሽር ማየት እወዳለሁ ከሆነ ነጥቦ (ከዚህ ቀደም ይህን ሲያደርጉ ግን አላየሁም። ይልቁንስ የተላከሎት ጽሑፍ ሲያፍኑ እንጂ) የአንድ ግለሰብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሀገሩ ባለው ነገር የአቅሙን ለማበርከት በሚያደርገው ትግል ለምሳሌ በስነ ጽሑፍ የተሰለፈ እንደሆነ ስራዎቹን ለንባብ/ለሕዝብ እንዳይደርሱ በማፈንና በማሳፈን ስምም በማጥፋት አላምንም ብለው የሚስቡ ከሆነ፤ ይልቁንስ ከዚህ ቀደም ሕዝብ በፖለቲካዊ አመለካከትዎ የሚያውቆት አቶ አበበ (የኢሳት ባለደረባ) መሆንዎ ቀርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር በመወያየትና በመከራከር የማምን ግለሰብ ነኝ እያሉን ያሉት እንደሆነና አዎ! የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አምናለሁ ብለው የሚያስቡ ከሆነ ይሄው መፍትሔው ቀላል ነው። ይኸውም፦

በአሁን ሰዓት አቶ አበበ የሚገኙበት ሁኔታ ማለትም ኢሳት ገቢ ለማሰባሰብ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ከመሳተፍ የዘለለ ከተቋሙ ጋር ያሎት ግኑኝነት ባልውቅም ቀደም ሲሉ ግን እንደ ግለ ግዛትዎ የፈለጉትን ጠርተው የሚናግሩበት የዓይኑ ቅንድብ ያላመሮት ደግሞ ያገሉበት በነበረ ሚድያ ዜጎች በዜግነታቸው ያለመከልከልና ያለገደብ ሃሳባቸውን በነጻነት የሚገልጹበትን መድረክ አያዘጋጅተው በሚያመችዎት ሰዓት በአድራሻዬ ቢጠቁሙኝ አለሁ በማለት ድምጼን ለሰፊው ሕዝብ፥

 • ለማሰማት፣
 • ጋዜጠኝነት፤
 • ነጻ: ገለልተኛ: ፍትሐዊና ሚዛናዊ ሚድያ፤
 • ፓለቲካ፤
 • ሰብአዊነት ጎጠኝነትንና ጠባብ ዘረኝነት፤
 • ኢትዮጵያዊነት ባንዳነትና ሽብርተኝነት፤
 • እንዲሁም የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ወይ ተምሬ እወጣለሁ ወይንም ደግሞ አስተምሬ አመለሳለሁ። ቀላል!

አውቆት ዘንድ ዕድሉ ስለ ሰጡኝ በድጋሜ አመሰግናለሁ

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s